Kaba MultiMedia - ካባ መልቲ ሚዲያ

Kaba MultiMedia - ካባ መልቲ ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kaba MultiMedia - ካባ መልቲ ሚዲያ, Media/News Company, Jijiga.

የቅዱሳን ስዕላትን በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስታሰራጭ የነበረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ *** ቤተልሄም ሚሊዮን ሳህሉ ሠሞኑን ...
26/09/2025

የቅዱሳን ስዕላትን በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስታሰራጭ የነበረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
ቤተልሄም ሚሊዮን ሳህሉ ሠሞኑን የቅዱሳን ስዕላት በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨቷ ይታወቃል፡፡ ኃይማኖትን ማንቋሸሽ እና ማዋረድ ተገቢነት የሌለው እና በህግ የሚያስጠይቅ ህገ-ወጥ ተግባር በመሆኑ ፖሊስ ግለሰቧን በፈፀመችው ድርጊት መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ።  የአየር መንገዱ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን በአሜሪካ ዋሽንግ...
26/09/2025

የ2025 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆኑ።

የአየር መንገዱ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው።

ዋሽንግተን ዲሲ መስከረም 16/2018) ፤ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው የ2025 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የሚሰናዳ ነው። በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው።

አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት ተካሂዷል። እውቅና ከተሰጣቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ደግሞ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

2019: ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን( ቴዲ አፍሮ)፣ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሚስተር ማርክ ጌልፋንድ

2020: በኮቪድ-19 ምክንያት አልተካሄደም

2021: አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ድምፃዊ ኤኮንና አቶ በረከት ወልዱ

2022: አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ "እረኛዬ" የቴሌቪዥን ድራማ፣ አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እና ንግስት ሰናይ ልኬ

2023: የዲባባ ቤተሰብ፣ አቶ ግርማ ዋቄ፣ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄና አትሌት ስለሺ ስህን

2024: ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ አትሌት ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋዬ፣ እና ርብቃ ሀይሌ ።

ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፤ በስፖርቱ ዘርፍ የኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፕዮን ሜዳሊያዎች ባለቤት አትሌት መሰረት ደፋር፣ በቢዝነስ ዘርፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ ባለሃብቱ ጆ ማሞ፣ በስነ ጥበብ ዘርፍ አንጋፋው ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ እና ታዋቂው የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያ ሰይፉ ፋንታሁን ተሸላሚዎች ይሆናሉ።

ዝግጅቱ በጊፍት ሪል ስቴት የአቅራቢ ስፖንሰርነት የሚታገዝ ሲሆን፤ በእለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ፤ ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል። በተጨማሪ የሙዚቃ ዝግጅት የሚቀርብ ይሆናል። ዝግጅቱ በሜሪላንድ ስቴት ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ሲቪክ ህንፃ ኦክቶበር 12 ምሽት በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በሚገኙበት ይከናወናል።

For more: Nova Connections, Email: [email protected]; https://www.africanrun.com/impact

Via fast

የቀድሞ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ስለ ወደብ ጉዳይ-----------------------------------------------“ኤርትራ ሶስት ባህር ይዛ ከምትገነጠል ቢያንስ አሰብ የኢትዮጵያ እንዲሆ...
23/09/2025

የቀድሞ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ስለ ወደብ ጉዳይ
-----------------------------------------------

“ኤርትራ ሶስት ባህር ይዛ ከምትገነጠል ቢያንስ አሰብ የኢትዮጵያ እንዲሆን የአሜሪካ መንግስት ማስማማት እንደሚችል ለኢህአዴግ ወክለው ሲደራደሩ የነበሩት እነ መለስ ዜናዊና ስዩም መስፍን ሃሳብ ቢያቀርቡላቸውም ፤ እነ አቶ መልስ ግን አንፈግም የሚል መልስ ነው የሰጡት“
የቀድሞ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ

ግእዝ ሚዲያ

🇺🇬 ዩጋንዳ የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የወደፊት ዕጣ እየመራች ነው! 🌍ዩጋንዳ ዘላቂ ወደሆነ ትራንስፖርት ያላትን ሽግግር በሚያሳይ ታላቅ ክስተት ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች...
23/09/2025

🇺🇬 ዩጋንዳ የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የወደፊት ዕጣ እየመራች ነው! 🌍
ዩጋንዳ ዘላቂ ወደሆነ ትራንስፖርት ያላትን ሽግግር በሚያሳይ ታላቅ ክስተት ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ትርኢት 2025 (National E-Mobility Expo 2025) በማዘጋጀት ታሪክ እየሠራች ነው። የዚህ አብዮት ግንባር ቀደም መሪ ኪራ ሞተርስ (Kiira Motors) የተባለ የአገር ውስጥ ኩባንያ ሲሆን የካዩላ አውቶቡሶች (Kayoola buses) የሚባሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከማምረት በተጨማሪ አፍሪካ በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ መሪ መሆን እንደምትችልም እያረጋገጠ ነው። ከመላው አህጉር እና ከዓለም የተውጣጡ ልዑካንን የሳበው ይህ ትርኢት ዩጋንዳ ንፁህና ዘላቂ የወደፊት ሕይወትን በመገንባት ላይ ትኩረት ያደረገች የፈጠራ ማዕከል መሆኗን አረጋግጧል።

ይህ ተነሳሽነት በሺዎች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥ ስራዎችን ለመፍጠር እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመገንባት ያለመ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜም ሀገሪቱ ከውጭ በሚገቡ ነዳጆች ላይ ያላትን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሳል። ንፁህ አየርን እና ዘላቂ ልማትን በማስተዋወቅ የዩጋንዳ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ስትራቴጂ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና በራሳቸው መንገድ ኢንዱስትሪ ማልማት ለሚፈልጉ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ይሆናል። የትራንስፖርት የወደፊት ዕጣ ኤሌክትሪክ እና ዘመናዊ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ በአገር ውስጥ የተሰራ መሆኑን ኪራ ሞተርስ ያሳያል።

23/09/2025

የፓሪስ ከተማ በደማቅ ብርሃን ስትዋብ፣ የኳስ እግር አለም አይኑን ወደ ቲያትር ዱ ቻትሌት አቅጣጫ አድርጎ ነበር። እዚያም፣ የ28 ዓመቱ ፈረንሳዊ ኮከብ ኡስማን ደምቤሌ፣ የዓለማችንን ታላቅ የግል እውቅና፣ የባሎን ዶር ሽልማትን ለመቀበል ሲቆም፣ ልቡ በስሜት ተሞልቶ ነበር። የርሱ ስም፣ በታላቁ ሮናልዲኒሆ ሲጠራ፣ አዳራሹ በጩኸትና በጭብጨባ ደመቀ፤ በውጪም ርችቶች ሰማይን አበሩ።

ነገር ግን፣ የደምቤሌ እውነተኛ ድልና ስሜት የተገለጠው፣ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ባሉት ደቂቃዎች ውስጥ ነበር። በመድረኩ ላይ የእናቱ ገጽታ እንደታየ፣ የልጁ አይኖች በእንባ ተሞሉ፣ ድምፁም በስሜት ታፈነ። ይህ የማይጠፋ ታሪክ ነው፤ የእናትን ፍቅርና መስዋዕትነት የሚያንፀባርቅ።

“ማልቀስ አልፈለግኩም ነበር” ሲል ከዝግጅቱ በኋላ ለሮይተርስ ተናግሯል ደምቤሌ። “ነገር ግን ስለ ቤተሰቤ፣ ሁልጊዜ ከጎኔ ስለነበሩ ሰዎች ማውራት እንደጀመርኩ፣ እንባዬ መጣብኝ፤ መቆጣጠር አልቻልኩም።” ይህ ቃል፣ ከትልቅ የእግር ኳስ ኮከብ የሚመነጭ ሳይሆን፣ የእናቱን ውለታ ከተሸከመ ልጅ ልብ የወጣ ነበር።

ደምቤሌ ለብዙ ጊዜ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ያልተረጋጋ ተጫዋች በመባል ይታወቅ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2017 ባርሴሎናን በከፍተኛ ገንዘብ ሲቀላቀል ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውት ነበር። ነገር ግን እ.ኤ.አ. በ2023 ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን (PSG) ሲዘዋወር ሁሉም ነገር ተለወጠ። አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ፣ ግቦችን ከማስቆጠር በተጨማሪ የመከላከያ ስራውን ጭምር የሚሰራ የተሟላ አጥቂ እንዲሆን ረድተውታል።

ባለፈው የውድድር ዘመን፣ 35 ግቦችን አስቆጥሮ 14 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የPSGን የሊግ 1 ሻምፒዮናነት አስገኝቷል። ይሁን እንጂ፣ ለባሎን ዶር ሽልማት ብቁ ያደረገው፣ PSG የቻምፒየንስ ሊግን ዋንጫ ሲያነሳ ያሳየው አስደናቂ ብቃት ነበር። ደምቤሌ በፍፃሜው ጨዋታ ኢንተርን 5-0 ሲያሸንፉ፣ ለሁለት ጎሎች አመቻችቶ በማቀበል የቡድኑ ወሳኝ አካል ሆኖ አገልግሏል።

“ያጋጠመኝ ነገር ልዩ ነው፣ ከPSG ጋር የሆነውን ለመግለጽ ቃላት የለኝም” ሲል በመድረኩ ተናግሯል። “ትንሽ ውጥረት ይሰማኛል፣ ይህን ዋንጫ ማሸነፍ ቀላል አይደለም፣ ምን ይሄ ብቻ... በሮናልዲኒሆ፣ በእግር ኳስ አፈ ታሪክ መሸለሜ ልዩ ያደርገዋል።”

ልቡን የነካው የምስጋና ንግግሩ ግን ወደ ቤተሰቡ ሲመለስ ነበር። “እ.ኤ.አ. በ2023 እኔን ሊወስዱኝ የመጡትን [PSGን] ማመስገን እፈልጋለሁ። የማይታመን ቤተሰብ ነው። ፕሬዚዳንቱ ናስር (አል-ኬላፊ) እንደ አባቴ ናቸው። እንዲሁም እጅግ በጣም ጥሩ የነበሩትን ሰራተኞች እና አሰልጣኜን ማመስገን እፈልጋለሁ - እሳቸውም እንደ አባቴ ናቸው - እንዲሁም ሁሉንም የቡድን አጋሮቼን።”

“ሁሉንም ነገር አብረን አሸንፈናል። በጥሩም በከፉም ጊዜ ከጎኔ ቆማችኋል። ይህ የግል ሽልማት በጋራ ያገኘነው የቡድን ድል ነው” ሲል የቡድን መንፈሱን አጉልቶ አሳይቷል።

ኡስማን ደምቤሌ፣ በፈረንሳይ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳረፈበት ምሽት ነበር። ከእንባው በስተጀርባ የእናት ፍቅር፣ የትጋት መንገድ፣ የትብብር መንፈስ እና የእግር ኳስ ውበት የተደበቀበት ልዩ ጊዜ። ታሪኩ ብዙዎችን የሚያበረታታ፣ ስሜት ቀስቃሽና ዘላቂ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው!

ለዘ-ሐበሻ ስፖርት - ሊሊ ሞገስ።

 ወጣቱ የዩንቨርስቲ መምህር : ኢንጅነር እንዲሁም ቲክቶከር /ብሩክ ጫላ / ዛሬ ተሞሽሯል።ፈጣን መረጃዎችን በማቅረብና በጎ ስራዎች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣት በርካታ ሽልማትና ዕውቅና የ...
20/09/2025



ወጣቱ የዩንቨርስቲ መምህር : ኢንጅነር እንዲሁም ቲክቶከር /ብሩክ ጫላ / ዛሬ ተሞሽሯል።

ፈጣን መረጃዎችን በማቅረብና በጎ ስራዎች ላይ በመሳተፍ የሚታወቀው ወጣት በርካታ ሽልማትና ዕውቅና የተሰጠው ለበርካታ ወጣት አርአያ መሆን የሚችል ታታሪና ጠንካራ ወጣት ሲሆን ቀጣይ የትዳር ህይዎቱ የሰመረ እንዲሆን ካባ መልቲሚዲያ ይመኛል።

‎የዘፀአት ሪል ስቴት 1 አክሲዬን ማህበር ተቋቋመለህዝቡ እንባ መፍትሄ ያመጣል የሚል ግምት ተሰጥቶታል!‎‎ዘፀአት የለዉጥ ሪል ኢስቴት 1 አክሲዬን ማህበር  ካጋጠመዉ ችግር በመዉጣት በዛሬዉ ...
20/09/2025

‎የዘፀአት ሪል ስቴት 1 አክሲዬን ማህበር ተቋቋመ
ለህዝቡ እንባ መፍትሄ ያመጣል የሚል ግምት ተሰጥቶታል!

‎ዘፀአት የለዉጥ ሪል ኢስቴት 1 አክሲዬን ማህበር ካጋጠመዉ ችግር በመዉጣት በዛሬዉ ዕለት መስከረም 10/2018 ዓ/ም መስራች አባላት በተገኙበት በአዲስ መልክ የተቋቋመበትን እና ከሚመለከተው አካላት ፍቃድ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።


ከዚህም ጋር በተያያዘ በአዲስ በመደራጀት ዘፀአት የለዉጥ ሪል ኢስቴት 1 አክሲዬን ማህበር በሚል በአዲስ ተደራጅተው ወደስራ ገብተዋል። ይህ ማህበር በተለይ ለተጎዱና ንብረታቸውን ሸጠው ቅሪት በማፍራት ፈንታ የተነጠቁ ወጣቶችን ችግር ይፈታል ተብሎ ይታመናል።

‎በአዲስ መልክ አባላቱን በማደራጀት ምስረታዉን ካደረገ በኋላ በዛሬዉ ዕለት አዲስ አመራሮችን በመምረጥ ከአባላቱ ጋር ትዉዉቅ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ስለሚኖረዉ የስራ እንቅስቃሴ አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል።

‎በዕለቱ ከአባላቱ ስለማህበሩ ቀጣይነትና መተዳደሪያ ደንቦችን በተመለከተ በጥልቀት ዉይይትም አድርገዋል።

‎ዘፀአት ሪል ስቴት 1 አክሲዬን ማህበር በአራት ሺ አባላት የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ታስቦ ነው ምስረታዉን ያደረገዉ።

‎የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አካለወርቅ ጳውሎስ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ ካደረጉ በኋላ ከእዚህ በፊት ግለሰቦች ራሳቸውን ጥቅም አስቀድመው ሲያጭበረብሩንና ሲያንገላቱን ቆይተዋል ሿሿ የተሰራው ህዝብ ነው ብለዋል።

  የአሸናፊዎች አሸናፊጴጥሮስ ማስረሻ የ1.5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆኗል።
20/09/2025

የአሸናፊዎች አሸናፊ
ጴጥሮስ ማስረሻ የ1.5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆኗል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለተለያዩ የጦር መኮንኖች ሹመት ሰጡአዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽ...
20/09/2025

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለተለያዩ የጦር መኮንኖች ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የጦር መኮንኖችን ሹመዋል፦

በዚህም መሰረት በጄነራልነት ማዕረግ፦
1 ሌ/ጄኔራል አለምሸት ደግፌ
2 ሌ/ጄኔራል ደስታ አብቼ
3 ሌ/ጄኔራል ይመር መኮንን
4 ሌ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን

በሌ/ጄኔራል ማዕረግ፦
1 ሜ/ጄኔራል ከፍያለዉ አምዴ ተሰማ
2 ሜ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ

በሜ/ጄኔራል ማዕረግ፦
1 ብ/ጄኔራል ታደሰ አመሎ ሲኤሳ
2 ብ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ክቲላ
3 ብ/ጄኔራል ኃይሉ እንደሻዉ አቶምሳ
4 ብ/ጄኔራል ዋኘዉ አለሜ አያሌዉ
5 ብ/ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ ሙለታ
6 ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ረጋሳ አመንቴ
7 ብ/ጄኔራል ደረጀ መገርሳ እሰታ
8 ብ/ጄኔራል በርሄ ገ/መድህን ደመወዝ
9 ብ/ጄኔራል ያሲን ሙሃመድ ሲሳይ
10 ብ/ጄኔራል ዘዉዱ ሰጥአርጌ ደመቀ
11 ብ/ጄኔራል ሚልኬሳ ረጋሳ ኢተፋ
12 ብ/ጄኔራል መለስ መንግስቴ ንረይ
13 ብ/ጄኔራል ተሾመ አናጋዉ አየለ
14 ብ/ጄኔራል አማረ ባህታ በርሄ
15 ብ/ጄኔራል አበባዉ ሰኢድ ይመር
16 ብ/ጄኔራል ደስታ ተመስገን አራጋዉ
17 ብ/ጄኔራል ከማል ኤቢሶ

በብ/ጄኔራልነት ማዕረግ፦
1 ኮ/ል ግርማ ፌዬ ከበደ
2 ኮ/ል ደመቀ መንግስቱ ጽዱ
3 ኮ/ል ተመስገን አስማማው አስናቄ
4 ኮ/ል ሰጠኝ ሊክሳ ኒካ
5 ኮ/ል ጌትነት አዳነ ካሳ
6 ኮ/ል ዮሃንስ መኮንን እጄታ
7 ኮ/ል አባቡ ተሸመ ለገሰ
8 ኮ/ል መኮንን መንግስተ ተበጀ
9 ኮ/ል አሰፋ ደበሌ ነጋዎ
10 ኮ/ል አለሙ ቂጣታ ወረታ
11 ኮ/ል ሙላው በየነ አማኑ
12 ኮ/ል ደጀነ ፀጋዬ ተሻለ
13 ኮ/ል ቾምቤ ወርቁ እሬሶ
14 ኮ/ል አባተ አሰፋ ካሴ
15 ኮ/ል ተሾመ ባጫ ጎሹ
16 ኮ/ል አዲሱ ትርፌሳ በየነ
17 ኮ/ል ዩሃንስ ትኬሳ አያንሳ
18 ኮ/ል ዳኛቸው አያሌው እንግዳ
19 ኮ/ል ፍቃዱ ታደሰ ሰጠኝ
20 ኮ/ል አስናቀ አይተነው መንግስቴ
21 ኮ/ል የሺጥላ ተስፋዬ ደመቀ
22 ኮ/ል መልካሙ ቶማ በየነ
23 ኮ/ል ፈይሳ አየለ ገብረየስ
24 ኮ/ል ጀማል ከድር በዳሳ
25 ኮ/ል ቸርነት መንገሻ ገብሬ
26 ኮ/ል አዘነ ሽመልስ ታደሰ
27 ኮ/ል ጥላሁን ዱጋሳ ጌቱ
28 ኮ/ል ንጉሴ ለውጤ መንግስቱ
29 ኮ/ል ገነት ይማም ታደሰ
30 ኮ/ል ጥላሁን ደምሴ ይርሳው
31 ኮ/ል መሀመድ አህመድ መሀመድ
32 ኮ/ል መስፍን በየነ ኃይሌ
33 ኮ/ል ቡሩክ ሰይፉ ሰርበቶ
34 ኮ/ል መሰረት ጌታቸው የሱነህ
35 ኮ/ል ሁሴን መሃመድ አሕመድ
36 ኮ/ል ግርማ አየለ ጉርሙ
37 ኮ/ል ጣሂር ሳሌህ አሊ
38 ኮ/ል ቦጃ አጋ በዳኔ
39 ኮ/ል አካሉ ካሳ ቦኬ
40 ኮ/ል አዲሱ በድሩ መሃመድ
41 ኮ/ል ቢራራ አበበ ተክሉ
42 ኮ/ል ረሺድ ኢብራሂም አሊይ
43 ኮ/ል ደምሴው አንተነህ ደመላሽ

የፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሚስት "ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ" ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰማ  | የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ለጉብኝት ወ...
18/09/2025

የፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሚስት "ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ" ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰማ

| የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ለጉብኝት ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዊቱ ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የባለቤታቸውን ቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን "ጥፊ ሲቀምሱ" በካሜራ ዕይታ ውስጥ ከገቡ ወዲህ በርካታ የሴራ ተንታኞች "የማክሮን ሚስት ዓለም ያወቀውን የአገር መሪ በአደባባይ የሚደበድቡት ወንድ ቢሆኑ ነው ፤ ፊታቸውም የሚያሳብቀው ይሄንኑ ነው" በማለት ውንጀላ ማቅረብ መጀመራቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ እና ባለቤታቸው የስም ማጥፋት ክስ መስርተው ጉዳዩ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይሁንና ክሱ የተመሠረተው በአሜሪካ በመሆኑ ፤ በአገሪቱ ሕግ መሠረት በታዋቂ ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ተፈጽሟል የሚል ውንጀላ ሲቀርብ ከሳሽ ወገን ተከሳሹ "ሆን ብሎ ጉዳት ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን" ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ተከትሎም የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለቤታቸው ብሪጄት ማክሮን ፣ ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፎቶግራፍ እና ሳይንሳዊ ማስረጃ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰምቷል።

ከቢቢሲ ፌም አንደር ፋየር ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን ጠበቃ ቶም ክሌር ፣ ይህ የስም ማጥፋት ዘመቻ "በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበሳጭ" እና በፕሬዝዳንቱ ላይም ተጽዕኖ ያሳደረ ነው ብለው ቀዳማዊት እመቤቷ እርጉዝ ሳሉ እና ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ጨምሮ ሌሎች ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርበን በሐሰት የጠፋው ስማችንን ለማደስ ቆርጠን ተነስተናል ሲሉ ተናግረዋል።

በቃልኪዳን ይጥና

ኢትዮጵያውያኑ በአሜሪካ አዲስ ታሪክ ሰሩ !‎‎"አሜሪካ እናንተን ትፈልጋችኋለች !" /Simon Cowell /‎‎‎በምድሪቱ ቁጥር አንድ በሆነው American's Got Talent የ 2025 ዉ...
18/09/2025

ኢትዮጵያውያኑ በአሜሪካ አዲስ ታሪክ ሰሩ !

‎"አሜሪካ እናንተን ትፈልጋችኋለች !" /Simon Cowell /


‎በምድሪቱ ቁጥር አንድ በሆነው American's Got Talent የ 2025 ዉድድር ላይ ቀርበዉ ማጣርያዉን ግማሽ ፍፃሜውን ባሳዩት ድንቅ ብቃት ካላመኑበት ፊታቸዉ የማይፈታውን ዳኞችን ከመቀመጫቸው ቁጭ ብድግ ያደረጉት ኢትዮጵያዊያኑ ቶማስና ታምራት የተመረጡት ምርጦች ብቻ የሚያልፉበት semi final ላይ ምርጥ ብቃታቸውን በማሳየት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያው በምስራቅ አፍሪካ በእጣት የሚቆጠሩ የደረሱበት ታላቅ ጀብድ ፈፀሙ ።

‎በትላንትናው እለት የዉድድሩ የዩቲዩብ ገፅ ላይ በተለቀቀው ቪዲዮ ካለፉት ዙሮች በተለዬ በእሳት ቀለበት የታጀበ አስደናቂ ጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች ያሳዩት ቶማስና ታምራት በዳኞቹና በአዳራሹ በታደሙት ከአራት ሽህ በላይ ታዳሚዎች ታላቅ አድናቆት ተችሯቸዋል ።

‎በአንጋፋዉ ዳኛ Simon Cowell "ለዘንድሮው ዉድድር ድምቀት ከሆኑ ጥቂት ተወዳዳሪዎች መካከል መሆናቸውን በመግለፅ አሜሪካ ትፈልጋችኋለች ሲል ተደምጧል ። ሌሎችም ዳኞች ከዙር ዙር ያሳዩትን ለዉጥና ከፍታ ለመፃፍ በሚቸግር የአድናቆት መአት አዢጎድጉደዉታል ።
‎ኢትዮጵያውያኑ ቶማስና ታምራት በዘንድሮው የAmerican's Got Talent ለአሸናፊነት ግምት ከሚጠበቁ ጥቂት ባለተሰጥኦዎች መካከልም ሁነዋል ።


‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ


በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተጻፉ
16/09/2025

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተጻፉ

Address

Jijiga
1234

Telephone

+251909042930

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaba MultiMedia - ካባ መልቲ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share