
18/09/2025
እንዲታሰር ስትማፀኑ የነበራችሁ
ይሄው ታሰረ ምን ይሆን ትርፋችሁ!!!
ወንድሜ ብሩክ ካሜራ ፊት ሲቀርብ እንደሚያወራው አይደለም። ካሜራ ፊት ሲናገር ድምፁን ከፍ አድርጎ በስሜት ሲናገር በትክክለኛ ሕይወቱም የተረጋጋ አይመስለንም። እኔም እንደዛ ነው የሚመስለኝ የነበረው። ነገር ግን አንዴ ሐረር ለስራ አብረን ሄደን ያየሁት ግን ከማስበው የተለየ ነው። የተረጋጋ አብዝቶ የሚጸልይ ልታይ ልታይ የማይል ሰው ነው። ምናልባትም ይህ ወንድም እንዲታሰር ግፊት ያደረጋችሁት የልጅቷን እናት ሄዶ በመቅረፁ ሳይሆን ልክ ቀድሞ እኔ እንደምረዳው አይነት ሰው ስለመሰላችሁ በምክንያት እርካታን ለማግኘት ይሆናል።
ለማንኛውም ወንድማችን ሌሎች ወንድሞች ታስረው እንደተፈቱት እርሱም ይፈታል። በእራሳችሁ ልጅ ውድቀት እርካታ የሚሰማችሁ ግን ህሊና ይውቀሳችሁ።
#አሉ