Seve

Seve Yirabow Amaanale num yoo Ab

25/05/2024

በሰሜን ሪጅን ያለውን የመለዋወጫ እቃዎች እጥረት ለመቅረፍ እየተሰራ ነው፤
…….//……
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ሪጅን ያለውን የመለዋወጫ እቃዎች እጥረትን በመቅረፍ የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፊያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡

የዘርፉ ሥራ አሥፈጻሚ ተወካይ አቶ አበባው ያለው እንደገለጹት በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት በሪጂኑ ላይ ያጋጠመውን የመለዋወጫ እቃዎች አቅርቦት ችግር ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡

በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ያጋጠመውን የኃይል አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ተቋሙ ጥናት ማድረጉን የገለጹት አቶ አበባው ጥናቱን መሰረት በማድረግ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

በዚህም የሰሜኑን ግሪድ አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል “ኖርዘርን ግሪድ ሪሃብሊቴሽን” በተባለ ፕሮጀክት የማስተላለፊያ መስመር ኮንዳክተርና ኦፕቲካል ፋይበር (OPGW) ግዥ ተፈጽሞ ሰመራ ከተማ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

አቶ አበባው አክለውም ጉዳት ደርሶበት የነበረውን የአዲግራት ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ለመቀየርና በጭነት ልዩነት ወቅት ቮልቴጅን ለመቀጣጠር የሚረዳ መሣሪያ (shunt reactor) በግዥ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተከዜ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያም በጭነት ልዩነት ወቅት ቮልቴጅን ለመቀጣጠር የሚረዳ መሣሪያ የተከላ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመርም ጠቁመዋል፡፡

በፕሮጀክቱ አማክኝነት የሰሜኑን ግሪድ በማስተካከል በአካባቢው ያለውን የኃይል መዋዤቅ ይቀርፋሉ ተብሎ የታሰበ ተጨማሪ ትራንስፎርመር ግዥም በሂዳት ላይ እንደሚገኝ አቶ አበባው ተናግረዋል፡፡

በሁሉም ሪጅኖች ላይ ችግር የሆነው የኧርዚንግ ትራንስፎርመር (Earthing transformer) ን እጥረት ለመቅረፍም 40 ባለሰላሳ ሶስት እና ባለአስራ አምስት ኪሎ ቮልት ኮንትራት ተፈርሞ ግዥ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በሰሜን ሪጅን ከፍተኛ የመለዋወጫ እቃ ፍላጎት መኖሩን የሚናገሩት ተወካዩ የመለዋወጫ እቃዎች አብዛኞቹ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ በመሆናቸው እቃዎችን በማቅረብ በኩል አልፎ አልፎ የመዘግየት ችግር ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ ለሪጅኑ የሚያስፈልጉት የመለዋወጫ እቃዎች አብዛኞቹ ወደ ተቋሙ እቃ ግምጃ ቤት መግባታቸውን እና ቀሪውን ለማሟላት ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ አበባው ተናግረዋል፡፡

"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/ethio_power
ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Address

Logya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Seve posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share