12/04/2023
የሶማሊ - አሜሪካዊው ፎቶ በEthio 360 ፊልም
~ ~ ~
በሶማልያ የእርስ በእርስ ግጭት ወቅት Barkhad Abdi የሰባት ዓመት ህጻን ነበር:: በወቅቱ ከቤተሰቦቹ ጋር አባቱ የምወደሚኖርበት የመን ተሰደደ::
እድል ትከተለውና "ዲቪ" ደርሶት ወደአሜሪካ ያመራል:: አሜሪካ ግን አልጋ ሆና አልጠበቀችውም - ቀጋ እንጂ:: እናም ህልውናውን ለማስቀጠል ወንድሙ በከፈታት ትንሽዬ የሞባይል መሸጫ ሱቅ ውስጥ ስልኮችን መጠጋገን ይጀምራል:: ከጥገና ሰዓት ውጭ ያለው ጊዜውንሞ ታክሲ የመንዳት ሥራ ያከናውናል:: በዚህ ምክንያት ህይወት አሰልቺ ትሆንበታለች::
በአንድ እለት አንድ ወሬ ከጆሮው ይደርሳል:: "ሆሊውድ በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ፊልም የሚተውኑ ለመምረጥ እየመዘገበ ነው" የሚል:: የሚፈልጉት ተዋናይ ደግሞ መርከብ የሚጠልፍ የባህር ላይ ወንበዴ ሲሆን ሶማሌያዊ ነው:: Barkhad Abdi ለመመዝገብ ሲሄድ ግን ለአንድ ሰው 700 ሶማልያውያን አሰፍስፈው ያገኛል:: የመመረጥ እድሉ እጅግ ዝቅተኛ ቢሆንም ተስፋ ሳይቆርጥ ተመዘገበ:: . . .
ከቀናት በኋላ ተደውሎ ህልም የሚመስል ዜና ይነገረዋል:: "ተመርጠሃል!" የሚል የብስራት ዜና:: ቅድመ ክፍያም $65 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተከፈለው:: የሚሰራበት ፊልም ርዕስ "Captain Philips" ይሰኛል:: ፊልሙ ተሰርቶ ለዓለም ሲቀርብ የመረጡት ባለሙያዎች በጣም ትክክል እንደነበሩ አረጋገጠ:: ተመልካቾች ተደነቁ - ተደመሙ:: ዝናው በመላው ዓለም ናኘ::
ጭራሽ ባሳየው ምርጥ የትወና ብቃት የ"2014 British Film Academy Best Supporting Character" አሽናፊ ሆነ:: በወቅቱ ለOscarም ታጭቶ ነበር - ባያሸንፍም::
በCaptain Philips ባገኘው ዝናና እውቅናም Eye in the sky እና Good time የተሰኙ ፊልሞች ላይ የመተወን እድል አገኘ:: በሀብት ላይ ሀብት - በዝን ላይ ዝና . . . ቀጠለ::
በመጨረሻም ዛሬ የEthio 360 ፊልም ላይ በፎቶው ብቻ "የህዝባዊ እምቢተኝነት ማቀጣጠያ ቅመም" ሆኖ ተወነ::
Hanan Federalist