29/06/2025
ገላዋ ልስልስ ያለ ነው:: ከሴቶች ይበልጥ ሴትነት የሰፈረበት፤ የግብረ ስጋ መቅደስ ያቀፍኩ መሰለኝ:: ትንፋሿ አንገቴ ላይ የፍትወት ነበልባል ያቀጣጥላል፡፡ ሁለታችንም ወጣት ነን፣ ሁለታችንም ሰክረናል፣ ሁለታችንም ምስጢራዊ ጭለማ ውስጥ ተደብቀናል፣ ሁለታችንም የምኞት ማእበል የሚያናውፀው ሙቀት ውስጥ ተጠቅልለናል፣ የሁለታችንም ደም ፈልቷል። እጄን ከትከሻዋ ወረድ ባደርግና የማባብላት አስመስዬ ወገቧን ጥብቅ አድርጌ ባቅፈው... እንደዚህ! — ደስ ማለቱ!, . . ቀስ አድርጌ በቸልታ እጄን ወደታች ሰደድ ባደርገውና ዳሌዋ ላይ ባሰፍረውስ?. . እንደዚህ! ከፑንቲዋ ጠርዝ ከእጄ ስር ታወቀኝ፡ ከገላዋ ሙቀት የባሰ የሙታንቲዋ ጠርዝ በምኞት ወጠረኝ፡፡ እኔ ሳላውቀው እጄ ሙታንቲዋ ውስጥ እየገባ አፌ አፏን ጎረሰው:: የት እንደሆንኩና ማን እንደሆንኩ ረሳሁ:: በመርሳቴ ደመና ላይ የባህራም ፈገግታ ብልጭ አለ።
እጄን ከሙታንታዋ እያወጣሁና አፌን ከአፏ እያላቀቅኩ፤ በሹክሹክታ
«ደግ አይደለም» አልኳት
«አዎን ደግ አይደለም» አለችኝ እሷም በሹክሹክታ
«ግን በጣም በጣም እፈልግሻለሁ፡፡ አንቺም ፈልገሽኛል፣
አይደለም?»
«አዎን›
«ምን ይሻላል?>>
«እኔ 'ንጃ»
«እኔ በበኩሌ ልተውሽ አልችልም»
ዝም
«ደሞ ልተውሽ አልፈልግም:: አንቺን መተው ራስን መኮነን ነው
ዝም
«ምን ይሻል ይመስልሻል?»
«እኔ 'ንጃ»
«ባስገድድሽስ?»
«ማስገደድ አያስፈልግህም»
«እስከ ዛሬ ድረስ ያንቺን ያህል ያማረችኝ ሴት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ደሞ እስከ ዛሬ ድረስ ሴት አግኝቼ ለሌላ ሰው ስል ትቼያት አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን እንዴት ልበልሽ»
«አሁን ሁለታችንም የማናምንበት ነገር ብናደርግ በኋላ ይቆጨናል፡፡ ግን እንድትለዪኝ አልፈልግም:: ምን ይሻላል?»
«እኔ 'ንጃ:: መብራቱን አብርተን የተረፈንን ካልቫዶ እየጠጣን ብናወራስ?»
በመብራቱ ስንጠጣ ስናወራ ምን ያህል እንደቆየን አላስታውስም፡፡ እንዲያውም ከዚያ በኋላ ምን እንዳደረግን ወይም ምን እንደተባባልን የማስታውስ አይመስለኝም፡፡ ብቻ፤ ከአንድ አመት በፊት እንዳየሁት ህልም ሆኖ ትዝ የሚለኝ አንድ ነገር አለ:: ጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን መጠጥ ከጨለጥነው በኋላ፤ ራሴን ደረቷ ላይ እያንተራስኩ
«ይሄ ጡት መያዣሽ ይቆረቁረኛል» አልኳት
«ቆይ ላውልቅልህ» ብላ አውልቃው እንደገና ራሴን ደረቷ ላይ አንተራሰችልኝ፡፡ «ጡትሽ እንደ ሞቃት ሰማይ ነው፤ ሰማዩ ላይ በፅጌረዳ ብርሀን የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች» አልኳት
«ውሸታም! መቼ አየኸው?» አለችኝ
«ማየት የለብኝም»
«አሁን ዝም ብለህ ተኛ» አለችኝ
ከዚያ ወዲያ ምንም አላስታውስም በነጋታው፣ ከሰአት በኋላ ወደ ስምንት ሰአት ላይ ስነቃ፣ ኒኮል ደረቴን ተንተርሳ ተኝታለች፡፡ አፌ ውስጥ የፋንድያ ጣእም ተሰማኝ፡፡ ኒኮልን ቀሰቀስኳት
«ደህና ነሽ?» አልኳት
«ደህና»
አፈርኩ
«ሳናውቅ የማንፈልገውን ነገር ስራን 'ንዴ?» አልኳት
«የለም»
«ጎሽ»
ከስብሀት ገብረእግዚአብሔር የወሰድኩት