
02/07/2025
የጭፍራ ወረዳ ያለማውን እንሰሳት መኖ በወረዳው በድርቅ ለተጋለጡ ቀበሌዎች ስርጭት አደረገ።
ሰመራ ፣ ሰኔ 25/2017 (አፋ.ብ.መ.ድ)
በአፋር ክልል አውሲ ረሱ የጭፍራ ወረዳ ያለማውን እንሰሳት መኖ በወረዳው በድርቅ ለተጋለጡ ቀበሌዎች ስርጭት አድርጓል ።
የጭፍራ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ አሊ አርባ እንደተናገሩት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ እየተስተዋለ ያለው ድርቅ በእንሰሳት ላይ አስከፊ ጉዳት እንዳያደርስ በ19 ቀበሌ የመኖ ስርጭት ማድረጋቸውን ገልጿል
በመቀጠል የጭፍራ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወግሪስ ሀፋ እንደተናገሩት በወረዳው ላይ በተለያዩ ፕሮጀክቶች የተለያዩ ቀበሌዎቹ ላይ የመኖ ልማት ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ አንስተው ይህም በወረዳው ያለውን እንሰሳት ለድርቅ እንዳይገለጥ የማይናቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል
በመጨረሻም ይህን ድጋፍ የተረከቡት የቀበሌ ሊቀመንበሮችም እንደተናገሩት በዝናብ እጦት ምክንያት እየተከሰተ ባለው ድርቅ ምክንያት አርብቶ አደሩ ለግጦሽ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እየሄዱ እንደነበረ አንስተው ድጋፍ ይህን ችግር እንደሚቀርፍ ተናግረዋል
በመጨረሻም አመራሮች በወረደው ስር ያሉ ቀበሌዎች ላይ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል