
20/02/2025
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በፈንቲረሱ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ
************
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በፈንቲረሱ ዞን ኡዋ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ድጋፍ በኡዋ ወረዳ እየተሰራ የሚገኘውን ግድብ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
እየተገነባ የሚገኘው ግድብ ከ65 ሚሊዮን ሜትሪክ ክዩብ በላይ ውኃ የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በግድቡ አቅራቢያ የችግን ተከላም አካሂደዋል።
በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ በኡዋ ወረዳ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰሩዋቸው የሚገኙ የግብርና ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የዞን እና ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሁሴን መሐመድ