05/09/2025
(በያዕቆብ ጥላሁን_ጃክ)
ነሃሴ 30/2017 ዳግም የተፖሰተ!
እኔ'ስ ስንኳ በዚህች የዕውቀት አድማሴ ድሮ ሰይጣንን የሆኔ 'ሆረር አይነት፣ጥርሱ የረዘመ፣ፀጉሩን ያጨበሬሬ ያጎፌሬ፣ጥፍሮቹ ምናምን ረጃጅም ፣የዓይኖች ትልቅነት የሰማይ ስባሪ የሚያካክሉ አይነት፣ተኋላው ጭራ ምናምን ያለው እና ጽማም ምናምን ሳመሳስል ከርሚያለሁ😭የክሳራ ጊዜ😭'
ሌላው ደግሞ መኖሪያው 'አመድ ምናምን ያለበት፣ትላልቅ ወንዞች ውስጥ(ነሪ,ማኪ,አብነት,ኦምቤት,ሳላ,ፖሽት,ሱላብ,ኩልፎ,ገንዳይሶ😂)፣ምንጮች ውስጥ፣መቃብር ውስጥ፣ጭፈራ ቤት ምናምን፣ደም ውስጥ ምናምን፣ኦና ቤት ውስጥ(የይስ ቱፍ ቱፌ ጋይስ አርትካ😎) እና ጫካ በረሃ ውስጥ የምኖር ይመስለኝ ነበር😭....(እሱንም አለማወቅ ክሳራ ነው ኦንድም )!.....ሰይጣን ግን መኖሪያው በሁሉም ስፍራ ነው።ደግሞም ግዑዝ ሳይሆን ነው።መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል
👉“እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ ፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን #አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።”
— ማቴዎስ 16፥23
አየህ ጎበዝ በዚህ ክፍል ላይ እኮ ኢየሱስ ጰጥሮስን አይደለም ሰይጣን ያለው።የጰጥሮስ ሃሳብ ለካ ሰይጣን ሆኖ ኖሯልና😭.....
👉“እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው #አሳብ ካገባ በኋላ፥” ዮሐንስ 13፥2
✍️ስለዚህ በእያንዳንዳችን ቤት ሰይጣን አለ።ክፉ ሃሳብ ስናመነጭ ሰይጣን ነው።አንዲት የ20ብር ስኒ ስሰበር ተነስተን ሃምሳ ክፉ ቃል ክፉ ሃሳብ Rise የምናደርግ ከሆኔ ሰይጣኑን ከቤታችን እንገስፅ።ከምስትህ ጋር በሃሳብ ሳትስማማ ቀርተህ መንገጭላዋን ምናምን አቅጣጫውን አስተህ ላይ አራት ክሎ ያለውን ጠቅላይ ምኒስተሩን'ይሄ ማንግስት ዳሞ' ብለህ መውቀስ ከጀመርክ ቱማ ሰይጣን አለብህ።
✍️ክፉ ሓሳቦች በሙሉ ሰይጣን ናቸዉ።
✍️ሰይጣን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከ40ቀን ጦሙ በኋላ ያመጣለት ፈተና የ ጽሁፍ ሳይሆን oral question ነው።ይህ ማለት ክፉኛ የሃሳብ ፈተና።ክርስቶስም የበከለውን የሃሳብ ሙግት በተቀደሰው ቃሉ አጠራውና ህድ አንተ ሰይጣን አለው።(ሾካካ በለው ቱማ😎)
ስለዚህ በቢሮኣችን፣ በሚንሰራበት መስሪያ ቤት ፣በአገልግሎት መስኮቻችን፣በኑሮኣችን ውስጥ እና በማህበራዊ ኑሮኣችን ውስጥ ማንኛውም የተመረዙ ሃሳቦች፣ክፋት የሞሉ እይታዎች በሙሉ ከሰይጣን ናቸዉ።ከእውነት የራቀ በውሸት የተሞከሻሼ ከትርጉም ባዳ የሆኔ የሃሳብ መንጋ ሰይጣኖች ናቸዉ እግዚአብሔር ይገስፃቸው።ምስትህን በጥፍ ብለህ 'ሰይጣን እኮ አሳሰተኝ አትበል' አንተ ራስህ ሰይጣን ሆነህ ከሰይጣን ጋር ተባበርክ እንጅ😍...
✍️ይሁዳ ኢየሱስን ይሸጥ ዘንድ በልቡ እኮ ክፉ ሃሳብ ስላደረ እንጅ ስንት ዓመት ከክርስቶስ ጋር የኖሬ የሃዋርያቶች አባል ነበር'ኮ😎.....
👉“ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤”
— ሉቃስ 22፥3
እግዚአብሔር ክፉ ሃሳቦቻችንን ይገስፀው።