Kaffa Regional state

Kaffa Regional state facebook

የአባት ሀገር ሩሲያ ፕሬዚዳንት ወደህንድ ሊያቀኑ ነዉ !በምዕራባዉያኑ እስር ማዘዣ የወጣባቸው የአባት ሀገር ሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚርፑቲን በዚህ ሳምንት ሀሙስና አርብ በህንድ ጉብኝት እንደሚ...
03/12/2025

የአባት ሀገር ሩሲያ ፕሬዚዳንት ወደህንድ ሊያቀኑ ነዉ !

በምዕራባዉያኑ እስር ማዘዣ የወጣባቸው የአባት ሀገር ሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር
ፑቲን በዚህ ሳምንት ሀሙስና አርብ በህንድ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተሰማ ።

ፑቲን የሁለትዮሽ ስትራቴጂካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን ለማጠናከር ሰፊ ዓላማ ይዘው ሐሙስ ኒው ዴልሂ የሚደርሱ ሲሆን አርብ ዕለት ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ዋሽንግተን በህንድ እቃዎች ላይ ከፍተኛ 50 በመቶ ታሪፍ ከጣለችና የህንድ እና የአሜሪካ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ መበላሸቱን ተከትሎ እየተጠናከረ በሄደው የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት
ወቅት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ወደ ህንድ የሚያደርጉት ጉዞ አሜሪካን ክፉኛ ከማስቆጣት አልፎ በህንድ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ልትጥል እንደምትችል ተሰግቷል ።

ፑቲን በህንድ በሚኖራቸው ቆይታ
የመከላከያ ግንኙነቶችን ማጠናከር፣ የሁለትዮሽ ንግድን ከውጭ ጫና መከላከል ፣የህንድ ወደ ሩሲያ የሚላኩ ምርቶች በፋርማሲ፣ በግብርና፣ በምግብ ምርቶች እና በሸማቾች እቃዎች ዘርፎች የህንድ ሰራተኞች ወደ ሩሲያ እንዲንቀሳቀሱ ማመቻቸት እና ሌላኛው ደግሞ በሰፊው የመከላከያ ትብብር ማዕቀፍ ስር የሎጂስቲክስ ድጋፎች ዙርያ
ስምምነቶችን እንደሚፈርሙ ይጠበቃል ።

ጎን ለጎን በሉአቸው በሚደረጉ ዉይይቶችም የሁለትዮሽ የኃይል ትስስርን ለማጠናከር መንገዶችም እቅዶች ጎልተው እንደሚታዩ ይጠበቃል።

ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ አጠቃላይ ትኩረቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቅርብ የመከላከያ እና የደህንነት ትስስር የበለጠ ለማስፋት እንደሆነ ገልፀዋል ።

ከጉባኤው በፊት የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ሐሙስ ዕለት ህንድ ተጨማሪ የኤስ-400 ሚሳኤል ስርዓቶችን እና ሌሎች ወሳኝ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ከሩሲያ ለመግዛት ባላት እቅድ ላይ ያተኩራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቁሟል ።

ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ግንኙነቶችን እድገት እንደሚገመግሙ፣ የጋራ ጥቅም ጉዳዮችን እንደሚወያዩ እና በዲፓርትመንቶች እና በንግድ ስምምነቶች ላይ እንደሚፈርሙ ይጠበቃል ሲሉ ሁለቱም መንግስታት ተናግረዋል።

ከጉባኤው በኋላ ፑቲን አዲሱን የሩሲያ የመንግስት ብሮድካስት ቻናል በህንድ ለማስጀመር ተዘጋጅተዋል፣ ከዚያም በፕሬዝዳንት ድሮፓዲ ሙርሙ ለክብር በሚዘጋጅ የመንግስት ድግስ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ፑቲን ለመጨረሻ ጊዜ ህንድን የጎበኙት በ2021 ሲሆን ሞዲ ባለፈው ዓመት በሞስኮ ነበር፣ እና ሁለቱ መሪዎች በመስከረም ወር በቻይና በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ወቅት ለአጭር ጊዜ ተገናኝተዋል። ሲሉ ያስነበቡት ኢንዲያን ታይምስ ዘጋርዲያን ናቸዉ ።
DireTube

አዲስ የትምህርት ደንብ: እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ! 🇪🇹የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣ...
20/11/2025

አዲስ የትምህርት ደንብ: እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ! 🇪🇹

የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።

ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።

ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።

የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።

ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day

የሚሉት ይገኙበታል።

Via Capital

01/11/2025

ተወዳጁ ድምጻዊ ምትኩ በቀለ (ቸውሲ) በአዲስ 3ተኛ አልበም እየመጠሁ ነው ብሏል።

አርቲስቱ በአባይ ቴሌቪዥን በ"መቅዲ Show" ፕሮግራም ጋር በነበረው ቆይታ በአሁኑ ወቅት አልበም ላይ አትኩሮት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

በቀጣይ በሚመጣው በዚህ አልበም ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን ለተቀረው የሀገሪቱ ክፍል በሚችላቸው ቋንቋዎች እንዲሁም በተለያዩ ስልተ ምቶች የተቃኙ ሥራዎችን ይዞ በመምጣት ለማስተዋወቅ ጥረት እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

‎💬 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ⚡️ t.me/doch_hd

ዶች HD

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ለተከበሩ አቶ ብርሃኑ አደሎ፣ጉዳዩ ያለምንም ወንጀልና ጥፋት በተርጫ ማረሚያ ታስሮ ያለውን ዶክተር አስራት ወልዴን ጉዳይ ይመለከታል።ዶክተሩ ባልሰሬው ...
23/09/2025

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ለተከበሩ አቶ ብርሃኑ አደሎ፣
ጉዳዩ ያለምንም ወንጀልና ጥፋት በተርጫ ማረሚያ ታስሮ ያለውን ዶክተር አስራት ወልዴን ጉዳይ ይመለከታል።

ዶክተሩ ባልሰሬው ስሪ በክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ተብዬው ኢብራሂም ተማም ያልተገባ ትዕዛዝ በዚህ ሰዓት ያለአግባብ እስር ላይ ይገኛል። ስቀጥል ምንም ህክምናም ሆነ ሌሎች አገልግልግሎቶችን እንዳያገኝ አሁን በዚህ ኢብራሂም ተማም ትዕዛዝ ከባድ ተጽዕኖ እየደረሰበተ ይገኛል።በመቀጠል ይህ አመራር ስልጣኑን ተገን በማድረግ የተከሳሹን ፋይል በየቀኑ እየበረበረ እንደፈለገ እያደረገ ስለሚገኝ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን በጥልቀትና በቅርበት በመከታተልና በማየት ያለወንጀሉ የታሰረውን ወንድማችንን እንድያስፈታልን እንጠይቃለን።

ነገሩ በቦንጋ ደም ባንክ ነው  የደምባንኩ ሃላፊ(አቶ ፍቃዱ ገሸሬ (የወላጋ ኦሮ)እና የደም ባንኩ ሹፈር (ወ/ሮ ስንቅነሽ ገምታ ጉድ ነው ሰውዬው በቀድሞ ሃላፍ ቦታ ውክልና ተቀብሎ መሥራት ከ...
21/09/2025

ነገሩ በቦንጋ ደም ባንክ ነው የደምባንኩ ሃላፊ(አቶ ፍቃዱ ገሸሬ (የወላጋ ኦሮ)እና የደም ባንኩ ሹፈር (ወ/ሮ ስንቅነሽ ገምታ ጉድ ነው ሰውዬው በቀድሞ ሃላፍ ቦታ ውክልና ተቀብሎ መሥራት ከጀመረ ዛሬ ድፍን 3ዓመት አልፎታል በዚህ ጊዛያት ውስጥ እንደአንድ የቢሮ ሃላፍ ሥራዎችን በዕውቀት በብስለት በመመሪያ መሠረት የማይመራ ለሰራው ስኬት ከመሮጥ ይልቅ አበል ማሳደድ ስልጠና መራራጥ ለሥልጠና ከዚህም የ15-20ቀን በ አ.አ አዝዞ ይዞ ወጥቶ ከዚያም ከሄደበት መቀበል የሰለጠነውን ስልጠና አንድም ቀን ለstaffዎቹ አስረድቶ አስገንዝቦ የማያውቅ ;የመምራት አቅሙ ዜሮ ሁኖ ለሥራ የሚሯሯጡ ምስክን ሴት ሰራተኞችን በጥቅማጥቅም በአጉል ዘረኝነት መጉዳት ማሸማቀቅ በተለይ ሲ/ር አብነት ሸዋታጠቅን አማራ ነች ብሎ በማሰብ
👉ከፋይናንስ ሰራተኞች ጋር በድብቅ የሚቀብራቸው እና አዟዙሮ የሚጠቀሙት የተቀበረ የተጠቀሙት ብዙ በጀት ስላሌ እና ያለአግባብ የሚበሉት አቀል ስላሌ የፋይናንስ ሠራተኞችን መንካት ማዘዝ አይችልም ከዚህም የተነሳ ለሥራው ብቁ ያልሆኑ ብሎም የማይታዘዙ ለሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለምሳሌ ሚሪንዳ,ውሃ,ኮሸሮ,ናፍጣ ,,,እነዚህን በአግባቡ ሰሪቶ እንድሰጡ ስታዘዙ መናቅ አልታዘዝም ማለት አታዘኝም ማለት ሥራዎችን ማስተጓጎል አስከዛሬ የቀጠለ አንተ ሌባ ብሎ ንቆ እስከመሳደብ የእሱን የመምራት ውድቀት የሚሳይ ነው
👉የአምቡላንስ ሹፈሯ እና የእሱ ጥምርታ ሹፈሯ እንዴ እርጎ ዝንብ ሁሉንም አዋቅ ታዋቅ ነኝ እንድትል የሥራ ግዴታዋን በአግባቡ አስጠንቅቆ ከመምራት ይልቅ በሹፈሯ መመራት ሁሉንም ሠራተኛ ሰድባ አስፈራርታ እሱንም አዋርዳ እንደፈለገች አላግጣ መኖሯ ሳያንስ የመንግስት በጀት በናፍጣ ሰበብ በስሟ እያዘዘ አብሮ መጠቀም ;
👉 አዲስ ጎማ እንድገዛ በማኔጅመንት ተወስኖ የተሰጠውን 260,000 ብር ሰኔ ወር 2017ዓ.ም ተወስኖ ወጭ የተደረገ ገንዘብ አዲስ ጎማ ሳይገዙ ተገዛ ብሎ በመሸወድ ከሹፈሯ(ወ/ሮ ስንቅነሽ ገምታ )ጋር በመሆን ገንዘቡን እንደሁልጊዜው የቀበሩ ሲሆን አዲስ ጎማ ሳይገጠም ተገጠመ ተብሎ አድዮ ወረዳ ለስራ በሄዱበት ከተገዛው በ1 ሣምንት ዕድሜ 2 ጎማ ፈንድቶ ማታ 3:30 ካለፌ በኃላ ቦንጋ በመግባታቸው ሠራተኞች ሴቶች በመሆናቸው ደደብና ሌባ ሃላፊው ;ሹፈሯ ና የፋይናንስ ሠራተኞች ገዛን ብሎ በበሉት ሠራተኞች መማረራቸው እና የደምባንኩ ሰነድ ያዥ የተገዛውን ጎማ ማየት አለብኝ አሮገውን ጎማ አስገብ ብላ በሚትጠየቅበት ሰዓት ሰነድ ያዧን መሳድብ ማንጓጠጥ ''አንቺ ማን ስለሆንሽ ነው የሚትጠይቅኝ ማለት አይደለምና አንቺ ፍቃዱ ገሸሬ እንኳን አይጠይቀኝም ብላ መሳደብ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመለከተው የክልል ጤና ቢሮ ;ፀሬ ሙስና ;የክልል ኦድት በአግባቡ ፈትሾ የእርምት እርምጃ እንድወስድ በአስቸኳይ
👉የአምቡላንስ ሹፈሯ ጉዶች :-
ከ4ወር በፊት ከአቶ ፍቃዱ ገሸሬ ጋር በመመሳጠር እንደሁልጊዜው ህገወጥ ስራዎችን በመስራቷ ህገወጥ መድሃኒት ከአዲስ አበባ ጭና በመምጣት ግቤ ጉምሩክ ኬላ ላይ በመያዝ ሁለቱም በእስር ቆይቶ ሹፈሯ ከባድ ወንጀል በመሆኑ እስከ አዲስአበባ አስርቤት በመላክ ከ2 ሳምንት በላይ መታሰሯ ይታወሳል ለደም ባንክ አገልግሎት የተሰጠውን አምቡላንስ መኪና ከቦንጋ ለተለያየ ስልጠና ስሄዱ ህገወጥ የቡና መነገጃ ስመለሱ ህገወጥ ከግል ፋርማስዎች እና ክሊኒክ ካላቸው ባለሃብቶች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ መድሃኒት ማመላላስ አልፎም ማታ ማታ ህገወጥ የመሬት የማዳበረያ ወደተለያዪ ወረዳዎች አጎራባች ዞኖች ጭምር አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።

ይቀጥላል !!

ፍትህ!! ፍትህ!!! ፍትህ!!!!ከማንኪራ ኮፊ( Mankira Coffee) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫበማይሆን ጥርጣሬ የግለሰቦችን ማንነትና መብት መንካት በህግም በፈጣሪም ያስጠይቃል።ዶ/ር...
18/09/2025

ፍትህ!! ፍትህ!!! ፍትህ!!!!
ከማንኪራ ኮፊ( Mankira Coffee) ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
በማይሆን ጥርጣሬ የግለሰቦችን ማንነትና መብት መንካት በህግም በፈጣሪም ያስጠይቃል።
ዶ/ር አስራት ወልዴ ፣ በካፋነቱና ለካፋ ህዝብ እድገትና ብልጽግና ተግቶና ቆርጦ በመፋለሙ ፣ በኢብራሂም ተማሚና በጀሌዎቹ ከባድና ብርቱ ቅጣት ከመድረሱም በላይ ምንም ባላደረገው "makira coffee " አንተ ነህ ፣በማለትና ባልፈጸመው ወንጀል በክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ኢብራሂም ተማሚ ትዕዛዝ በዚህ ሰዓት በእስር ላይ ይገኛል ። የሚገርመው ግን አንድ የክልልም ሆነ ሌላ ባለስልጣን በግል ጥላቻ እንደፈለገ ግለሰቦች እንዴት ማሳሰር ይችላል????? ደቡብ ምዕራብ ክልል፣ እንደኢብራሂም ተማሚ ባሉ ዋልጌዎች ስሙ መጥፋት የለበትም። ማንኪራ ኮፊ ፣ዶ/ር አስራት ወልዴ ነው ብላችሁ ከደመደማችሁ አሁን ዶ/ር አስራት ከታሰረ በኋላ እየጻፈ ያለው ማነው?? እውነቱና ሀቁ እዚህ ጋር ነው። አንድ የተማረ ፣ለአካባቢው እድገት ተሟጋች ዶክተር እንዴት በተደጋጋሚ በአንድ ተራ አመራር ትዕዛዝ በህገወጥ መንገድ እንዴት ይታሰራል?? ችግሮች ካሉ ተነጋግሮና ተጠያይቆ መፍታት እየተቻለ ፣በማንአለብኝነት ዶ/ር አስራት ወልዴን ያሰረ፣ያሳሰረና የተባበረ ከአሁኑኑ ከድርግቱ ልታቀብ ይገባል እያልን ፣በአስቸኳይ እንቁ ወንድማችንን እንድትፈቱልን በጥብቅ እንጠይቃለን።ይህ ባይሆን ክልሉም፣ሆነ ዞኑ( ካፋ ዞን) ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ እንደሆነ ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን። አቶ ኢብራሂም ተማሚ በፈጠረው ችግር ምክንያት ክልሉም ሆነ ዞናችን ችግር ውስጥ መግባት የለበትም። በተጨማሪም ለግል ጥቅሙ ብቻ የቆመውን ሆዳም ኢብራሂም ተማሚን ከክልሉ ጤና ቢሮ በአስቸካይ እንድታነሱ አጥብቀን እንጠይቃለን። መታወቅ ያለበት ዶክተር አስራት ወልዴ የታሰረው በካፋነቱ፣ለአካባቢው ልማትና ብልጽግና በርትቶ በመፋለሙ፣ለካፋ ህዝብ እድገት ነቀርሳ የሆኑትን ሌቦች በርትቶና ሳይሰላች በመፋለሙ እንጂ ምንም ወንጀል ሰርቶ እኖዳልሆነ ህዝቡ በደንብ እንድያውቅልን እንፈልጋለን።
በአጠቃላይ የክልልም ሆነ የዞን አመራሮች የኢብራሂም ተማምን የዘቀጠ አመለካከትና አስተሳሰብ ወደጎን በመተው ወደቀልባችሁ በመመለስ በህገወጥ መንገድና ባልሰራው ስራ የታሰረውን ዶ/ር አስራት ወልዴን በአፋጣኝ ፍቱልን!!!ፍቱልን!!!!ፍቱልንንንን!!!! ይህ ሆኖ ባይገኝ በክልሉም ሆነ በዞኑ ላይ ለሚፈጠረው ችግር ኢብራሂምና አመራሮቹ እንደሆኑ እንድታወቅል እንፈልጋለን። አሁንም አስረግጬ የሚነግራችህ Mankira.Coffee አስራት ወልዴ ሳይሆን እኔ ነኝ።ወንድ ከሆናችሁ እኔን እሰሩ/ያሳስር። ብቻ ውርደት ነው አንድ የክልል አመራርን የመሰለ ሰው እንዴት ባልተረጋገጠ መረጃ እንዴትግለሰቦችን ማሳሰር ይችላል???? አግባብነት አለው? ለክልልም ሆነ ለዞን ገጽታ መልካም ነውን? በጣም ያሳፍራል፣ ያሸማቅቃልም።በመጨረሻም በዶክተር አስራት ወልዴን አውቃችሁም፣ሆነ ሳታውቁ ከኢብራሂም በተጨማሪነት እጃችሁን ያስገባችሁ የክልልም ሆነ የዞን አመራሮችና ሌሎች ፣ለማሰርና ለማሳሰር እንደተረባረባችሁ ከዚህ ደቂቃ ጀምሮ ዶ/ሩን እንድትፈቱልን እያልን ይህ ባይሆነ ለእያንዳንዳችሁ ተኝተን እንደማናድርና ብርቱ ቅጣትና ውርደት እንደምጠብቃችሁ ከወዲሁ አጥብቀን እንጠይቃለን።
ፍትህ!!!ፍትህ!!!?ፍት፣ህ ለወንድማችን ዶ/ር አስራት ወልዴ!!!?!!!?

ዶ/ አስራት ወልዴ በዋስትናምይሁን በነፃ የማይለቀቅ ከሆኔ የመኪራ ማዕከላዊ ኮሚቴ መንገድ የመዝጋት እርማጃ የሚወስድ መሆኑን በይፋ ተወያይቶበታል ።

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናልየትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን...
13/09/2025

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

የትምህርት ሚኒስቴር ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፤ የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ10 ሰዓት ጀምሮ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል።

የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱ ይታወሳል።

በተፈጥሮ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 608 ሺህ 742 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ይታወቃል።

ቀሪዎቹ 473 ሺህ 914 ተማሪዎች ደግሞ በወረቀት ተፈትነዋል ሲል ፋና ሚዲያ ዘግቧል።

ፈተናው በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተቋቋሙ 216 የመፈተኛ ማዕከላት በበይነ መረብ በአራት ዙር እንዲሁም በወረቀት በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

የአካባቢያችን የትራንስፖርት፣ ታርፍና ትራፍክ ነገር!!!ከሰሞኑ በዚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ህግ ተላልፎ የተገኙ ተሽከርካሪና አሽከርካሪዎች ተቀጡ የሚል ከወደ ታርጫ ከሺሾእንዴ...አየውና በቀጣይ ...
03/09/2025

የአካባቢያችን የትራንስፖርት፣ ታርፍና ትራፍክ ነገር!!!
ከሰሞኑ በዚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ህግ ተላልፎ የተገኙ ተሽከርካሪና አሽከርካሪዎች ተቀጡ የሚል ከወደ ታርጫ ከሺሾእንዴ...አየውና በቀጣይ ለእነሱ የሠርግና ምላሽ ዓይነት የዘመን መለወጫና የመስቀል በዓል ልደርስ በዋዜማው ይህ መታየቱ ከሆነ ለጥቆማ ካልሆነም ለጥንቃቄ ይህንን ፃፍኩ።
ይሄ ጉዳይ ለያዥ ገናዥ ግራ አጋቢ ሆኖ የሰነበተ ነገር ነው። እኔ እንደ ተሣፋሪ ላውራ ስለሆንኩም። ከመነሻው አልከፍልም ቢል እዛው መናኸሪያ ውረድ ይባላል እንደ ማርያም ጠላት ማንም አይጭነውም የጉዞው ቀን ይቀይራል ፤ በበነጌውም ቢሆን ልብሱን ቀይሮ አንገቱን ደፍቶ ትንሽ እንደ ሰላይ ቢጤ መስሎ መምጣት አለበት ፤ መንገድ ጀምሮ ቢከራከርም ተስማምተህ የለ!? የተለመደ አይደል!? አቦ አትጨቃጨቅ በሠላም ያስገባን በል(ይ)! ከአድርባይ የገዛ ወገኑ ተሣፋሪ፣ ከረዳት ከሾፌር እግዚኦ ያጋግሉታል። በአጋጣሚ ቀንና ሰው ገጥሞት ህግ ቢያስከብር መብቱን ቢጠቀም በተለይ ቀሪ መንገድ ረዥም ከሆነ እሱን አያድርገኝ መብቱም ብሩም በቀረብኝ እርም ያስብላል። ያልጠፋ ሞተር ይጠፋል ፍሬን ይተዋል ራድያተር ይሞቃል ወዘተርፈ... ለሌላውን ሁሉ ስጋት ውስጥ በመክተቱ በትክክለኛው ሥራ ይፀፀታል። ምን ይደረግ ይሄኮ የታወቀ ነው ህዝቡ ለምዶት ለትራፊክ ፖሊስ ከመንገር ከባለሀብቱ መደመር ጀምሮ ዋጋ አልባ በብርድ በፀሐይ የመንግስትና ህዝብ ኃይል ላይ ጉዳት መድረስ ከጀመረ ሰነባበተ። ይህ የህግ ማስከበር የምር ከሆነ ህግ ህግ ነው የተፃፈ ነው አዝመራ የለውም ጠዋትና ማታ ክረምት በጋ የለውም እናንተም ስሩ ህዝቡም ከድባቴ ይውጣ ይንቃ ይታባበራችሁ ዘላቂነት ይኑረው። ማን ከማን ወገን እንደምቆም ጎራው ይለይ። ከመናኸሪያ እስከ መውጫ ከጉዞ እስከ መድረሻ የግድ ተመሣሣይና አንድ እንኳን ባይሆን የተቀራረበ የህግና የህግ አስከባሪ አቋም መኖር አለበት። ሃሳቤ ለሁለቱም ወገን ጭፍንና ጨፍላቂ አይደለም በሙያቸው በሥነ ምግባራቸው ምስጉን የሆኑ የህግ አስከባሪዎች እንዲሁም ከገንዘብ ይልቅ ለሰውነትና ስብዕና ክብርና ቅድሚያ የሚሰጡ ባለሀብትና ሠራተኞቻቸው እንዳሉ አልዘነጋሁም። ክብረት ይስጥልኝ! ሁሉም ቦታ እያወቅን እየተበላን ነው። ሀብታምም ወደ ሀብት ከፍታ ፤ ደሃውም ካለችውም ለሀብታም በግፍ እየደጎመ ወደ ቁልቁለት እየዳሸቀ ነው። ፈጣሪ ሳይመጣባችሁ ሀብታምና ህግ አስከባሪዎች የድርሻችሁን ተወጡ! ሁላችንም ከ7 ቀን በኋላ የሚሸት የሚተላ የሚበሰብስ ስጋ እንደተሸክምን እናስተውል ወገን እንተሳሰብ! መቼስ ለአንዳንዱ ባለሥልጣንና የግል መኪና አሽከርካሪዎች ካልሆነ በስተቀረ አዲስ ነገር ስላላወራው ሃሳቤን ከተጋራችሁ ተሣፋሪዎች እያራባችሁ ህግ ይከበር ወገን እንተሳሰብ በሉ! (በአንዳንድ የመናኸሪያ ''ወያላ'' ተራ አስከባሪ፣ ረዳትና ሾፌር የምደርስ ምንጭቅ፣ ስድብ፣ ማዋረድና ማኮስመን በወገናችሁ አይድረስ!!)

ከ242 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገነባ "ቃልአብ ባለ 5 ወለል የእንግዳ ማረፊያ" ህንፃ በቦንጋ ከተማ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ::"ቃልአብ ባለ 5 ወለል የእንግዳ ማረፊያ" ህንፃ የካፋ ዞን ዋና ...
31/08/2025

ከ242 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገነባ "ቃልአብ ባለ 5 ወለል የእንግዳ ማረፊያ" ህንፃ በቦንጋ ከተማ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ::

"ቃልአብ ባለ 5 ወለል የእንግዳ ማረፊያ" ህንፃ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደና ሌሎች የዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል::

ባለቤትነቱ የልማታዊ ባለሃብት አቶ ወንድሙ ወ/ሚካኤል ሲሆን ፕሮጀክቱ በወንድሙ ወ/ሚካኤል ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እንደሚገነባ ታውቋል::

ፕሮጀክቱን "ሳማድ ኢንጂነሪንግ" የሚባል ድርጅት በአማካሪነት አብሮ እንደሚሰራ ተጠቅሷል::
የወንድሙ ወ/ሚካኤል ጠቅላላ ሥራ ተቋራጩ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጥበብ ሰለሞን ስለአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ማብራሪያ ሰጥቷል::

እንደ ሥራ አስኪያጁ ማብራሪያ በውስጡ በርካታ አገልግሎቶችን ይዞ የሚገነባው ይህ ባለ 5 ወለል ህንፃ ሲጠናቀቅ በቦንጋ ከተማና በዙሪያው የሚስተዋለውን የሆቴልና የእንግዳ ማረፊያ ዕጥረቶችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተናግሯል::

ይሄው ባለ 5 ወለል ህንፃ በአጠቃላይ 909 ካሬሜትር የሚሸፍን ሆኖ 430 ካሬሜትሩ ህንፃው የሚያርፍበት መሆኑን ኢንጂነር ጥበብ ሰለሞን ጠቅሷል::

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 242 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን የሆቴል: የካፍቴሪያ: የመኝታ አገልግሎት: የመናፈሻ: ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም የመኪና ማቆሚያና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ሥራ አስኪያጁ አብራርቷል::

ፕሮጀከቱን ከህንፃ ዲዛይን እስከ ጥራት ያለው ሥራ ስታንዳርዱን ያሟላና ዘመናዊ እንዲሆን የማማከር ተግባር እንደሚወጡ የሳማድ ኢንጂነሪንግ ባለቤትና አማካሪ ኢንጂነር አዲስ ደምሴ ተናግሯል::

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በቦታው ተገኝቶ መሰረተ ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት እንደተናገሩት በዞኑና በከተማው የሚስተዋለውን የመዝናኛ ዕጥረት ከመቅረፍ አኳያ የህንፃው መገንባት እፎይታ የሚሰጥ ነው ብሏል::

ለዚህም ልማታዊ ባለሀብቱ አቶ ወንድሙ ወ/ሚካኤል ሁሌም ለሚያደርጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡት ዋና አስተዳዳሪው የዞኑ መንግስት እንዲሁም የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ለህንፃው መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍና ዕገዛ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል::

የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መረረጃ እንዳመለከተው በመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ: የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ነጉሤ: የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አተ ታከለ ታምሩ: የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመን ጨምሮ የዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ተገኝቷል::

በደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያጊዜ የአይን ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሎች ሊጀመር ነው ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵ...
29/08/2025

በደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያ
ጊዜ የአይን ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሎች ሊጀመር ነው ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚፈፀም የሶስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ የዓይን ጤና አገልግሎት ማደረጃትና ማስፋፊያና አዲስ ፕሮጀክት በይፋ ማስጀመሪያ እንዲሁም ትራኮማን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት የመጡ ስኬቶች የእውቅና መድረክ ተካሄዷል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራህም ተማም እንደገለፁት ከዚህ በፊት በዘመቻ መልክ ይሰጥ የነበረው የአይን ህክምና በክልሉ በሚዛን ሆስፒታል ፣ በቦንጋ ሆስፒታል እንዲሁም በቀጣይ በዚሁ ፕሮጀክት በተርጫ ሆስፒል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚጀምር ተናግረዋል።

አያይዘውም ህክምናው ኦርቢት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከተሰኘው ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሆነ የተናገሩት አቶ ኢብራህም በክልሉ የትራኮማ በሽታ ለማጥፋት በሸካ ዞን ለታዬው አፈጸጸም እውቅና ለመስጠት የታሰበ መድረክ እንደሆነም ተናግረዎል ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማው ዘውዴ በበኩላቸው የትራኮማ በሽታ ከክልላችን ለማጥፋት ተስፋ ሰጭ ውጤት መታየት መጀመሩን ተናግረው በተለይ የአይን ህክምና ለህጸናት ለልጆቻችን የወደፊት ህይወታቸው ተስፋሰጪ በመሆኑ የጋራ ትብብር እንደሚጠይቅ ገልጸዋል፡፡

የሸካ ዞን ያሳካውን የትራኮማ በሽታ መከላከል
በሌሎች ዞኖችም መስፋት እንደሚገባም ገልፀው በክልል ደረጃ በሦስት ዞኖች ላይ የአይን ህክምና ማስፋፊያ በመደረጉ የተሠማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

በመድረኩም የሸካ ዞን ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ድርጅት ጋር በመተባበር በዞኑ የሚገኙ ሶስት ወረዳዎችን ከትራኮማ ነፃ በማድረግ እንደሀገር ሁለተኛ ከክልሉ አደኛ በመሆኑ የውቅና ሽልማት ከድረጅቱ ተበርክቶላቸዋል።

እድሉን ያገኙ ዞኖች በበኩላቸው ከዚህ በፊት አገልግሎቱን ለማግኘት ጅማ ድረስ በመሄድ እና በዘመቻ መልክ ከመንግሥታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድረጅቶች ይሰጥ የነበረው አሆን ላይ እንደክልል ለሶስት ዞን እድሉ በመሰጠቱ ደስታቸውን ገልፀው አገልግሎቱን ለማስጀመር ከባለሞያ ቅጥር ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማው ዘውዴ ጨምሮ የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከጤና ተቋማት የመጡ የሚመለከታቸው የጤና ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የፕሮግራሙ ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

‎‎ በደቡብ ምህራብ ኢትዮጵያ ክልል ለመጀመሪያ
ጊዜ የአይን ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሎች ሊጀመር ነው ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚፈፀም የሶስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ የዓይን ጤና አገልግሎት ማደረጃትና ማስፋፊያና አዲስ ፕሮጀክት በይፋ ማስጀመሪያ እንዲሁም ትራኮማን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት የመጡ ስኬቶች የእውቅና መድረክ ተካሄዷል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራህም ተማም እንደገለፁት ከዚህ በፊት በዘመቻ መልክ ይሰጥ የነበረው የአይን ህክምና በክልሉ በሚዛን ሆስፒታል ፣ በቦንጋ ሆስፒታል እንዲሁም በቀጣይ በዚሁ ፕሮጀክት በተርጫ ሆስፒል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚጀምር ተናግረዋል።

አያይዘውም ህክምናው ኦርቢት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከተሰኘው ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሆነ

 #የካፋን ባህል ታሪክና እሴት ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ድርሻ  የሚጫወቱ አርቲስቶች:አርቲስት ሻምበል አስራት ሀይሌናአርቲስት ዋና ሳጅን አስራት ሀይሌ/ሞክሸዎቹ/
29/08/2025

#የካፋን ባህል ታሪክና እሴት ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ድርሻ የሚጫወቱ አርቲስቶች:
አርቲስት ሻምበል አስራት ሀይሌና
አርቲስት ዋና ሳጅን አስራት ሀይሌ/ሞክሸዎቹ/

27/08/2025

Address

Bonga
Kefa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaffa Regional state posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category