
02/07/2025
ከድጋፍ ከተመለሱ የጤና መምሪያ ሰራተኞች ጋር ግምገማ ተደረገ፦
***
ሰኔ 25/2017 ዓ.ም/ከሚሴ/ኦዞጤመ ህዝብ ግንኙነት/
የኦሮሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኡስማን አሊ እና ም/ኃላፊ ወሮ አንሻ መሀመድ ከሰኔ 12/2017 ዓ.ም ጀምረው በሁሉም ወረዳዎችና በጤና ተቋማት በተመረጡ ተግባራት ድጋፍና ክትትል አድርገው ከተመለሱ የጤና መምሪያው ሰራተኞች ጋር ግምገማ አድርገዋል።
በውይይቱ በስምሪት ወቅት በቼክ ሊስት ተሰፍረው በተሰጡት ተግባራት ዙሪያ በዋነኝነት፦
✔️ የ2018 ዓም እቅድን እስከ ተቋማትና ግለሰብ ድረስ እንዲወርድ ማድረግ
✔️ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታን የንቅናቄ መድረክን በሁሉም ቀበሌዎች እንዲወርድ ማድረግ
✔️ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን ከሴቶች፣ ህጻናት፣ ማህበራዊ ዘርፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ማጠናከርና ያልተደራጁትን ሴቶች ማደራጀት
✔️ የጎጥ የጤና መሪዎችን በቀበሌ ማእከል ስልጠና መስጠት
✔️ ከኃይጅንና ሳኒቴሽን አንጻር ጽዱ ተቋማትና መንደርን ከመፍጠር አኳያና በየወረዳው ለሳኒቴሽን ግብይት እንዲውል በተመጣጣኝ ዋጋ እንዳሸጥ የተሰራጨው የፕላስቲክ መጸዳጃ ቤት ክዳን (M-Slab) ለማህበረሰቡ በደንብ በማስተዋወቅ ገዝቶ እንዲጠቀምበት ማድረግ
✔️የጤና መድህን አባላትን መረጃ በማጥራትና ወደ መረጃ ቋት በሶፍት ኮፒ ማስገባትና የውስጥ ኦዲት ማድረግ
✔️ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎችን በዝርዝር ማቀድና የደም የማሰባሰብ ስራ
✔️ በትራኮማ በሽታ ምክንያት የሚከሰተውን የአይን ቆብ ጭራ ወደ ውስጥ መቀልበስ በህክምና የማስተካከል ስራ ዘመቻ በሚፈለገው አግባብ ከመስራት አኳያ እንዲሁም
✔️ የወሳኝ ኩነት የአንድ መስኮት አገልግሎት በጤና ጣቢያዎች ማስጀመር እና ሌሎች ተግባራት ዙሪያ በየወረዳው በተደረገው ድጋፍ የተሰሩ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይትና ግምገማ ተደርጓል።
በመጨረሻ የውይይት መድረኩን የመሩት የመምሪያችን ኃላፊዎች በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት እንደ ዞን ለወረዳዎች ተደረገው ድጋፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በተከታታይነትና በትጋት መደገፍ እንደሚገባና የሚሰሩ ተግባራትን መረጃ በየእለቱ በመለዋወጥ መሆን እንደሚገባ በማሳሰብና የቀጣይ የስምሪት ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል።