29/01/2025
ተሸከርካሪ ላይ የሚፃፉ የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃላት ምንነትና ትርጉማቸው!
(V8, D-4D, GDI, SRS Airbag, 4WD, 2WD)
ተሽከርካሪ ላይ በአጭሩ ስለሚፃፉ ፅሁፎች አብዛኛው ሰው በቂ ግንዛቤ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት የሞተር አይነቶችን ለተሸከርካሪው ስያሜ ሲጠቀመት ይስተዋላል:: በዛሬው የአዉቶ ቅምሻ ዝግጅታችን የነዚህን ቃላት ትክክለኛ ትርጉም እናስቃናችሁአለን::
V8
ቪ ኤት 8 ሲሊንር ያለዉ እና ቅርፁ V የሆነ ሞተር ነዉ። V የሞተሩን ቅርፅ ማለትም የሲሊንደሮችን አቀማመጥ 8 ደግሞ የሲሊንደሮችን ብዛት ይወክላሉ (የሲሊንደሮችን አቀማመጥና ብዛት ከፎቶው ይመልከቱ!)
ሲሊንደሮቹ ሞተር ላይ በሁለት ረድፍ እኩል ብዛት ኑሯቸዉ (አራት አራት) ትይዩ ሆነው ይቀመጣሉ።
በተመሳሳይ V6 ኢንጅን 6 ሲሊንደሮች ያሉት ሲሆን አቀማመጣቸዉ ከ V8 ኢንጅን ጋር ተመሳሳይ ነዉ።
ስለዚህ V8 የሞተር አይነት እንጂ የመኪና መጠሪያ ስም (ብራንድ)
አይደለም::
D-4D
ዲ ፎር ዲ በተመሳሳይ የመኪና ብራንድ ስያሜ ሳይሆን የሞተር አይነት ነው::
ዲ ፎር ዲ የናፍጣ ሞተር ሲሆን D-4D የሚለው የእንግሊዝኛ १८ ۶۵ ۸۲۱۲۶- (Direct Injection 4 Cylinder
Common Rail Diesel Engine) የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡
ይህ ሞተር (ኢንጅን) አራት ሲሊንደሮች ያሉትና በሲሊንደሮች ውስጥ የገባው አየር ከታመቀ በኋላ ሰዓቱን ጠብቆ በእያንዳንዱ ሲሊንደር በቀጥታ ናፍጣ በመርጨት ኃይል ማምረት የሚችል የሞተር አይነት ነዉ::
GDI
ዘመናዊ የቤንዚል መኪኖች ላይ GDI የሚል ፅሁፍ አለ።
GDI ማለትም ጋዞሊን ዳይሬክት ኢንጀክሽን ማለት ሲሆን የነዳጅ አረጫጭ ስርዓት ነዉ። ይህን የነዳጅ አረጫጭ ዘዴ የሚጠቀሙት ዘመናዊ የቤንዚን መኪኖች ናቸዉ።
-በብዛት በቤንዚን ሞተር ነዳጅና አየር በካርቡሬተር አማካኝነት ተቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር የሚገባና በስፓርክ ፕለግ (ካንዴላ) አማካኝነት የሚቀጣጠል ሲሆን ይህ GDI ሞተር ግን ካርቡሬተር የለዉም። ነዳጅና አየር በአንድ ላይ ተቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር አይገባም::
እንደ ናፍጣ ሞተር መጀመሪያ አየር ወደ ሲሊንደር ከገባ እና ከታመቀ በኋላ ቤንዚን በጉም መልክ ወደ ሲሊንደር ይረጭና የመቀጣጠልና ሀይል የማምረት ስራ ይካሄዳል።
ጂ ዲ አይ ኢንጅን ነዳጅ የሚረጨዉ በከፍተኛ ግፊትና በቀጥታ በያንዳንዱ የሲሊንደር ኮምበስሽን ቻምበር ላይ ነዉ።
ይህም ሰዓቱን የጠበቀ የነዳጅ አረጫጭ እና የተመጠነ ነዳጅ እንዲረጭ ያደረገዉ ሲሆን ነዳጅ ቆጣቢ እንዲሆንም አድርጎታል። በካይ ጋዝ ልቀትንም እንዲቀንስ አስችሎታል።
SRS Airbag
ኤር ባግ መሪ እና ዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኝ የአየር ከረጢት ሲሆን ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ በአየር በመሞላት እና ተስፈንጥሮ በመዉጣት አሸከርካሪ እና ተሳፋሪ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ከባድ ጉዳት ይከላከላል።
SRS;- ሰፕለመንታሪ ሬስትሬንት ሲስተም ማለት ሲሆን ትርጉሙም ተጨማሪ ማገጃ ስርዓት ማለት ነዉ። ይህ የተባለበት ምክንያት ኤር ባግ ከደህንነት ቀበቶ በተጨማሪነት አደጋን ለመከላከል የተገጠመ በመሆኑ ነዉ።
4WD
4WD - ሲተነተን Four wheel drive (ፎር ዊል ድራይቭ) የሚል ትርጉም ይሰጣል::
ፎር ዊል ድራይቭ ተሸከርካሪዎች በምቹ አነዳድ ጊዜ በኋላ ጎማዎች እንቅስቃሴ ተሸከርካሪው የሚንቀሳቀስበት የፊት ጎማዎች በነፃ የሚሽከረከሩበት ስርዓት ያላቸው ሲሆን በአስቸጋሪ ወይም ኃይል በሚያስፈልግበት የአነዳድ ሁኔታ ኃይል ለአራቱም ጎማዎች እንዲደርስ በሚፈለግበት ጊዜ አሸከርካሪዉ የማርሽ እጀታዉን በማንቀሳቀስ የሞተር ኃይል ለሁሉም ጎማዎች እንዲደርስ የሚያስችልበት ስርዓት አላቸው።
2WD
2WD - የሚለው የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል Two wheel drive (ቱ ዊል ድራይቭ ) የሚል ትርጉም ይሰጣል::
በ ቱ ዊል ድራይቭ መኪኖች (Two wheel drive) ኃይል ወደ
ሁለቱ ጎማዎች ብቻ የሚደርስ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ጎማዎች በነፃ
በመሽከርከር አጠቃላይ መኪናዉ የሚንቀሳቀስበት ስርዓት አላቸው።
FWD እና RWD የተሰኙ የቱ ዊል ድራይቭ አይነቶች ደግሞ Front
wheel drive (ፍሮንት ዊል ድራይቭ) እና Rear wheel drive
(ሬር ዊል ድራይቭ) የሚል ትርጉም አላቸው::
ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Sami Automotive technology
Telegram:https://t.me/samiauto1
መኪናችን ላይ GPS ካስገጠምን በኋላ እንዴት ንብረታችንን መቆጣጠር እንችላለን?
መኪናዎት ላይ ጂፒኤስ በማስገጠም መኪናዎትን ስልኮ ላይ ያድርጉ። የመኪናዎትን ሞተር በስልኮ በመቆለፍ በተመሳሳይ ቁልፍ የሚደረግ የመኪና ስርቆትን ይከላከሉ።
የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ መኪናዎት ላይ ሲያስገጥሙ
- መኪናዎት የት እንዳለ በስልኮ መከታተል ይችላሉ።
· በመተግበሪያ (Application) እንዲሁም በኮምፒዮተር መጠቀም ይችላሉ። · የየቀኑን የጉዞ ታሪክ መዝግቦ ያስቀምጣል።
መኪናው የተጉዋዘዉን ኪሎ ሜትር ይመዘግባል።
- እርሶ ከፈቀዱት ክልል ከወጣ ያሳዉቆታል።
- የመኪናዎትን ሞተር በስልኮ መክፈትም ሆነ መቆለፍ ይችላሉ።
- መኪናዎትን ከስርቆት መከላከል ይችላሉ።
ይህንን የGPS GNSS ቴክኖሎጂን በመጠቀም ድርጅቶን ያዘምኑ ስራዎንም ያቅልሉ
ምንጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።
☎️አሁኑኑ ደውለው ያስገጥሙ።
🙏ስልኮቻችንን በተደጋጋሚ ተይዞዋል ካሎት እባኮን ደግመው ይደውሉ።
📲 0912072874
📲 0947329334
📲 0913917373
📲 0906015555
📲 0906065151 አዳማ
📲0948110505 ድሬዳዋ ቢሮ
📍 አድራሻ - መስቀል ፍላወር ፣ ምስራቅ በር ስጋ ቤት
መግዛት ከፈለጉ ለበለጠ መረጃ አሁኑኑ ይደውሉልን
📍 አድራሻ አዳማ 04 ኮንደሚኒየም
📍 አድራሻ ድሬዳዋ ሳቢያን እሸት አክባቢ አባይ ባንክ ያለበት ህንጻ