27/02/2026
ብልፅግና፡ የሰከነ ፖለቲካ እና የተግባር ምላሽ! ⚖️🗳️
በምርጫ ክርክር ወቅት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ላነሱዋቸው የተለያዩ ጥያቄዎችና ሂስዎች፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በሀቅና በማስረጃ የተደገፈ፣ የሰከነና ተስፋ ሰጪ ምላሽ ሰጥተዋል። ክርክሩ የዲሞክራሲያዊ ባህላችን መገለጫ ሲሆን፣ ብልፅግና ግን ከንግግር ባለፈ በተግባር የታዩ ስኬቶችንና ለወደፊት የተቀረጹ ግልጽ እቅዶችን በማቅረብ የበላይነቱን አሳይቷል። በከተማችን አዲስ አበባም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የልማት ስራዎች፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና የሰላም ግንባታ ጥረቶች የፓርቲያችን የማይናወጥ ቁርጠኝነት ማሳያ ናቸው።
ተፎካካሪዎች ለሚያነሱዋቸው ስጋቶችና ጥያቄዎች ምላሻችን ሁሌም "የህዝብ ተጠቃሚነት" ነው። እኛ የምንመራው በስሜት ሳይሆን በዕውቀት፣ በጥላቻ ሳይሆን በሕዝቦች አብሮነት ላይ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ብልፅግና ብቸኛው አማራጭ ብልፅግና ፓርቲ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠናል። የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስና ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በጋራ እንቆማለን!
ምርጫችን ለተግባር፣ ለልማትና ለሁለንተናዊ ብልፅግና ነው! ✅🇪🇹