East Africa Media and Communication

East Africa Media and Communication በእዉነተኛ መረጃ ማንሰራራት!

መረጃ/ መዝናኛ / ዜና እና ማስታወቂያ
----------------------------------------------------
Official "East Africa Media C." page
(2)

ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነማንችስተር ዩናይት በብራይተን ተሸንፎ ከኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ውድድር ውጪ ሆኗል።በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ በኦልድትራፎርድ ...
11/01/2026

ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

ማንችስተር ዩናይት በብራይተን ተሸንፎ ከኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ውድድር ውጪ ሆኗል።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ በኦልድትራፎርድ የተጫወተው ዩናይትድ 2ለ1 ተሸንፏል።

ብሪያን ግሩዳ እና የቀድሞ የዩናይትድ ተጫዋች ዳኒ ዌልቤክ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ቤንያሚን ሼሽኮ ማስቆጠር ችሏል።

በጨዋታው በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ተቀይሮ የገባው የአካዳሚ ምሩቅ ሼ ሌሲ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል ሲል አዲስ ሚዲያ ዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ በኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ውጪ ሲሆን በ40 ዓመት ውስጥ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

 እንኳን ለ2018 የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" በሰላም አደረሳችሁ!!  ቢስት ባር ቤንቾች አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት የበኩር እህል በጋራ  የሚቀመስበ...
11/01/2026


እንኳን ለ2018 የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ "ቢስት ባር" በሰላም አደረሳችሁ!!

ቢስት ባር ቤንቾች አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት የበኩር እህል በጋራ የሚቀመስበት ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው ።

መልካም በዓል!
(ኢስት አፍሪካ ሚዲያ)

የቢጣ-ደካ መንገድ ስራ አሁን ያለበት ደረጃ  ምልከታ ተደረገ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን የቦንጋ ድስትሪክት የሚሰራው የቢጣ_ደካ መንገድ ፕሮጀክት  በአጭር ጊ...
11/01/2026

የቢጣ-ደካ መንገድ ስራ አሁን ያለበት ደረጃ ምልከታ ተደረገ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን የቦንጋ ድስትሪክት የሚሰራው የቢጣ_ደካ መንገድ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለማስመረቅ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።

በመንገድ ስራ ምልከታ ላይ የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ፣ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ፣ የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ሀይሌን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ አስተባባሪ አካላት እንዲሁም የዞን አመራሮች መገኘታቸዉ ተዘግቧል።

ከንቲባ  አዳነች አቤቤ በተገኙበት የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ተመሠረተበኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የፌዴራልና የክልል መጅሊስ አመራ...
11/01/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ተመሠረተ

በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የፌዴራልና የክልል መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአድዋ ሙዚየም ተመስርቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምሥረታ መርሐ-ግብሩ ለይ እንደተናገሩት፤ ወጣቱ ሃይማኖትዊ እሴቱን በመጠበቅ ለከተማዋና ለሀገር ልማት መሠራት ይኖርበታል ብለዋል።

መንግሥት የወጣቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ወጣቶች አዲስ አበባን ፅዱ እና ሳቢ ለማድረግ በሚሰራው ስራ እየተወጡ ያለውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው ፤ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥር የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል፣ ከምሥረታው አንሥቶ ከወጣቶች ጋር የተያያዙ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመበየንና የእስልምናን እሴቶችን ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ትልቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዚደንት ዑስታዝ ሀይደር ኸድር በበኩሉ፤ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቋቋመው ካውንስል ወጣቱ ስለ ሃይማኖቱ በቂ እውቀቱን እንዲያዳብርና ለሀገር ልማት የበኩሉን ኃላፊነት ከሌሎች የእምነት ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዚዳንት ወጣት መንሱር ከድር ን እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት አሚር ሻፊን አድርጎ ተመርጠዋል።

በምሥረታ መርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሱልጣን ሐጅ አማን ኤባን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ዑለማዎች፣ ኡስታዞች እና ወጣቶች ተገኝተዋል ሲል ጋዜጣ ፕላዝ ዘግቧል።

ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው  የደካ ዳሩ ሰላም መስጊድ ተመረቀ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ካፋ ዞን ደካ ከተማ ውስጥ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሙሉ ተሳትፎ ከ14...
11/01/2026

ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የደካ ዳሩ ሰላም መስጊድ ተመረቀ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ካፋ ዞን ደካ ከተማ ውስጥ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ሙሉ ተሳትፎ ከ140 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ግዙፉ የዳሩ ሰላም መስጊድ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

በ1,950 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ ዘመናዊ መስጊድ፣ ለከተማው ተጨማሪ ውበትና ቅርስ ከመሆኑም ባሻገር፣ የማህበረሰቡን የመተባበርና የአንድነት መንፈስ በተግባር ያሳየ ፕሮጀክት መሆኑ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በክብር እንግድነት የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ ኢትዮጵያ ያላት የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር ልምድ ልዩ የሚያደርጋት ሀብቷ ነው ሲሉ ገልጸዋል። መንግስት ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩል ዓይን እንደሚመለከትና የሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንደሚያደንቅ ጠቁመው፣ ህዝበ ሙስሊሙ የበኩሉን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት፣ የመስጊድ ቦታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

የደካ ከተማ ከንቲባ አቶ አድነው ኃይሌም መስጊዱ ለከተማው ውበት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፣ በግንባታው ሂደት ውስጥ አሻራቸውን ላሳረፉ ግለሰቦችና ተቋማት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፈትዋ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢና የምስራቅ አፍሪካ ኡለማዎች ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ደጄላን ከድር የመስጊዱን መመረቅ አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸዉን የደካ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ የገቡ ሲሆን በፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ሁለቱ መሪዎች በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም...
11/01/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ጂቡቲ የገቡ ሲሆን በፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሁለቱ መሪዎች በጆኦፖለቲካል ጉዳዮች፣ በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ብሎም የሁለትዮሽ ጉዳዮች በተለይም በንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና የልማት ሥራዎች ይወያያሉ ተብሏል::

ይኽም ለሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትስስር እና የጋራ ብልጽግና ያለዉን የወል ጽኑ አቋም የሚያመለክት ነው ተብሏል።

ከካፋ ዞን እስከ ቱርካና ሀይቅ ‎በታችኛው ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚመደበው የጎጀብ ወንዝ‎መነሻውን ከፋ ዞን ቢጣ ወረዳ በማድረግ ኦሮሚያንና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልን በማዋሰን ወደ ቁልቁል...
11/01/2026

ከካፋ ዞን እስከ ቱርካና ሀይቅ

‎በታችኛው ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚመደበው የጎጀብ ወንዝ
‎መነሻውን ከፋ ዞን ቢጣ ወረዳ በማድረግ ኦሮሚያንና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልን በማዋሰን ወደ ቁልቁል የነጉዳል።

‎ጎጀብ ወንዙ ለመስኖ አገለግሎት ልውል በሚችል መልኩ በረጅምና በሰፊው ተዘርግቷል። ‎ያም ሆኖ ግን በሚፈለግበት ደረጃ አገልግሎትን መስጠት አልቻለም። ቀጣይም የፌደራል መንግስት ልዩ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል:: ‎ወንዙ ቢሰራበት የቱርስት መዳረሻነት ልውል እንደሚችል ብዙ ማሳያዎች አሉት።

‎መነሻውን ከካፋ ዞን ያደረገው ታላቁ የጎጀብ ወንዝ በደቡብ ኦሞ ዞን አድርገው ወደኬንያ አቅንተው ቱርካና ሀይቅ ጋር ይቀላቀላል።

(ኢስት አፍሪካ ሚዲያ )

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ "ቢስት ባር " በደመቀ መልኩ መከበር ጀምሯል። ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በሚከበረው ቢስት ባር እንግዶች ወደ ሼይቤንች ወረዳ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።የሼይ ቤንች...
11/01/2026

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ "ቢስት ባር " በደመቀ መልኩ መከበር ጀምሯል።

ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በሚከበረው ቢስት ባር እንግዶች ወደ ሼይቤንች ወረዳ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

የሼይ ቤንች ወረዳና የሲዝ ከተማ ማህበረሰብ ከሲዝ ከተማ ወጣ ብለው እንግዶችን በባህላዊ ጭፈራ ተቀብለዋቸዋል።

ቢስት ባር ትናን በወጣቶች ዋዜማው የተከበረው በዛሬው ዕለት በሲዝ ከተማ በፓናል ውይይት የሚከበር ይሆናል ።

በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ የፌዴራል ፣የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የተከበሩ አቶ ፍቅሬ አማን በዚሁ የፓናል ውይይት ለመሳተፍ የተገኙ ሲሆን ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራው አቅንተዋል ሲል የቤ/ሸ/ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ቢስት ባር ቤንቾች አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት የበኩር እህል በጋራ የሚቀመስበት ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው ።

የሃላባ የዘመን መለወጫ "ሴራ" በድምቀት እየተከበረ ነውየሃላባ የዘመን መለወጫ "ሴራ" በዓል በባህላዊ የዘመን አቆጣጠር  ስርዓት የማህበረሰቡ ሀገር በቀል እውቀት ማሳያ ሲሆን በየዓመቱ ከታህ...
11/01/2026

የሃላባ የዘመን መለወጫ "ሴራ" በድምቀት እየተከበረ ነው

የሃላባ የዘመን መለወጫ "ሴራ" በዓል በባህላዊ የዘመን አቆጣጠር ስርዓት የማህበረሰቡ ሀገር በቀል እውቀት ማሳያ ሲሆን በየዓመቱ ከታህሳስ መጨረሻ እስከ ጥር ወር መጀመሪያ ባሉ ቀናት ውስጥ ይከበራል።

በሃላባ ጥንታዊ የዘመን አቆጣጠር ቀመር "መንገሳ" የዓመቱ የመጨረሻው ወር ሲሆን ይህ ወር የአሮጌው ዓመት ማብቂያ እና ወደ አዲሱ ዓመት መሽጋገሪያ ነው ።

የአካባቢው ተወላጆች በዚህ ወር አዲሱን ዓመት ለመቀበል አርሶ አደሩ በእርሻው፤ ነጋዴው በንግዱ ሁሉም በየተሠማራባት መስክ ለአዲስ ስኬት እራሳቸውን በስነ- ልቦና የሚያዘጋጁበት ወር ነው።

የሴራ በዓል በውስጡ በርካታ እሴቶችን ይዟል። በየዓመቱ በበዓሉ መዳረሻ እድሜያቸው የደረስ ታዳጊዎች ግርዛት በመፈፀም ወደ ወጣትነት የሚሻገሩበት እና ሃላፊነት የሚቀበሉበት ሥርዓት ይፈፅማሉ፡፡

በበዓሉ ወቅት አባቶች የተጣሉ ሰዎችን በማስታረቅ በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ የሚያደርጉበት ማህበራዊ ሃላፊነት ከበዓሉ መገለጫዎች መካከል ይገኛል።

የዘንድሮው የሃላባ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ "የሴራ" በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በሃላባ ቁልቶ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የሃላባ "ሴራ" ማህበረሰቡ በዘመናት ሂደት ያጎለበታቸው የእለት ተእለት የሕይወት መስተጋብር የሚመራበት ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ነው።

"ሴራ" ወይም (የባህላዊ የአስተዳደር ሕግ) በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በባህላዊ ፍልስፍናው የተለያዩ ጉዳዮች የሚመራበት ስርዓትን አበጅቷል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

“ኦገቴ ሴራ” የተሰኘ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት እና “ሚሻላ ሴራ” በመባል የሚታወቀው የተመረዳዳትና የመደጋገፍ ሥነ-ስርዓቶችም ተጠቃሽ የአካባቢው ባህሎች ናቸው፡፡

እነዚህ ባህላዊ ሕጎች ዘመናትን ተሻግረው ዛሬ ላይ የደረሱት በቃል እና በተግባር በመኖር በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠብቀው ነው።


#ሃላባ

አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀአፈርን ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁ...
11/01/2026

አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ

አፈርን ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ (ኢ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተጠናው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ ማዘጋጀት ላይ ነው።

ቴክኖሎጂው የተለመደውን ብሎኬት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአካባቢው የሚገኘውን አፈር ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ለሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ የግንባታ ወጪን በእጅጉ እንደሚቀንስም ተገልጿል ሲል ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል።

ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት ቀርቧል።

11/01/2026

የኢትዮጵያ ተፈጥሮ መበልፀግ ነው

ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች በአሜሪካ ፍሎሪዳ በድምቀት የተከናወነው 46ኛው የአለም አገር አቋራጭ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል ።የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከ...
11/01/2026

ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች

በአሜሪካ ፍሎሪዳ በድምቀት የተከናወነው 46ኛው የአለም አገር አቋራጭ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል ።

የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

ፈታኝ እና ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት ውድድር ኢትዮጵያ በመድረኩ ባስመዘገቻቸው አጠቃላይ ሰባት ሜዳሊያዎች ኬኒያን ተከትላ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

485 አትሌቶች ከተለያዩ 52 የአለም ሀገራት በተፎካከሩበት ውድድር ምንም እንኳን በወጣት ወንድ አንድ አትሌት ብቻ እና በሴቶች ወጣት 3 አትሌቶች ብቻ በቪዛ ምክንያት ማሰለፍ ባለመቻላችን የቡድን ውጤት ሊመዘገብልን ባይችልም በተሰለፋት ልጆቻችን ኢትዮጵያ በሶስት የወርቅ፣በሁለት የብር እና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎች ነው በኬኒያ ብቻ ተበልጣ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በአዋቂ ወንዶች እና ሴቶች 10 ኪ.ሜ በቡድን ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ በማስመዝገብ በመድረኩ ታሪክ ስትሰራ ፣ በአትሌት ማርታ አለማየው ወርቅ ፣በአዋቂ ወንዶች በአትሌት ሪሁ አረጋዊ እና በወጣት ሴቶች አትሌት ወሰኔ አሰፋ የብር ሜዳሊያ እና በድብልቅ ሪሌይ በቡድን የነሃስ በአዋቂ ሴቶች በአትሌት ሰናይት ጌታቸው የነሃስ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።

ሙሉ ቡድኑ እንዲመዘገብና ወደ ውድድር እንዲያቀና ለማድረግ ቢሞከርም ከታሰቡት ቋሚ 28 ተሰላፊዎች ያለቪዛ ችግር ማሰለፍ የቻልነው 14 ብቻ ሲሆን ይህም ከቋሚ ተሰላፊዎች 50% ያህሉን ብቻ ነው ማሰለፍ የቻልነው ።

ከዚህ አንጻር የ2026 አለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በሶስት ወርቅ በሁለት ብር በሁለት ነሐስ በሁለተኛ ደረጃ የተገኘው ውጤት ከፈተኛ ነው።

Address

Bonga
Kefa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Africa Media and Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to East Africa Media and Communication:

Share