EOTC Amaro Woreda Betekihnet PR በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kele
  • EOTC Amaro Woreda Betekihnet PR በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት

EOTC Amaro Woreda Betekihnet PR በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት ይህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት ባለቤትነት በወረዳ ቤተ ክህነት እየተከናወኑ የሚገኙ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የሚዘግብ ገፅ ነው

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 22 - 24/2017 ዓ.ም በአማሮ ኬሌ ደ/ብ/ቅ/ጊ ቤ/ን ተዘጋጅቷል :: እርስዋም በጉቤኤው ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል::
17/10/2024

ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 22 - 24/2017 ዓ.ም በአማሮ ኬሌ ደ/ብ/ቅ/ጊ ቤ/ን ተዘጋጅቷል :: እርስዋም በጉቤኤው ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል::

የ2016 ዓ/ም የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአማሮ ኮሬ ዞን ባሉ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሮ ውሏል:: የዞኑ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት አማሮ ኬሌመስከረም 16/2015 ዓ...
27/09/2023

የ2016 ዓ/ም የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአማሮ ኮሬ ዞን ባሉ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከብሮ ውሏል::

የዞኑ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት

አማሮ ኬሌ
መስከረም 16/2015 ዓ/ም

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ መዝ 65:11 እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን:: አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና፤ የፍቅር፤ የበረከት፤ ንስሐ ገብተን በቅዱ...
12/09/2023

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ መዝ 65:11

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን::

አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና፤ የፍቅር፤ የበረከት፤ ንስሐ ገብተን በቅዱስ ቁርባን ከብረን በፍፁም መንፈሳዊነት ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖርበት የምህረት ዓመት ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት!
መስከረም 1/2016 ዓ/ም

የቤተ ክህነቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
አማሮ ኬሌ ኢትዮጵያ

የተተኪ ካህናትና የወንጌል አገልጋይ ኮርሰኞች ምረቃ ተካሄደ በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀ/ስብከት በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ 21 አጥቢያዎች በቅስና ክህነት ሊያገለግሉ የሚች...
06/09/2023

የተተኪ ካህናትና የወንጌል አገልጋይ ኮርሰኞች ምረቃ ተካሄደ

በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀ/ስብከት በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ 21 አጥቢያዎች በቅስና ክህነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ዲያቆናትን እና በስብከተ ወንጌል በገጠር አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ሊያገለግሉ የሚችሉ ኮርሰኞችን በአማሮ ኬሌ ደ/ብ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ን የክረምት ወራት አዳሪ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 29 ሰልጣኞች
ተመርቀዋል።
ተመራቂዎቹ ከቡንቲ፤ ከአልፋጮ፤ ከዬሮ፤ ከደርባ ማናና፤ ከትፋቴ፤ ከጉሙሬ፤ ከኬረዳ፤ ከሹኮ፤ ከጋሙሌ፤ ከቢቲ፤ ከቆቦ፤ ከጎልቤ፤ ከማረቴ፤ ከዛርገቴ፤ ከማዳይኔ፤ ከሀይሎ፤ ከሳጋኔ፤ ከጂጆላ፤ ከቆሬ፤ ከዳኖ ቡልቶ እና ከኬሌ የመጡ ሙሉ የዞኑን ቤተ ክህነት አጥቢያዎች ያካተተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በስልጠናው ይታይ የነበረው የተተኪ አገልጋይ ችግር ይቀረፋል ተብሎ እምነት ተጥሏል።

የህዝብ ግንኙነት ክፍል

ነሐሴ 29/2015
አማሮ ኬሌ

በአማሮ ኮሬ ዞን በጉሙሬ ቀበሌ ተሰርቶ የተጠናቀቀው የጉሙሬ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ከበረ:: በዞናችን ቤተ ክህነት በጉሙሬ ቀበሌ የኢየሱስ ቤ/ን ህንጸቱ ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ ነሐሴ ...
06/09/2023

በአማሮ ኮሬ ዞን በጉሙሬ ቀበሌ ተሰርቶ የተጠናቀቀው የጉሙሬ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ከበረ::

በዞናችን ቤተ ክህነት በጉሙሬ ቀበሌ የኢየሱስ ቤ/ን ህንጸቱ ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ ነሐሴ 27/2015 ዓ/ም መክበሩ ታውቋል::
ይህ ቤተ ክርስቲያን በጉሙሬና አካባቢው ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲቸገሩ የነበረው የሚያቀል መሆኑን ማወቅ ተችሏል::
በክብረ በዓሉ ላይ ከተለያዩ ቀበሌያት የመጡ ምዕመናን የታደሙ ሲሆን ቃለ ወንጌል ፤ ጸሎተ ቅዳሴ ፤ ዝማሬ እና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎት መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል::

የህዝብ ግንኙነት ክፍል!
ነሐሴ 29/2015 ዓ/ም
አማሮ ኬሌ

በኢ/ኦ/ቤ/ክ በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ በሹኮ፤ በዛርገቴ በደርባ ማናና አዲስ ህንጻ ቤ/ን ለመስራት መሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ:: በኢ/ኦ/ቤ/ክ በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስ...
04/09/2023

በኢ/ኦ/ቤ/ክ በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ በሹኮ፤ በዛርገቴ በደርባ ማናና አዲስ ህንጻ ቤ/ን ለመስራት መሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ::
በኢ/ኦ/ቤ/ክ በአማሮ ኮሬ ዞን ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ በሹኮ፤ በዛርገቴ በደርባ ማናና አዲስ ህንጻ ቤ/ን ለመስራት መሠረተ ድንጋይ በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀ/ስብከት ተልከው በመጡ ቆሞስ መልዐከ ሰላም አባ ዮሐንስ ምህረቱ እና በሌሎች አባቶች ጸሎተ ቡራኬ ተደርጎ በቀበሌያቱ አዲስ ህንጻ ቤ/ን ለማነጽ መሠረተ ድንጋይ ለማወቅ ተችሏል:: በዚህም መሠረት በሹኮ ባአታ ለማርያም፤ በዛርገቴ መስቀለ ክርስቶስ እና በደርባ ማናና ነባሩ የቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቤ/ን በአዲስ መልኩ እንደሚታነጽ ለማወቅ ተችሏል::

በመርሃ ግብሮቹም ላይ በየአካባቢው የነበሩ ህዝበ ምዕመናን በነቂስ ወጥተው መታደማቸው ለማወቅ ተችሏል::

የቤተ ክህነቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

አማሮ ኬሌ

ነሐሴ 29/2015 ዓም

ከ21 የገጠር አብያተክርስቲያናት ለተወጣጡ የተተኪ ሰባኪያንን ኮርስ ለጨረሱ 42 ዲያቆናት አገልግሎት የሚሆን 42 መጽሐፍ ቅዱስ እና ነጠላ እንለግሳቸው።***ይህኝ በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች...
02/09/2023

ከ21 የገጠር አብያተክርስቲያናት ለተወጣጡ የተተኪ ሰባኪያንን ኮርስ ለጨረሱ 42 ዲያቆናት አገልግሎት የሚሆን 42 መጽሐፍ ቅዱስ እና ነጠላ እንለግሳቸው።
***

ይህኝ በጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት በአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኙ የ21 የገጠር አጥቢያ አገልጋይ ዲያቆናት ናቸው።

አማሮ ወረዳ ባለፉት ስድስት ዓመታት በጦርነት ምክንያት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አብያተክርስቲያናቱ አገልግሎት ያቆሙበት በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ወረዳ ነው።

አሁን ግን በአከባቢው የታዬውን ትንሽዬ የሠላም አየር ምክንያት በማድረግ ለሐዋርያዊ አገልግሎት የሚሰማሩ ደቀመዛሙርትን በክረምት ወደ ሥልጠና ማዕከል በማስገባት ለማፍራት ተጥሯል።

ይህኝ 41 ዲያቆናት በአማረኛ እና ኮይረኛ ቋንቋ ሰባኪያን ይሆኑ ዘንድ የተተኪ ሰባኪያን የክረምት ኮርስ ለ2 ወር ጨርሰው ቀጣይ እሁድ ይመረቃሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ እና እና የአገልግሎት ነጠላ ግን የላቸውም።

እንግዲህ

40 መጽሀፍ ቅዱስ (40*500 ብር =20,000 ብር)
40 ነጠላ (40*500 ብር =20,000 ብር)

እንድትለገሱ በእግዚአብሔር ፍቅር እንጠይቃለን።
***
እነሆ ስጦታችሁን መቀበያ ህጋዊ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር

አማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት መንፈሳዊ አገልገሎት

1000547452066

***

ያስገባችሁትን የባንክ ስሊፕ በገጻችን የውስጥ መስመር ወይም በቴሌግራም እና ዋስአፕ ላኩልን።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

ዜና በዓል (የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት,12/12/2015ዓ/ም)በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን በዓመት ውስጥ ከሚከበሩት ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓላት አንዱ የሆነው የደብረ ታቦር ቡሄ በ...
18/08/2023

ዜና በዓል
(የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት,12/12/2015ዓ/ም)

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን በዓመት ውስጥ ከሚከበሩት ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓላት አንዱ የሆነው የደብረ ታቦር ቡሄ በዓል በአማሮ ኬሌ ደ/ቅ/ጊ/ቤ/ን በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
በደብሩ ሰንበት ት/ቤት በተዘጋጀው ክብረ በዓል በውዳሴ ማርያም ጸሎት ፤ በደብሩ ዘማርያንና በተጋባዥ ዘማርያን ዝማሬዎች ፤ በቃለ እግዚአብሔር፤ በድራማና ሥነ ጽሑፍ ክፍል በተዘጋጀ ግጥምና ድራማ ፤ ለዕለቱ በተዘጋጀው ጸበለ ጻድቅ ፤ በጧፍ እና ችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት በመጨረሻም በጸሎት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

የአማሮ ልዩ ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል
አማሮ ኬሌ

በአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት በቡንቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን የመጎብኘትና የማፅናናት ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ::በአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት በቡንቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤ...
09/08/2023

በአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት በቡንቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን የመጎብኘትና የማፅናናት ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ::

በአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት በቡንቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን የመጎብኘትና የማፅናናት ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ከነሐሴ 28-38/2015 ዓ/ም ተካሂዷል::

ባለፉት ሶስት ዓመታት በአካባቢው ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ተፈናቅለውና ተበታትነው የነበሩት ክርስቲያኖች አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም አግኝተው ባሉበት እነዚህን ክርስቲያኖች የማቀራረብ የመረጋጋትና ተጎጂዎችን የማጽናናት መርሃ ግብር ተካሂዷል::

በመርሃ ግብሩ ምዕመናን በእግዚአብሔር ቃል የማጽናናት ፤ ዳግም የማጠናከርና የእርቅ ስራዎችም የተሰራ ሲሆን ምዕመናንም ቤተክርስቲያን ይህንን ሰማያዊ ተግባሯን ደርሳ በማከናወኗ ትልቅ ደስታ ተሰምቷቸዋል::

በቀጣይም በአካባቢው ጠንካራ የሆነ ስራ ለመስራት እና ቤተ ክርስቲያንን ለማጠናከር አበክሮ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል::

የአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት ክፍል
አማሮ ኬሌ
ሰኔ 2/2015 ዓ/ም

የጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ዲላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው !ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ወደ ተመደቡበት የጌዴኦ አ...
29/07/2023

የጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ዲላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው !

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ወደ ተመደቡበት የጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ፤ ዲላ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ብፁዕነታቸው ሐምሌ 9 ቀን ከተሾሙ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ሲሆኑ በዛሬው ዕለት በልዩ ሁኔታ በከተማው ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት ተወካዮች ከወረዳው የተለያዩ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ተገኝተዋል::

የአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት

ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም
አማሮ ኬሌ

 ዓመታዊው የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ስላሴ ክብረ በዓል በአማሮ ልዩ ወረዳ ኬሬዳ ቅድስት ስላሴ ቤ/ን በድምቀት ተከበረ:: በበዓሉም ላይ ካህናት አባቶች፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ህዝበ ምዕ...
14/07/2023



ዓመታዊው የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ስላሴ ክብረ በዓል በአማሮ ልዩ ወረዳ ኬሬዳ ቅድስት ስላሴ ቤ/ን በድምቀት ተከበረ::
በበዓሉም ላይ ካህናት አባቶች፤ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ህዝበ ምዕመናን ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች በመገኘት የታደሙ ሲሆን ዕለቱን በማስመልከት ትምህርት፤ ዝማሬ እና ጸሎተ ቅዳሴ ተከናውኖ ታቦተ ህጉ ከመንበሩ ወጥቶ እጅግ ባማረ መልኩ ተከብሯል:: በበዓሉም 23 (ሃያ ሶስት) ነፍሳት የስላሴን ልጅነት አግኝተው ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ህብረት ተቀላቅለዋል::

የአማሮ ልዩ ወረዳ ቤተክህነት ህ/ግ ክፍል
ሐምሌ 7/2015 ዓ/ም
አማሮ ኬሌ

ዜና ጉባኤ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኙት የቡንቲ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል እና በአልፋጮ ቅ/ጊዮርጊስ አቢያተ ክርስቲያናት ከሰኔ 28 - ሐምሌ 1/2015 ዓ/ም የቆዬ ታላቅ...
08/07/2023

ዜና ጉባኤ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኙት የቡንቲ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል እና በአልፋጮ ቅ/ጊዮርጊስ አቢያተ ክርስቲያናት ከሰኔ 28 - ሐምሌ 1/2015 ዓ/ም የቆዬ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሂዷል:: በጉባኤውም በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ተራርቆ የነበረውን ምዕመን የማቀራረብ በእግዚአብሔር ቃልም የማፅናናት እንዲሁም የወንድማማች አንድነትን የማጠንከር መርሀ ግብር ተካሂዷል::

የአማሮ ወረዳ ቤ/ክ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ
ሐምሌ 1
አማሮ ኬሌ

Address

SNNPR
Kele

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EOTC Amaro Woreda Betekihnet PR በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአማሮ ወረዳ ቤተ ክህነት ህዝብ ግንኙነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share