Adab press

Adab press We will win

የእኔ ጥቅም ከሕዝብ ጥቅም  ይበልጣል የሚሉ ጥቅመኞች ! በፍ/ቤት የመንግስትን ሀብት የሚያስመልሱ  ጠንካራ ተቋማት መሪዎች  ላይ ለምን ጥቅሜ ተነካ የሚሉ ግለሰቦች  በሚዲያ ዘመቻ  የፍ/ቤት...
04/11/2025

የእኔ ጥቅም ከሕዝብ ጥቅም ይበልጣል የሚሉ ጥቅመኞች !

በፍ/ቤት የመንግስትን ሀብት የሚያስመልሱ ጠንካራ ተቋማት መሪዎች ላይ ለምን ጥቅሜ ተነካ የሚሉ ግለሰቦች በሚዲያ ዘመቻ የፍ/ቤት ውሳኔን እያጣጠሉ እየተመለከትን ነው፡ ፡

አንዳንድ ግለሰቦች ከለውጡ በፊት ከጥቀመኛ ባለስልጣኖች ጋር ተመሳጥረው የወስዱትን የመንግሥት ይዞታ በፍ/ቤት ለመንግስት እንዲያሰረክቡ ሲወሰንባቸው ቀድሞ የለመዱትን ሕገ ወጥነት ተግባር የማያስተናግድ የሥራ መሪ ሲያጋጥማቸው በማህበራዊ ሚዲያ ጥቅማቸው ሊያሰከብሩ ሲንቀሳቀሱ እያየን ነው፡ ፡

በተለይ አሁን ላይ የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም ይከበር ብለው የቆሙን የተቋም መሪዎች ማበረታት የሚጠበቅ ሆኖ ሳለ ጭራሽ ሙሰኛ ብለው ቢቻላቸው ለማሸማቀቅ ጥረት ሲያደርጉ ስንመለኮት የጉዳዩን አሳሳቢነት በግልፅ ያሳያል።

በተለይ የመንግስት ደጋፊ ነኝ የሚሉ ነገር ግን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅምን የሚያስከብሩ ጠንካራ ሐቀኛ መሪዎችን ስም በማጥፋት መልሰው መንግስትን የሚወጉ ግለሰቦች አንድ ሊበሉ ይገባል ።

እነዚህ ግለሰቦች ያልተረዱት ነገር ቢኖር መንግስት ከሚኮራባቸው ውጤቶች አንዱ የመንግሥት ይዞታዎችና ቤቶችን ለማስመለሰ የተሰራው ሥራ ነው፡ ፡

አንትነህ አብርሃም የተበለውም ግለሰብ
በፍ/ቤት ተከራክሮ ማሸነፍ ሰያቅተውና ከለውጥ በፊት በሕገወጥ መንገድ የወሰደው የመንግስት ቦታን ፍ/ቤት ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እንዲመለሰ ተወስኗል።

ክርክሩ የጀመረው በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ቦታውን ለፓርላማ አባላት መኖሪያ ፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያነት የሚጠቀምበት ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ በወረራ የያዙት የእነ አንተነህ አብርሃም እናት ወ/ሮ ሳራ ጀግሬ ቦታውን አስረክቡ ሲባሉ ከግለሰቦች በስጦታ ተሰጥቶኝ ነው አለቅም ማለታቸውን ተከትሎ ይዞታውን እንዲያስረክቡ በማለት ክስ ተመሰርቶባቸው ፍ/ቤት ለፌቤኮ ወስኗል።

በመቀጠልም የሳራ ወራሽ ነን የሚሉ ልጆች በ3 የተለያየ ጊዜ የመቃወም አቤቱታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መሰረት አቅርበዉ በሶስቱም ላይ ተወስኖባቸዋል።

አሁን ላይ ከአራቱ ተከራካሪዎች አንደኛው ልጅ አንተነህ አብርሀም ሰበር ድረስ ጉዳዩን ወስደውት በተቋሙ መልሶ ተሰጥቷቸው ለምርመራ ለ30/3/2018 ዓ.ም ተቀጥሯል።

አንተነህ አብርሀም ያለ አግባብ የያዘው መሬት መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቅና በእጁ ማስረጃ የሚበል ነገር ሰለሌለው የሰበር ውሳኔ የተለየ አይሆንም በሚል ግምት የተቋሙን መሪዎች ስም እያነሳ ስም ለማጥፋት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ሰምተናል።

የፌቤኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በያዙት ጠንካራ አቋም ሊኮሩ ይገባል ። እኛም በሕዝባዊ አቋማችሁና የግል ጥቅማችሁን ትታችሁ ሕገወጦችን ለመጋፈጥ በመወሰናችሁ አድንቀናል።

ከእውነታው ውጭ መረጃን ለማዛባት የሚደረጉ ጥረቶች የማይቋሙ ከሆነና ያለ መረጃ ግለሰብ ተኮር ስም ማጥፋቶች ከቀጠሉ ጉዳዩ በሕግ እንዲታይ ማድረግም ይገባል።

መንግስትም ያወጣውን የሚዲያ አጠቃቀም አዋጅ ሲጣስ ዝም ብሎ መመልከት የለበትም ።አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል።

Congratulations our Ethiopian community
01/06/2025

Congratulations our Ethiopian community

01/06/2025

EVE
Black Elites Magazine
Highlights

01/06/2025
01/06/2025
እስቲ መልስ ስጡኝ
01/06/2025

እስቲ መልስ ስጡኝ

31/05/2025

Well come to our page

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adab press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share