Hawlt media_ሀውልት ሚዲያ

Hawlt media_ሀውልት ሚዲያ Page of media

"የግል ህልም የወል ህልምን ማጨናገፍ የለበትም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ****************"በትናንት ውስጥ ወረት እና እዳ በዛሬ ውስጥ እድል እና ፈተና በነገ ው...
31/10/2024

"የግል ህልም የወል ህልምን ማጨናገፍ የለበትም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************

"በትናንት ውስጥ ወረት እና እዳ በዛሬ ውስጥ እድል እና ፈተና በነገ ውስጥ ተስፋ እና ስጋት ስላለ ኢትዮጵያዊያን የጋራ እጣ ፈንታችንን በጋራ መወሰን አለብን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ አመራር አካላት በሰጡት ሥልጠና፡፡

የሚጋሩት የጋራ ህልም ያላቸው ህዝቦች ነጋቸውን በማይናድ ጠንካራ መሰረት ላይ ያኖራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአንድነት የሚያቆማቸው አካላዊ፣ ምናባዊ እና ሥርዓታዊ ውቅር አላቸው ብለዋል፡፡

ማንም ከመሬት ተነስቶ እንዳይዳፈረን ህልም ያነገብን፣ ህልምን የሰነቅን፣ ህልምን የምንናገር፣ የሚተገበር ተሻጋሪ ህልም ያለን ህዝቦች መሆን አለብን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የጋራ ህልም ጊዜን ተሻጋሪ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህልም ልዕልና መር ሲሆን ጊዜን ተሻጋሪ ለትውልድ የሚተርፍ ይሆናል ብለዋል፡፡

መነሻው በቀል እና የበላይነትን ማረጋገጥ የሆነ ሀሳብ ቅዠት እንጂ ህልም አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ እንደዚህ ዓይነቱ ስሁት ስሌት በጥላቻ ላይ ያተኮረ ባዶ ምኞት ስለሆነ መጨረሻው ጥፋት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

ህልም ግልጽና ቀጥተኛ፣ አሳታፊና አካታች፣ ቀጣይና አዳጊ እንዲሁም ተተግባሪ መሆን እንዳለትም ገልጸዋል፡፡

የወል ህልም፣ አዎንታዊ እና መልካም ገጽታ፣ የጋራ አቅጣጫ እና ዓለማ፣ ህብረት እና አንድነት፣ ፈጠራ እና ትጋት ሲኖረው በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ ይንጸባረቃልም ነው ያሉት፡፡

የህዝቦች ትብብር፣ የዜጎች ክብር፣ ሰብዓዊ ብልጸግና፣ ሀገራዊ ልዕልና የኢትዮጵያ ህልም መሰረታዊያን መናቸውን ጠቅሰው፤ ይህ እንዲሳካ ዜጎች በሰፈር እና በብሔር መከፋፈል የለባቸውም ብለዋል፡፡

በሕዝብ አገልጋይነት ህልማችንን ለማሳካት ለሀገር እድገት በመሥራት የብልጽግና ፊታውራሪ መሆን እንችላለን ሲሉም ነው ያወሱት፡፡

ወጣት ሀገር እና ህዝብ አለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጋራ ትርክት እና ራዕይ በመጋራት ከደም ባሻገር በላብ እና በሀሳብ የሚተሳሰር ወጣት መፍጠር መቻል አለብን ብለዋል፡፡

ትውልዱ ለመጪው ዘመን የተዘጋጀ፣ መጪውን ዘመን አሁን ላይ ምቹ አድርጎ የሠራ፣ ከቴክኖሎጂ የተዛመደ እና ከአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር አብሮ መጓዝ የሚችል ለማድረግ የወል ህልም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡

ወጣቶች የዲጂታሉ ዓለም ፈር ቀዳጆች የሰላም እና የእርቅ አምባሳደሮች መሆን እንደሚገባቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ሁሉም ሰው የግል ህልም እንዳለው ጠቅሰው፣ የግል ህልም የጋራ ህልምን የሚገዳደር መሆን የለበትም ብለዋል፡፡

የግል ህልም የጋራ ህልምን የሚያጨናግፍ ሳይሆን ለጋራ ህልም ስኬት ግብአት መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

በመሃመድ ፊጣሞ
Via: EBC

24/10/2024

የፋሲል ንግግር በሀገርኛ ቋንቋ ሲያምርበት❤️❤️❤️

አዲሱ የመንግስት ስራተኞች ደመወዝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለፀው የገንዘብ ሚኒስትር ለዚህም የአፈፃፀም መመሪያ መዘጋጀቱን አስታወቀ! የገንዘብ ሚኒስትር እንደገለፀው የጥ...
19/10/2024

አዲሱ የመንግስት ስራተኞች ደመወዝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለፀው የገንዘብ ሚኒስትር ለዚህም የአፈፃፀም መመሪያ መዘጋጀቱን አስታወቀ!

የገንዘብ ሚኒስትር እንደገለፀው የጥቅምት ወር የደመወዝ ክፍያ በአዲሱ በተሻሻለው የደመወዝ ስኬል መሰረት መሆን ይጀምራል ብሏል። ለዚህም በቂ ዝግጅት ከመደረጉ በላይ የአፈፃፀም መመሪያ መዘጋጀቱን አስታዉቋል።

ካፒታል ከዚህ ቀደም በተደረገዉ ማሻሻያ ላይ የመንግስት ሰራተኞች ያቀረብትን ቅሬታ አስመልክቶ እንደዘገበው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት: የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ከማፅደቁ አስቀድሞ ሰራተኞችን ማወያየት እንዳለበት እና በድጋሚ መታየት እንደሚኖርበት ተጠይቆ ነበር።እነዚሁ ሠራተኞች እንደገለፁት የደመወዝ ማሻሻያው አሁን ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ እንደተባለውም ከግምት ያላስገባና እንደጠበቁት እንዳልሆነ ማስረዳታቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር ደመወዝ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክርቤት በቀን 28 /12/ 2016 ዓ.ም. ያቀረበዉ ከሰሞኑ በካቢኔው መፅደቁን አስታዉቋል።ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እንዳስታወቁት " በአጠቃላይ ሪፎርሙ በህብረተሰቡ ላይ የተለየ ጫና አለማምጣቱን እና የተፈራው የዋጋ ንረት አለመድረሱን " የተናገሩት የካቢኔው የ 100 ቀን አፈፃፀም ግምገማ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ነዉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ካፒታል ማሻሻያው ተከትሎ በወቅቱ በሰራዉ ዘገባ የደሞዝ ጭማሪ መኖሩን መንግስት መናገሩን ተከትሎ በማግስቱ የሁሉም ነገር ዋጋ በሁለት እጥፍ ጨምሯል። በዚህም ሰራተኛዉም ሆነ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ምንም የተሰጣቸዉ ነገር ሳይኖርና ጭማሪ እጃቸዉ ሳይገባ የኑሮ ዉድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉም ሁኔታዉን በምሬት ገልፀዉለት እንደነበር ይታወሳል።
Via Capital

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ማን ናቸው?***********************በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር...
19/10/2024

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ማን ናቸው?
***********************

በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ማን ናቸው?

በሕገ-መንግስታዊነት፣ በሕግ የበላይነት፣ በዴሞክራሲ፣ ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ፣ በሃይማኖት ነጻነት እንዲሁም በአንፃራዊ ሕገ-መንግስታዊ ሕጎች ላይ ትኩረት አድርገው ምርምር የሠሩ የሕግ ምሁር ናቸው። በምርምሮቻቸው አፍሪካ ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው ሠርተዋል፡፡

በአዲስ አበባ፣ በማዕከላዊ አውሮፓ እንዲሁም በሃዋሳ እና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲዎች እስከ ድሕረ ምረቃ ባሉት ደረጃዎች አስተምረዋል።

የሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከማዕከላዊ አውሮፓ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን፣ የጁሪዲካል ሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪያቸውንም ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች እና በአንጻራዊ ሕግ ሠርተዋል፡፡

በበርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የሕግና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጽሑፎችን አሳትመዋል። በተጨማሪም በአማርኛ በሚታተሙ የሀገር ወስጥ ጋዜጦች ላይ የሕዝብ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ጽሑፎችን አሳትመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕግ ትምህርት ቤቱ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሕግ ጆርናል ዋና አዘጋጅ ሆነውም ሰርተዋል፡፡

በማዕከላዊ አውሮፓ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ሰመር ኮርስ የሕገ መንግሥት ትምሕርት ክፍል ተባባሪ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

በኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምሕርት ቤት የሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ማዕከል ተባባሪ መምህር እንዲሁም ተመራማሪ ሆነው ሠርተዋል፡፡

ከነሐሴ 2012 እስከ ጥቅምት 2014 ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ ከጥቅምት 2014 እስከ ዛሬ ድረስ የፍትሕ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

እንደ የምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የዳኝነት ጉባኤ (EAIAC) ባሉት የሕግ ፎርሞችና ኮንፈረንሶች ላይ በመሳተፍ ገንቢ እና ለውጥ የሚያመጡ ሀሳቦችን በመስጠት ይታወቃሉ፡፡

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በአካዳሚክ ሕይወታቸው ያዳበሯቸው ልምዶቻቸው በመንግሥት ሥራዎቻቸውም ተግባራዊ ያደረጉ ትጉህ አገልጋይ ናቸው፡፡ በለውጡ መንግሥት ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ፍትሕ ዘርፍ በማሻሻል ይጠቀሳሉ።

ዶክተር ጌዲዮን የምዕራባውያን ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለማጠልሸት በዘመቱበት ወቅት በቢቢሲ ሃርድ ቶክ ላይ ቀርበው መሬት ላይ ያለውን እውነታ በማሳየት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

ጌዲዮን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

በለሚ ታደሰ

የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?    | በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው በዛሬው ዕለት የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸ...
19/10/2024

የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?

| በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው በዛሬው ዕለት የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ማናቸው?

በ1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለዱት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ወዳጄነህ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።

በህዝብ ግንኙነትና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል።

በቅዱስ ዮሴፍ የወንዶች ትምህርት ቤት በእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህርነት የስራውን ዓለም አንድ ብለው የጀመሩት ወ/ሮ ሰላማዊት፤ በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን በመቀላቀል በጋዜጠኝነት አገልግለዋል።

ከሪፖርተርነት እስከ አዘጋጅነት በዘለቀው በዚሁ የኢቢሲ የጋዜጠኝነት ቆይታቸው በተለያዩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ዘገባዎችን ያቀርቡ ነበር።

ከዚያም በ2009 ዓ.ም ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬትን በመቀላቀል በጣቢያው የራሳቸውን አሻራ ስለማኖራቸው ይነገራል።

በሚዲያው ከከፍተኛ አዘጋጅነት እስከ ምክትል ዋና አዘጋጅነት በዘለቀው አገልግሎታቸው በተለይ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ የትንታኔ ዘገባዎችን መስራታቸው ተጠቃሽ ነው።

የቀድሞዋ ጋዜጠኛ በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በቆዩባቸው አሥር ገደማ ዓመታት በእቅድ የሚመሩ ጠንካራ የሥራ ሰው እንደነበሩ የቀድሞ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ።

በ2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ብልጽግናን በመወከል ተወዳድረው የከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባል በመሆን ተመርጠዋል።

ከዚያም በመስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ተሹመዋል።

በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ቆይታቸው የኢፌዴሪ መንግሥት ቃል አቀባይ በመሆን የተለያዩ መግለጫዎችን ለመገናኛ ብዙሃን እና ለህዝቡ ሲያደርሱ ነበር።

የተዋጣላቸው የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ስለመሆናቸው የሚነገርላቸው ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ውጤታማ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂዎችን በመቀመርም እውቅና የተቸራቸው ናቸው።

ላለፉት ሶስት ዓመታት በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታነት ሲያገለገሉ የቆዩት የቀድሞዋ ጋዜጠኛ፤ በዛሬው ዕለት ደግሞ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።

በናርዶስ አዳነ

Hello☎️ ስልክ ተደውሎልን ስልኩን  አንስተን  በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello'  ማለት ምን ማለት ነው ግን ? 'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ  የተወሰነ ሰው ስም ...
08/10/2024

Hello☎️
ስልክ ተደውሎልን ስልኩን አንስተን በተለምዶ 'ሄሎ' እንላለን። ግን 'Hello' ማለት ምን ማለት ነው ግን ?

'Hello' ሰላምታ ብቻ ሳይሆን የአንድ የተወሰነ ሰው ስም እንደሆነ ሲያውቁ ብዙዎችን ሊያስገርም ይችላል። 'Hello' የአሌክሳንደር ግርሃም ቤል እጮኛ Margaret Hello ስም ነበር።

የስልክ ፈልሳፊው ቤል በፈጠራው የመጀመሪያ ሙከራ ወቅት ''Hello' ን እንደ መጀመሪያው ቃል ተጠቅሟል።

ይህ ቀላል ንግግር እስከ ዛሬ ድረስ ስልኩን ስናነሳ እንደ ሰላምታ ጸንቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስልክ ጥሪዎች መደበኛ መክፈቻ ሆነ።

ታሪኩ ዘውዴ
ከካናዳ 🇨🇦

ካርቱም‼በአልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ዋና ከተማዋን ካርቱም በከፊል መቆጣጠሩ ተሠምቷል።በሀሚቲ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለወራት ይዞ የቆያትን ካርቱ ጥሎ ለመውጣት ጥቂት ኪሜ እንደቀረ...
08/10/2024

ካርቱም‼

በአልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ዋና ከተማዋን ካርቱም በከፊል መቆጣጠሩ ተሠምቷል።በሀሚቲ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለወራት ይዞ የቆያትን ካርቱ ጥሎ ለመውጣት ጥቂት ኪሜ እንደቀረ ተዘግቧል።አልቡርሃን በህዝብ ቅቡልነታቸው እየጨመረ ነው ተብሏል።

መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ተደረገ። መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥ...
08/10/2024

መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ተደረገ።
መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የነዳጅ ሪፎርም አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አማካሪ አህመድ ቱሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ የሪፎርም ሥራ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ጥሩ የሚባል ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል።

የሪፎርሙ ተግባራዊነት በዋናነት መንግሥት ላይ የነበረውን የዕዳ ጫና ያቃለለ፣ ኮንትሮባንድን መቆጣጠር ያስቻለ እና የነዳጅ ግብይትን ፈጣንና ዘመናዊ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ጥቅል ድጎማ ከ197 ቢሊየን ብር በላይ በመንግሥት ድጎማ መደረጉን የጠቆሙት አማካሪው፤ ለሁሉም የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርቶችም ከጥቅል ድጎማው በተጨማሪ ከ30 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሁኔታ ያገናዘበና ሀገር አቀፍ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ታሳቢ ያደረገ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በገበያ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ስትራተጂ ተነድፎ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

በስትራተጂው መሠረትም መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የተሟላ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት በነጭ ናፍጣ ላይ 80 በመቶ ድጎማ እንዲሁም በቤንዚን ላይ 75 በመቶ ድጎማ የሚደረግ ይሆናል፡፡
የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግም መንግሥት በዓመት እስከ 300 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ ከ35 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ ማድረጉንም ገልፀዋል።

የብዙኃን ትራንስፖርት ላይ የነበረው ድጎማ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል ሲሆን፤ መንግሥት ወደ ሕብረተሰቡ ሊሄድ የሚችለውን ጫና ለማቃለል ይሰራልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የድጎማ ሥርዓቱ የኢኮኖሚውን ወቅታዊ ሁኔታና የኅብረተሰቡን የመክፈል አቅም እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በገበያ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ያገናዘበ መሆኑንም አስረድተዋል።

በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር የ12ኛ ክፍል ውጤት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት 204 ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት...
08/10/2024

በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመማር የ12ኛ ክፍል ውጤት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት 204

ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች የሪሚዲያል መግቢያ ውጤት 192 ነው።

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?  የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ...
07/10/2024

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡

የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።

እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ወስደዋል።

በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።

አምባሳደር ታዬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል፣ የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኀላፊ፣ የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣ በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።

በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998 ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ኾነው ተሹመዋል።

በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ኾነው ሰርተዋል።

በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ኾነው አገልግለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ኾነውም ሰርተዋል።

አምባሳደር ታዬ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኾነው ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን አገልግለዋል።

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ላይ አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ የሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር ኾነው ተመርጠዋል።(አሚኮ)

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሆኑ።
07/10/2024

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሆኑ።

አዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን መፍረሳቸው ተሠምቷል በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒ...
07/10/2024

አዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ ቤቶችን መፍረሳቸው ተሠምቷል

በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ትናንት ምሽት የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተወሰኑ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ መሬት መሰንጠቁንም ዩኒቨርቲው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

በፈንታሌ ተራራ ላይ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ከሁለት ሳምንታት በላይ በተለያየ አጋጣሚ መከሰቱን ባለሞያዎች ገልጸዋል።

ትናንት መስከረም 26/2017 ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት ነበር።

"የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ ተገኝቶ መረጃ የመሰብሰብ እና ለማህበረሰቡ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሥራቱን ገልጿል።

የአካባቢው ነዋሪዎች የትናንቱ መንቀጥቀጥ ተወሰኑ ቤቶችን እንዳፈረሰ፣ መሬትን እንደሰነጠቀ እና በተለይ እንስሳት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገቡ ገልጸዋል::

የዩኒቨርሲቲው ጂኦሎጂስቶች ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ትናንት እሑድ ምሽት የተከሰተውና በአዲስ አበባ በነዋሪዎች ላይ መደናገጥ የፈጠረው የመሬት መንቀጥጠጥ ለ18 ሴኮንድ የቆየ እንደነበረ ባለሞያዎች መናገራቸውን አሐዱ ዘግቧል።

Address

Menaheria
Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawlt media_ሀውልት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hawlt media_ሀውልት ሚዲያ:

Share