Hadiya Hosanna ሀዲያ ሆሳዕና

Hadiya Hosanna ሀዲያ ሆሳዕና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hadiya Hosanna ሀዲያ ሆሳዕና, Digital creator, hosanna, Hossana.

የሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ አዲስ የተመረጡ የደጋፊ ማህበር አመራሮች መልካም የስራ ዘመን
12/07/2025

የሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ አዲስ የተመረጡ የደጋፊ ማህበር አመራሮች
መልካም የስራ ዘመን

ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ተነጠቀ*********************በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዶ የነበረው ሲዳማ ቡና ክብሩን ተነጥቋል፡፡ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስ...
01/07/2025

ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ተነጠቀ
*********************

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ ዋንጫውን ወስዶ የነበረው ሲዳማ ቡና ክብሩን ተነጥቋል፡፡

ሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ድቻን 2 ለ 1 ቢያሸንፍም ዋንጫውን እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

በጨዋታው ቅጣት የተጣለባቸው ተጫዋቾች መጠቀሙን ተከትሎ ውጤቱ እንደተሰረዘበት የኢትጵጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሳውቋል፡፡

30/06/2025
ዳኛ ሚሊዮን ደፋር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት  ም/ሰብሳቢ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ጋር  ድልድይ ሆነዉ የሚያገናኙ   የገለ...
30/06/2025

ዳኛ ሚሊዮን ደፋር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ጋር ድልድይ ሆነዉ የሚያገናኙ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ለመመስረት የተዘጋጀ ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል

ሆሳዕና ሰኔ 20 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ድልድይ ሆነዉ የሚያገናኙ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ለመመስረት የተዘጋጀ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል።

የማህበረሰብ ደህንነት የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤቶች የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ላይ ያተኮረ ውጤታማ የፖሊስ አገልግሎት መስጠት እንዲችዉ ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ለፖሊስ በማማከር እና ፖሊስንና ህብረተሰቡ ድልድይ ሆነዉ በማገናኘት የሚሰሩ መሆናቸዉተነግሯል።

በጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ የወንጀል ለመከላከል ስራ በፖሊስ ብቻ ሊረጋገጥ ስለማይችል የህብረተሰቡ ተሳትፎ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለፀዋል።

በነባሩ ክልል የሰላም እንቅፋት እና የፀጥታ ስጋት የነበሩ ጉዳዮችን በጥናት ለይተን ክልላችንን የሰላም ተምሳሌት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማማ መሆን አለበት ብለን ወደ ተግባር ገብተናል ብለዋል።

አቶ ተመስገን ካሳ በመጨረሻም መላዉ መሀበረሰባችን ለአካባቢዉ ሰላም መረጋገጥ ከፖሊስ ጎን ሆኖ በመስራቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን በሀገር ደረጃ የሰላም ተምሳሌት ለመሰኘት አብቅቶናል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ባሰሙት ንግግር የክልሉ ፖሊስ በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ በክልሉ ህዝብ ተሳትፎ አጋዥ ከሆኑ የፀጥ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በክልሉ አንፃራዊ የሆነ ሰላም ማስፈን ተችሏል ብለዋል።
በመሆኑም ከህብረተሰቡ መካከል በፈቃደኝነት የተመረጡ ነዋሪዎችን ያካተተዉ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት አደረጃጀት መመስረት በፖሊስ ተቋም እየተመራ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ዉጤታማ የሆነ የወንጀል መከላከል ስራ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ህዝባችንን ከወንጀልስጋት በማላቀቅ ይበልጥ ሰላምን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ኮሚሽነር አብራህም ቲርካሶ የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት (ፓትሮል) አደረጃጀትን በተመለከተ ሪፖርት ከቅርበዋል።

በቀረበዉ ሰፊ ሪፖርትም በክልሉ ሰባቱ ዞኖችና ሶስቱ ልዩ ወረዳዎች የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት በመመስረት ህብረተሰቡን ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ በባለቤትነት የፖሊስ አጋዥ ኃይል ሆኖ መስራት የሚያስችለዉን የከኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ፅንሰ-ሃሳብን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል መሆኑን ተመላክቷል።

በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎ በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ምርጫ ተከናዉኗል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ የአማካሪ ምክርቤቱ ሰብሳቢ ከሀድያ ዞን የሀገር ሽማግሌ ዳኛ ሚሊዮን ደፋር ምክትል ሰብሳቢ እና የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ኑረዲን አምዳለ ፀሀፊ ሆነዉ እንዲሰሩ ጎባኤዉ መርጧቸዋል።

# #ሰላም!!
ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!

ዳኛ ሚሊዮን ደፋር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት  ም/ሰብሳቢ በመሆን ተመርጠዋል ።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ጋር  ድልድይ ሆነዉ...
27/06/2025

ዳኛ ሚሊዮን ደፋር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ በመሆን ተመርጠዋል ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ጋር ድልድይ ሆነዉ የሚያገናኙ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ለመመስረት የተዘጋጀ ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል

ሆሳዕና ሰኔ 20 ቀን 2017 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስን ከህብረተሰቡ ድልድይ ሆነዉ የሚያገናኙ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ለመመስረት የተዘጋጀ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል።

የማህበረሰብ ደህንነት የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤቶች የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ላይ ያተኮረ ውጤታማ የፖሊስ አገልግሎት መስጠት እንዲችዉ ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ለፖሊስ በማማከር እና ፖሊስንና ህብረተሰቡ ድልድይ ሆነዉ በማገናኘት የሚሰሩ መሆናቸዉተነግሯል።

በጉባኤዉ ላይ ተገኝተዉ ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ የወንጀል ለመከላከል ስራ በፖሊስ ብቻ ሊረጋገጥ ስለማይችል የህብረተሰቡ ተሳትፎ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ገለፀዋል።

በነባሩ ክልል የሰላም እንቅፋት እና የፀጥታ ስጋት የነበሩ ጉዳዮችን በጥናት ለይተን ክልላችንን የሰላም ተምሳሌት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማማ መሆን አለበት ብለን ወደ ተግባር ገብተናል ብለዋል።

አቶ ተመስገን ካሳ በመጨረሻም መላዉ መሀበረሰባችን ለአካባቢዉ ሰላም መረጋገጥ ከፖሊስ ጎን ሆኖ በመስራቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን በሀገር ደረጃ የሰላም ተምሳሌት ለመሰኘት አብቅቶናል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ባሰሙት ንግግር የክልሉ ፖሊስ በቅድመ ወንጀል መከላከሉ ስራ በክልሉ ህዝብ ተሳትፎ አጋዥ ከሆኑ የፀጥ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በክልሉ አንፃራዊ የሆነ ሰላም ማስፈን ተችሏል ብለዋል።
በመሆኑም ከህብረተሰቡ መካከል በፈቃደኝነት የተመረጡ ነዋሪዎችን ያካተተዉ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት አደረጃጀት መመስረት በፖሊስ ተቋም እየተመራ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ዉጤታማ የሆነ የወንጀል መከላከል ስራ ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ህዝባችንን ከወንጀልስጋት በማላቀቅ ይበልጥ ሰላምን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ኮሚሽነር አብራህም ቲርካሶ የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት (ፓትሮል) አደረጃጀትን በተመለከተ ሪፖርት ከቅርበዋል።

በቀረበዉ ሰፊ ሪፖርትም በክልሉ ሰባቱ ዞኖችና ሶስቱ ልዩ ወረዳዎች የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት በመመስረት ህብረተሰቡን ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ በባለቤትነት የፖሊስ አጋዥ ኃይል ሆኖ መስራት የሚያስችለዉን የከኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ፅንሰ-ሃሳብን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል መሆኑን ተመላክቷል።

በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎ በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ የገለልተኛ አማካሪ ምክርቤት ምርጫ ተከናዉኗል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ የአማካሪ ምክርቤቱ ሰብሳቢ ከሀድያ ዞን የሀገር ሽማግሌ ዳኛ ሚሊዮን ደፋር ምክትል ሰብሳቢ እና የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ኑረዲን አምዳለ ፀሀፊ ሆነዉ እንዲሰሩ ጎባኤዉ መርጧቸዋል።

# #ሰላም!!
ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!

ልብ ሰባሪ ሀዘን 😭😭ወ/ሮ ጌጤነሽ መኮሮ ጦኔ ነፍስሽ በሠላም ትረፍ
15/06/2025

ልብ ሰባሪ ሀዘን 😭😭
ወ/ሮ ጌጤነሽ መኮሮ ጦኔ ነፍስሽ በሠላም ትረፍ

05/06/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆያታ ከዛሬ ሰባት ዓመት እስከዛሬ የነበሩ ችግሮች፣ የታለፉ መሰናክሎች እና የተገኙ ስኬቶች ምንድናቸው ለሚለው የሰጡት ማ....

17/05/2025
በሁሉም እቅዶቻችን የህዝብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ላይ ትኩረት ተደርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) ሆሳዕና፣ሚያዚያ 23/2017፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በፓርቲና...
01/05/2025

በሁሉም እቅዶቻችን የህዝብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ላይ ትኩረት ተደርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )

ሆሳዕና፣ሚያዚያ 23/2017፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በፓርቲና በመንግስት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት አስመልክቶ ክልል አቀፍ የአመራር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው፤

በመድረኩ ወደ እለቱ አበይት የውይይት አጀንዳ ከመገባቱ በፊት ሰሞኑን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት እና በመኪና አደጋ ህይወታቸው በድንገት ላጡት ለአቶ አሊ ከድር መታሰቢያ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል።

በመድረኩ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ አቶሬ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በሁሉም እቅዶቻችን የህዝብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

በክልሉ በመንግስት እና በፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በየደረጃው ሲገመገም መቆየቱንም ጠቁመዋል።

በክልሉ መንግስት ለአጠቃላይ ስራዎች አፈጻጸም አቅም የሚሆን አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር መግባት ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማው ይህንን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አመላክተዋል።

ለመፈጸም የታቀዱ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ስርዓት መገንባት ተቀዳሚ ተግባር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በመንግስትም ሆነ በፓርቲ የሚከናወኑ ተግባራት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲቃኙ ስለመደረጉም ጠቁመዋል።

በሁሉም መስክ የተቋም ግንባታን ማጠናከር እንዲሁም የህግ ማዕቀፎች መሰረት በማድረግ አዋጆችን፣ደንቦችን እና መመሪያዎችን በመጠቀም ወደ ተግባር መገባቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንዲሁም በጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስጀመር ላይ ትኩረት መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የመንገድ፣የድልድይ፣የንጹህ መጠጥ ውሀ ፣የትምህርት፣የጤና እና ሌሎችንም የልማት ፕሮጀክቶችን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

አደረጃጀቶችን በአስተማማኝ ደረጃ በማድረስ በተሟላ መንገድ ወደ ተግባር ማስገባት እና አቅሞችን በመጠቀም በልማት ስራ ላይ ማዋል ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በሁሉም ዘርፍ በሚተገበሩ ስራዎች ሰዎችን መመዘን ተገቢ ስለመሆኑ ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ከህገወጥ አሰራሮች በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር መላቀቅ ስለመቻሉም መገምገም እንደሚገባ ተናግረዋል።

በየተቋማቱ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራርን መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር መገባቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

በፓርቲ ስራ ላይ አመለካከትን የማጥራት እንዲሁም የመፈጸም አቅምን ማጎልበት ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የአመራር አንድነት እና ውህደት በአመቱ ለመፈጸም ከታቀዱ ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው(ዶ/ር)  የሆሳዕና ከተማ ኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰብን በተመለከተ ለታዳሚው ማብራሪያ ሰጥተዋል።።።።።  30/06/2017 ዓ.ም ።...
09/03/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው(ዶ/ር) የሆሳዕና ከተማ ኮሪደር ልማት ገቢ ማሰባሰብን በተመለከተ ለታዳሚው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
።።።። 30/06/2017 ዓ.ም ።።።።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ ሆሳዕና ከተማ ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን እንዲሁም 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እና የተለያዩ እንግዶችን ለመቀበል እየተሰራ ያለውን ሥራ ለመደገፍ የከተማው ባለሀብቶች፣የሐይማኖት ተቋማት እንዲሁም እያንዳንዱ ማህበረሰብ ሀላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

በመቀጠልም ለባለሀብቶች፣ለሐይማኖት ተቋማት፣ለመንግስት እና ለግል ባንኮች እንዲሁም ከኮንትራክተሮች ለልማት ስራው የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው(ዶ/ር) አስተላልፈዋል።

ለሆሳዕና ከተማ 10 የመጀመሪያ ደረጃ ባለሀብቶች እያንዳንዳቸው 10ሚሊዮን ብር ለልማቱ ገቢ እንዲያደርጉ፣ንግድ ባንክ 10ሚሊዮን ብር፣ሌሎች ባንኮች እያንዳንዳቸው 5ሚሊዮን ብር፣ኢንሹራንሶች እያንዳንዳቸው 1ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሀዲያ ዞን የሚገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች እያንዳንዳቸው 2ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲያደርጉ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈው

ለሆሳዕና ከተማ ልማት 2ኛ ደረጃ 31 ባለሀብቶች እያንዳንዳቸው 5ሚሊዮን ብር የሐይማኖት ተቋማት ለእያንዳንዳቸው ከ5መቶ ሺህ እስከ 1ሚሊዮን ብር ድረስ ገቢ እንዲያደርጉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

አዘጋጅ ታከለ አጋፋሪ ኤድተር ኤልያስ ተሰማ

Address

Hosanna
Hossana

Telephone

+251916475976

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Hosanna ሀዲያ ሆሳዕና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share