Agaw - Ancient Engineers Lalibla Aksum builders

Agaw - Ancient Engineers Lalibla Aksum builders To introduce the Agaw past history in ethiopia

እባካቹሁ  አረብ ሀገር በጅዳ ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ድረሱልን ሼር🙏ከስር በፎቶ የምትመለከቷት ልጅ ያልፍልኛል ብላ በባህር አቋርጣ ሳውዲ ገባች 4 አመት እየሰራች እናቷን ታስታምም ነበር። ...
10/08/2025

እባካቹሁ አረብ ሀገር በጅዳ ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ድረሱልን ሼር🙏

ከስር በፎቶ የምትመለከቷት ልጅ ያልፍልኛል ብላ በባህር አቋርጣ ሳውዲ ገባች 4 አመት እየሰራች እናቷን ታስታምም ነበር።
በመሀል ግን እሷ ታመመች ህክምና እየተከታተለች ድንገት ደውላ ማረፏን ጓደኛዋ ነገረችን ሀዘኑን ለእናት ነገረቻት እናት በሀዘን በጣም ታማ ልጄን ፈልጋችሁ አምጡልኝ እያለች ቀን ሌሊት ታለቅሳለች እባካችሁ ደጋግ ኢትዮጵያኖች በአረብ ሀገር በጅዳ ያላቹሁ ይህንን ፎቶ ተመልክታቹሁ ተባበሩን አድራሻው የሆስፒታሉ የሚነግረን ጠፋ ጅዳ እንደሆነ ብቻ ነው የምናውቀው እርዱን አስከሬኗን ወደአገሯ ለማምጣት በእግዚአብሄር ስም ተባበሩን

የሟች ስም ብርቄ ደርበው ሀይሉ እናት ተሰቃየች ቤተሰቦቿ 0912605467 0911691231 ደውሉልን አደራ።

09/08/2025

መቃብር ቦታ ያልጠበቁትን ነገር ተመለከትኩ!!

እረፍት ሳገኝ አንዳንዴ ወደ መቃብር ስፍራ መሄድ ያስደስተኛል።ከራስ ጋር ጊዜ ለማሣለፍ፣የጠፋውን እና በግርግር ጭልጥ ያለው ማንነታችን ለመፈለግ እና ለማግኘት ቆንጆ ስፍራ ነው።

ሰው ሟች እንደሆነ ከተራዳ የህይወት ፍጻሜውን አውቋልና ለመኖር አይከብደውም።

አንድ ቀን ግን መቃብር ቦታ ያልጠበቁትን ነግር ተመለከትኩ፤ ያየሁት የመቃብር ላይ ፅሁፍ ስላስገረመኝ ይሄን ሰው በደንብ ማወቅ አለብኝ አልኩና ስሙን ይዤ ማህበራዊ ሚድያ ላይ መፈለግ ጀመርኩ ።

የህክምና ባለሙያ እንደሆነና በካንሰር በሽታ ለብዙ ወራቶች ተሰቃይቶ በ 30 ዓመቱ እንዳረፈ መረጃ አገኘሁ
መቃብሩ ላይ የተፃፈው እንዲህ ይላል "የእኔም ተራ ደረሰና መጣሁ" ይላል።

የተራ ጉዳይ እንጂ ሁላችንም ሞትን ቀማሽ ነን።ነገር ግን በብዙ የህይወት ውጣ ውረድ ስንዳክር ሞት እንዳለ ረስተን ድንገት ይመጣና ይዞን ላይመለስ ይሄዳል::

እዚህ ዓለም ላይ እየኖርን ሳይሆን እያለፍን ነው ፤ የምንሞተው መሞታችንን በምንረሳበት ቅጽበት ነው፤ እንድንሞት የሚያስታውሱን ነገሮች ሁሉ ህይወት ይሰጡናል።

የግሪክ አካባቢ ሰዎች መሞታቸው የሚያስታውሳቸውን ነገር በኪሳቸው ይዘው ይንቀሳቀሳሉ። "ሜሜንቶ ሞሪ " የሚል ቃል አላቸው ትርጓሜውም 'አስታውስ ትሞታለህ' የሚል ነው። ይሄን ፅሁፍ ሲመለከቱ ክፋት ያሰበ ከክፍቱ ይቆጠባል፤ ምቀኛው ፣ ዘራፊው፣ ነፍሰ ገዳዩ ከድርጊታቸው ይታቀባሉ።

ለዛም ነው በታላቁ መፅሐፍ "ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና" (መክ 7:2) ይለናል።

መሞታችንን ስናውቅ መኖር እንጀምራለን።

ተጻፈ በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን (ነሀሴ 1/2017 ዓ.ም)

09/08/2025

Big shout out to my newest top fans! Ayenew Ashenefi, Genanew Asferaw

የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት "የተራዘመ ጦርነት የተጨናገፈባቸው ጠላቶች" ሲል የገለጻቸው ኃይሎች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭትን ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው ሲል ከሰሰ።ምክር...
09/08/2025

የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት "የተራዘመ ጦርነት የተጨናገፈባቸው ጠላቶች" ሲል የገለጻቸው ኃይሎች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭትን ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው ሲል ከሰሰ።ምክር ቤቱ "ጠላቶች" ሲል የገለፃቸውን በስም ባይጠቅስም፣ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ "ጽንፈኞችን" በመጠቀም የሕዝብን እና የመንግሥትን አንድነት ለመከፋፈል ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።🇪🇹🇪🇹👉🏾👉🏾

የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት "የተራዘመ ጦርነት የተጨናገፈባቸው ጠላቶች" ሲል የገለጻቸው ኃይሎች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭትን ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው ሲል ከሰ....

https://shorturl.at/9eNqD
09/08/2025

https://shorturl.at/9eNqD

ዘንድሮ፣በቶሮንቶ ካናዳ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ናሆም፣የአፕል ኩባንያ ለተማሪዎች ያዘጋጀውን ውድድር በማሸነፍ አለም ዓቀፍ ዕዉቅና...

https://shorturl.at/ijzTA
09/08/2025

https://shorturl.at/ijzTA

ስምንት የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈው ኮከስ «ገጽታውን እየቀያየረ በሕዝብ ላይ የሚደርስ» ያለው «እልቂት» እንዲገታ ገዢውን ሥርዓት «በሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ሕዝባዊ ትግል መቀየር የ...

በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ያቄር ቀበሌ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ከግንቦት ወር በኋላ 22 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በቀጣይ ሳምንታት እርዳታ የማይደርስ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊ...
08/08/2025

በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ያቄር ቀበሌ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ከግንቦት ወር በኋላ 22 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በቀጣይ ሳምንታት እርዳታ የማይደርስ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊያልቁ እንደሚችሉ የቆላ ተምቤን ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ገብረ ሐዋርያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
🇪🇹🇪🇹👉🏾👉🏾

በትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ 22 ሰዎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ

ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው።ነገር ግን 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...
08/08/2025

ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው።

ነገር ግን 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...

#የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...

#ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...

#ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?

2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?

#የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።

#ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን የሚቀጥሉት አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።

ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡

#አንተም በተመሳሳይ መንገድ አልፈህ በአዲስ ህይወት ከፍ ብለህ መብረር ትችል ዘንድ ታላቅ ማንነትህን እንደገና ውለደው!!!

ህይወት ቀጣይነት ያለው የእድገት እና የለውጥ ጉዞ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣ እንደገና መጀመር፣ ያለፈውን ትተን አዲስ ጅምር መቀበል እንደሚያስፈልገን ሊሰማን ይችላል። ይህ የዳግም ልደት ሂደት እንደገና መጀመር ብቻ ሳይሆን እውነተኛውን ማንነታችንን ገልጦ ከሱ ጋር ተስማምቶ መኖር ነው። ይህን የለውጥ ጉዞ እንዴት መጀመር እና ታላቅ ማንነትን እንደገና መውለድ እንድትችል የሚከተሉትን አድርግ:-

1. ለውጥን ተቀበል

ለውጥ የማይቀር ነው፣ እናም ይህን እውነት በመቀበል፣ እራሳችንን ለአዳዲስ መልካም አጋጣሚዎች እና እድሎች እንከፍታለን። የተለመደውን እና ምቹ የሆነውን ነገር መተው ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የምር የምናድገው እና የምንለወጠው በእነዚያ የለውጥ ጊዜያት ነው። ለውጥን ስንቀበል ካለፈው ውሱንነት ተላቀን ማለቂያ ወደሌለው እምቅ አለም እንገባለን።

2. ውስጣዊ ጥንካሬህን ፈልገህ አግኝ

በዳግም መወለድ እና መለወጥ ጉዞ ውስጥ ውስጣዊ ጥንካሬን ማግኘት አስፈላጊ ነው። ውስጣዊ ጥንካሬ የሚመጣው ከውስጥ ነው እና በጣም ጨለማ በሆነው ጊዜ ውስጥ እንኳን ሊመራን የሚችል ኃይል ነው። ተስፋ መቁረጥ በሚሰማን ጊዜ እንድንቀጥል የሚነግረን ውስጣዊ ድምፅ እና ኋላ ስንቀር ወደ ፊት የሚገፋፋን ጉልበት።

3. ያለፈውን ተወው

ያለፈው ህይወትህ ምንም ይሁን ምን ዳግም መ

እነሆ ነሃሴ ገባ፤ ሻደይም ደረሰ። ሻደይ በዋናነት የሴት ልጆች የጨዋታ ወይም ቡረቃ ቀን አይደለም። ሻደይ የሴት ልጆች ነጻነት ቀን ብቻም አይደለም። ሻደይ ከሁሉም በላይ በተለይም በጥንታዊው ...
08/08/2025

እነሆ ነሃሴ ገባ፤ ሻደይም ደረሰ። ሻደይ በዋናነት የሴት ልጆች የጨዋታ ወይም ቡረቃ ቀን አይደለም። ሻደይ የሴት ልጆች ነጻነት ቀን ብቻም አይደለም። ሻደይ ከሁሉም በላይ በተለይም በጥንታዊው የአገው ህዝብ የወል ትውፊት ውስጥ የሴትነት ጸጋ የሚዘከርበት ድንቅ የምስጋና ቀን ነው።

መልካም ሻደይ
15 days left

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ከሁለት ዓመት በኋላ ዓለምን በመምራት የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደሚችል የሚተነብይ ጥናታዊ ጽሁፍ መውጣቱን ተከትሎ በቴክኖሎጂው ዓለም ማዕበል ፈጥሯል።      ...
07/08/2025

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ከሁለት ዓመት በኋላ ዓለምን በመምራት የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደሚችል የሚተነብይ ጥናታዊ ጽሁፍ መውጣቱን ተከትሎ በቴክኖሎጂው ዓለም ማዕበል ፈጥሯል። 👉🏽👉🏽

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የሰውን ልጅ ጥፋት እንደሚያስከትል ተተነበየ፤ እንዴት?

የአዲስ አበባ አዳዲስ መልኮች እና  የአዲስ አበባ ልጆች ዝማሬየደማቆች ህብር ቀለምሰላማዊት ውቢት ዓለምእንደስሟ ውብ ከተማምስጢራዊት ህብር ሸማአዲስ አበባ (2) የህያው የታሪክ ምስክርየአብሮ...
07/08/2025

የአዲስ አበባ አዳዲስ መልኮች እና የአዲስ አበባ ልጆች ዝማሬ

የደማቆች ህብር ቀለም
ሰላማዊት ውቢት ዓለም
እንደስሟ ውብ ከተማ
ምስጢራዊት ህብር ሸማ
አዲስ አበባ (2)

የህያው የታሪክ ምስክር
የአብሮነት ልዩ ምድር
የባህል ደሴት መዳረሻ
የጥቁር ህዝቦች መካሻ
የዲፕሎማሲ ማዕከላችን*
ዓለምአቀፍ መዲናችን*
እናት ነሽ ለዘመኑ ከተሞቻችን*
ጌጣችን ነሽ ዕንቁ ፈርጣችን*

አዲስ አበባ

መአዛዋ ልዩ አደስ
የአፍሪካ ግርማ ሞገስ
ስሟ መኩሪያ የሚያድስ
አበባዋ ዘወትር አዲስ

ባንድ ማደሪያ የጋራ ቤት
የብዝሃነት፣ የአብሮነት
የሰው ተኮር ልማት*
የሰላማዊ ህይወት*
የብልጽግና መሠረት*
ማማችን ነሽ የኢትዮጵያዊነት*
የአንድነት ውብ ቀለበት
ቃል ማሰሪያ ልዩ ድምቀት

ስመ ቃሉ ልዩ ፊደል
በወርቀዘብ የሚፈተል
ድንቅ ካባ ሽልማቱ
ሁሉ ልጇ ሁሉ ቤቱ

ሳንባችን ነች መተንፈሻ
የሁላችን መናገሻ
ከፈጣሪ የተሰጠች
አዲስ ሁሌ ቤታችን ነች

የማትቆም ተሻጋሪ
ኮከባችን ሁሌም አብሪ
የሁላችን ልዩ አንባ
አዲስ አዲስ አዲስ አባ

“ፍልሰታ” የሚለው ቃል ፈለሰ፣ ተሰደደ(ተገለጠ)፣መከፈት፣ መገለጥ፣ የመዝጊያ የመጋረጃ ከሚለው የግእዝ ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤ ይመለከታል፡፡ ...
07/08/2025

“ፍልሰታ” የሚለው ቃል ፈለሰ፣ ተሰደደ(ተገለጠ)፣መከፈት፣ መገለጥ፣ የመዝጊያ የመጋረጃ ከሚለው የግእዝ ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤ ይመለከታል፡፡ “ፍልሰት” የሚለው ቃል ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡ “ፍልሰታ ለማርያም” ሲባልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን (ማረጓን)፣ በኋላም ሥጋዋ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትውፊትና ቀኖና መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አጿማት መካከል አንደኛው ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሲሆን ከህጻናት ጀምሮ እስከ አረጋውያን የሚጾም ታላቅ ጾም ነው

እንደ እማሆይ አሀዱ ሳይባል ቅዳሴ ለመድረስ
እኛንም ያድለን እንዲህ አይነት መንፈስ ።
መልካም ፆም
©️ማርያም አዶተና ቲዩብ

Address

Awi
Injibara
INJIBARA,6040

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agaw - Ancient Engineers Lalibla Aksum builders posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Agaw - Ancient Engineers Lalibla Aksum builders:

Share