Awusa.com

Awusa.com A resource and advocacy center for the art, history, culture, ethnography and current affairs of Afa

‹‹ጉበት የሌለው ገላ እና ቀይ ባሕር የሌለው አፋር አንድ ነው››   ‹‹የአፋር ድንበር ቀይ ባሕር ነው፤ የሰው ድንበር ደግሞ አፋር ነው››የአሰብ እና አፋሮችን ጥብቅ ትስስር ከሚገልጹ ስነ ...
15/01/2026

‹‹ጉበት የሌለው ገላ እና ቀይ ባሕር የሌለው አፋር አንድ ነው››

‹‹የአፋር ድንበር ቀይ ባሕር ነው፤ የሰው ድንበር ደግሞ አፋር ነው››

የአሰብ እና አፋሮችን ጥብቅ ትስስር ከሚገልጹ ስነ ቃሎች መሀል ሁለቱ ይጠቀሳሉ።

🔥 ሰበር ዜና! ጄኔራል አበባው ታደሰ ከወር በኋላ ዝምታቸውን ሰበሩ! "ካሁኑ መዘጋጀት አለብን!" 🚨​ላለፈው አንድ ወር በአደባባይ ያልታዩት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራ...
15/01/2026

🔥 ሰበር ዜና! ጄኔራል አበባው ታደሰ ከወር በኋላ ዝምታቸውን ሰበሩ! "ካሁኑ መዘጋጀት አለብን!" 🚨
​ላለፈው አንድ ወር በአደባባይ ያልታዩት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ዛሬ በአስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ጠንከር ያለ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አስተላልፈዋል!
​🗣️ የጄኔራሉ ወሳኝ መልዕክቶች፡
​🛑 "አሁን ያለው ጦርነት የቴክኖሎጂ እና የሳይበር ነው፤ ሠራዊቱ ከወዲሁ ራሱን ማዘጋጀት እና በሙያ መብቃት አለበት!"
​📡 "መገናኛ እና ኢንፎርሜሽን የወታደራዊ ስትራቴጂ 'ዋና የነርቭ ሥርዓት' ነው። ያለዚህ የትኛውንም የውጊያ ስምሪት ማሰብ አይቻልም!"
​ይህ የጄኔራል አበባው ንግግር፣ ትናንት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ "በቴክኖሎጂ የታገዘ ጦርነት ላይ መፍጠን አለብን" ካሉት ጋር ተዳምሮ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ አዲስና ዘመናዊ የዝግጅት ምዕራፍ እየገባ መሆኑን ያሳያል።
​💻 በሌላ በኩል: የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች (ሌ/ጄ መሰለ መሰረት እና ብ/ጄ አዱኛ ደሬሳ) ሠራዊቱ ሚስጥራዊ የመረጃ ስርዓቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ሥርዓት መቀየሩን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚመጥን የሰው ኃይል ስልጠና ላይ ትኩረት መደረጉን አረጋግጠዋል።

የአፋር ባህላዊ ህግ (ማድዓ)ን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል ሰፊ እንቅስቃሴ  እየተደረገ ነው🙏የአፋር ባህላዊ ህግ (ማድዓ)ን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል ሰፊ እንቅስቃሴ  እየተደረገ መ...
14/01/2026

የአፋር ባህላዊ ህግ (ማድዓ)ን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው🙏

የአፋር ባህላዊ ህግ (ማድዓ)ን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የአፋር ባህላዊ ህግ(ማድዓ)ን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) ማስመዝገብ የሚያስችል መረጃ ለመሰነድ ያለመ ኮንፍረንስ በአፋር ክልል ሠመራ ሊካሄድ መሆኑን ተገለጸ።

ኮንፍረንሱ ከየካቲት 3 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ስፖርት፣ ወጣቶችና ባህል ቢሮ ሃላፊ ሀሚድ ዱላ እና የአፋር ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቢሮ ሃላፊው ሀሚድ ዱላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ማድዓ ከሀገር በቀል እውቀቶች አንዱ ሲሆን ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያገለገለ የሚገኝ ነው።

ይህ ሀገር በቀል እውቀት ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት በህዝቦች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ይህንን ትልቅ እሴት በዩኔስኮ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ ሰፊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ማድዓን በዩኔስኮ ማስመዝገብ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የማይዳሰስ ቅርስ እንዲሆንና የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም የበለጠ እንዲነቃቃ ያግዛልም ብለዋል።

የአፋር ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሐመድ በበኩላቸው፥ በኮንፍረንሱ ባህላዊ መሪዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የአፋር ሱልጣን፣ የአፋር ልሂቃንና ሌሎችም የሚሳተፉበት መሆኑን ገልጸዋል።

በኮንፍረንሱ የአፋር ባህላዊ ህግ(ማድዓ)ን የተመለከቱ እሴቶች ላይ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን ተናግረዋል።

የአፋር ማህበረሰብ ከዘመናዊ የህግ ስርዓት በተጨማሪ ባህላዊ ዳኝነት ስርዓት ያለው ነውም ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የ ኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ኃላፊ በቀጣናዊ ውጥረቶች መሃል ሞቃዲሾን የጎበኙ ሲሆን የጠ/ሚኒስትሩን መልዕክት ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ማድረሳቸው ተጠቁሟል።በአፍሪካ ቀንድ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ው...
13/01/2026

የ ኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ኃላፊ በቀጣናዊ ውጥረቶች መሃል ሞቃዲሾን የጎበኙ ሲሆን የጠ/ሚኒስትሩን መልዕክት ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ማድረሳቸው ተጠቁሟል።

በአፍሪካ ቀንድ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በበረታበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት (NISS) ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው ዕለት ሞቃዲሾ ገብተዋል። በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ መልዕክትን ለሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ አድርሰዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሞቃዲሾ እንደደረሱ በቪላ ሶማሊያ ቤተ-መንግስት ከፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር መገናኘታቸውን ጋሮዌ ኦንላይን ዘግቧል። አምባሳደሩ ስላደረሱት መልዕክት ዝርዝር ይዘት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን፣ የኢትዮጵያም ሆነ የሶማሊያ መንግስታት ስለ ስብሰባው ውጤት እስካሁን የሰጡት ይፋዊ መግለጫ የለም።

በጉብኝቱ ወቅት አምባሳደር ሬድዋን ከሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ (NISA) ዳይሬክተር ማሀድ ሳላድ ጋር በኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት ተገናኝተው መወያየታቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ጋር እንደተደረገው ውይይት ሁሉ፣ የዚህም ውይይት ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

ጋሮዌ ኦንላይን እንደዘገበው፣ ይህ ድንገተኛ ጉብኝት የተካሄደው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌህ በጅቡቲ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ነው።

ጉብኝቱ እስራኤል ራሷን ገለልተኛ አድርጋ ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ግንኙነት መመሥረቷን የሚጠቁሙ መረጃዎች ካስነሱት አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ጋር ተገጣጥሟል።

ሶማሊያ ግዛቱን እንደ ሉዓላዊ ግዛቷ የምትቆጥረው በመሆኑ፣ የእስራኤል ውሳኔ በሞቃዲሾ በኩል ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞታል። በተጨማሪም ከበርካታ ዓለም አቀፍ አጋሮችም ትችት እየቀረበበት ሲሆን፤ ይህም የቀጠናውን ሁኔታ ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል።

ምንም እንኳን ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ በሞቃዲሾ መገኘታቸው፤ አዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ በአፍሪካ ቀንድ ግንኙነት እጅግ አንገብጋቢ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ በቀጥታ የመገናኛ መስመሮች ዳግም ለመቀራረብ እያደረጉት ያለውን ጥረት አመላካች ተደርጎ የሚወሰድ ነው ሲል ዘገባው አትቷል።

ከእነ ሙሉ ትጥቁና ታጣቂው እንደገቡ የሚያሳይ ፎቶ ነው🙏
12/01/2026

ከእነ ሙሉ ትጥቁና ታጣቂው እንደገቡ የሚያሳይ ፎቶ ነው🙏

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ ከነ አጃቢዎቹ በዳውንት ቆላ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጁን ሰጥቷል።ብቸኛው አዋጭ አማራጭ ሰላምና የሰላም መንገድ ብቻ ነው።ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ ከነ አጃቢዎቹ በ...
12/01/2026

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ ከነ አጃቢዎቹ በዳውንት ቆላ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጁን ሰጥቷል።

ብቸኛው አዋጭ አማራጭ ሰላምና የሰላም መንገድ ብቻ ነው።

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ ከነ አጃቢዎቹ በዳውንት ቆላ አካባቢ ከሌሊቱ 9:00 ሰሜን ለምስራቅ ዕዝ ለ46ኛ ክ/ጦር እጁን ሰጥቷል!

የኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ እና የአጃቢዎቹ እጅ መስጠት በዳውንት ቆላ ግንባር የተሰለፈው የጥፋት ቡድን የሞራል ስብራትና የስትራቴጂክ መፈራረስ ግልጽ ማሳያ ነው።



ይህ የፋኖ መፈረካከስ ከፍተኛ አመራሮች እጅ መስጠታቸው የቡድኑን መዋቅር እተበጣተሰ መሆኑን ያሳያል።

የሀገርን ሉዓላዊነት የሚገዳደር ሀይል መጨረሻው ወይ እጅ መስጠት አልያም መደምሰስ መሆኑን ዳግም ያልገባቸው አሁን ይገባቸዋል።

አስገራሚ የዱባ ጥቅሞችና መመገብ የሌለባቸው ስዎች እነሆ.......ዱባ (Pumpkin) በውስጡ በርካታ ቫይታሚኖችና ማዕድናት የያዘ በጣም ተወዳጅና ጤናማ የምግብ አይነት ነው። የዱባን ዋና ዋ...
11/01/2026

አስገራሚ የዱባ ጥቅሞችና መመገብ የሌለባቸው ስዎች እነሆ.......

ዱባ (Pumpkin) በውስጡ በርካታ ቫይታሚኖችና ማዕድናት የያዘ በጣም ተወዳጅና ጤናማ የምግብ አይነት ነው። የዱባን ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች እና ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸውን ሰዎች ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

​የዱባ ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች

1 ለዓይን ጤንነት፡ ዱባ በውስጡ ከፍተኛ መጠን ያለው ቤታ-ካሮቲን (Beta-carotene) ይዟል። ይህ ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ወደ ቫይታሚን A በመቀየር ዓይናችን ብርሃን እንዲያይና ከዓይን በሽታዎች እንዲከላከል ይረዳል።

​2 የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ይጨምራል፡ በውስጡ የያዘው ቫይታሚን A፣ C እና E እንዲሁም ብረት (Iron) በሽታ የመከላከል ስርአታችንን በማጠናከር ከኢንፌክሽኖች ይጠብቀናል።

3 ለልብ ጤንነት፡ ዱባ የፖታስየም፣ የፋይበር (Fiber) እና የቫይታሚን C ምንጭ ነው። ፖታስየም የደም ግፊትን ለመቀነስና የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል።

4=​ለክብደት መቀነስ፡ ዱባ በውሃ የበለፀገ እና ካሎሪው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ሳይወፍሩ ረሃብን ለማስታገስ ይረዳል።

5=​ለቆዳ ጤንነት፡ በውስጡ ያሉት ንጥረ ነገሮች ቆዳችን ከፀሐይ ጨረር (UV rays) እንዲጠበቅና ውብ እንዲሆን ያደርጋሉ።

ዱባን መመገብ የሌለባቸው ወይም ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው ሰዎች

​ምንም እንኳን ዱባ ለብዙዎች ጠቃሚ ቢሆንም፣ የሚከተሉት ሰዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል

1=​አለርጂ ያለባቸው ሰዎች፦ አልፎ አልፎ በዱባ ላይ የአለርጂ ችግር ያለባቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ዱባ ተመግበው ሽፍታ ወይም ማሳከክ የሚታይባቸው ከሆነ ማቆም አለባቸው።

2=​የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች፦ ዱባ ከፍተኛ የፖታስየም መጠን አለው። ኩላሊታቸው በትክክል የማይሰራ ሰዎች ፖታስየምን ከሰውነት ማስወገድ ስለሚቸግራቸው በብዛት መመገብ የለባቸውም።

3=​የሽንት ማስወገጃ መድሃኒት (Diuretics) የሚወስዱ ሰዎች፦ ዱባ በተፈጥሮው ሽንትን የማስወገድ ባህሪ አለው። ይህ ደግሞ የሚወስዱትን መድሃኒት ስራ ሊያዛባ ስለሚችል ከሀኪም ጋር መማከር ያስፈልጋል።

4=​ዝቅተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች፦ ዱባ የደም ግፊትን የመቀነስ ባህሪ ስላለው፣ ቀድሞውኑ የደም ግፊታቸው በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች በመጠኑ መመገብ ይኖርባቸዋል።

​ማሳሰቢያ፦ የዱባ ፍሬ (Pumpkin seeds) በጣም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በውስጡ ከፍተኛ ፋይበር ስላለው በአንድ ጊዜ በብዛት መመገብ ለሆድ መነፋት ወይም ለጋዝ ችግር ሊዳርግ ይችላል።

ጦርነት ክፉ እና አስቀያሚ ነው!------ይህ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እምብርት ላይ የሚገኘው የኮሪቲያ ሆቴል ነው። በቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ የተሰራ ...
11/01/2026

ጦርነት ክፉ እና አስቀያሚ ነው!
------
ይህ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እምብርት ላይ የሚገኘው የኮሪቲያ ሆቴል ነው። በቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ መንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ የተሰራ ባለ አምስት ኮከብ luxury hotel ነው። ለሆቴሉ ግንባታ 80M Euro ወጪ ሆኗል። ኪነ-ህንጻው በቀዘፋ ላይ ጀልባ ያስመስለዋል። በአርክቴቸሩ እና በፋናንስ ምንጩ ምክንያት የካርቱም ሕዝብ "የጋዳፊ እንቁላል" ይለዋል።
------
በመጀመሪያው ፎቶ ላይ የሚታየው ሆቴሉ በተሰራበት ዘመን የነበረው ውበትና እና ግርማ ሞገስ ነው። የዛሬ ሶስት ዓመት በሱዳን በፈነዳው ጦርነት ምክንያት ሆቴሉ ምስቅልቅሉ ወጥቶ በሁለተኛው ፎቶ ላይ የሚታየውን መልክ ይዟል። ካርቱም የነበራት ብቸኛው ውብ ህንጻ እንደዚህ ሆኖባታል።
------
ጦርነት እንዲህ ነው! ውጤቱ ውድመትና ጥፋት ብቻ ነው። የሰዎች እልቂት፣ የብዙዎች መፈናቀል፣ የቤተሰብ መበተንና ስደትም የጦርነት ክፉ ገጽታዎች ናቸው።
ህሊና ያለው ሰው ጦርነትን አይመኝም። አዕምሮው የሚሰራ ሰው ጦርነትን አይናፍቅም። ከጦርነት የሚያተርፉት የመሳሪያ ነጋዴዎች፣ ህገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችና ጦርነቱን የቀሰቀሱ ጀብደኞች ብቻ ናቸው። በዳፋውና ውድመቱ የሚጠፉት ሰፊው ሕዝብና ሀገር ናቸው።
እባካችሁ ጦርነትን አንናፍቅ። ጦርነትን እንጠየፍ። ጦርነትና ጦረኞችን እናውግዝ።
ሰላም! ሰላም! ሰላም!

©አፈንዲ ሙተቂ/Afendi Muteki- Ethnographer

አሰብ 'ነፃ ወደብ' ለኢትዮጵያ 👍****የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ነፃ ወደብ ነበር ፣የአሰብ ወደብ ከመቶ አመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ የኢትዮጵያ ዋና የንግድ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ለዚህም...
10/01/2026

አሰብ 'ነፃ ወደብ' ለኢትዮጵያ 👍
****
የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ነፃ ወደብ ነበር ፣የአሰብ ወደብ ከመቶ አመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ የኢትዮጵያ ዋና የንግድ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ለዚህም ነበር '' አሰብ ማለት ዉሃ ስንራጭ ያደግንበት ሀብታችን እርስታችን ነው" ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የተናገሩት፡፡

"ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ለምታደርገው ጥረት ጃፓን ድጋፏ ይቀጥላል" - የጃፓን ፓርላማ ልዑክ‎በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢንዶ ቶሺያኪ ...
09/01/2026

"ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ለምታደርገው ጥረት ጃፓን ድጋፏ ይቀጥላል" - የጃፓን ፓርላማ ልዑክ


በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢንዶ ቶሺያኪ የተመራ የጃፓን የፓርላማ ልዑክ ቡድንን ተቀብሎ ውይይት አደረገ።

ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ጃፓን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

‎በውይይቱ የጃፓን ልዑክ ቡድን መሪ ኢንዶ ቶሺያኪ፤ ይህ ዓይነቱ መድረክ የቆየውን የኢትዮጵያን እና የጃፓንን ወዳጅነት በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከርና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል።

ጃፓን፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛውን ግዙፍ የሕዝብ ቁጥር የያዘችና በዕድገት ጎዳና ውስጥ ያለች ሀገር ‎እንደመሆኗ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እንዲሁም የዓለም የንግድ ማኅበር አባል ለመሆን ለምታደርገው ጉዞ ድጋፏ ይቀጥላል ብለዋል።

ኢንዶ ቶሺያኪ ኢትዮጵያም የሴቶችን ተሳትፎና የአስተዳደር አካል በማድረግ እየሰራች ያለችበት ሂደት የሚደነቅ መሆኑን መግለጻቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ እና ጃፓን የሁለቱ ሀገራት ረጅም ዓመታት በዲፕሎማሲ ፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ረጅም ታሪክ ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አስታውሰው፤ ለጋራ እድገት እና ብልፅግና የሚጠቅሙ መልካም ግንኙነቶች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ እና ጃፓን ግንኙነትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር በማደግ በንግድ ፣ በልማት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው ትስስር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መምጣቱንም አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ‎ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በማከናወን በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ በርካታ ዕድገትን እያስመዘገበች እንደምትገኝ ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኗን የገለጹት ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) ፤ በዚህ ረገድ ጃፓን በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላት ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በመጀመር ረገድ ቀዳሚ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረጓም በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ሙሳ ከአፋር ሕዝብ የተገኘች፣ በቀይ ባህር ዳርቻ ተወልዳ ያደገች ጀግና ሴት ናት!!በአፋር ክልል በበርሀሌ ተወልዳ በአሰብ ያደገች ናት (አሰብ የቀይ ባህር ዳርቻ ወደብ...
08/01/2026

ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ሙሳ ከአፋር ሕዝብ የተገኘች፣ በቀይ ባህር ዳርቻ ተወልዳ ያደገች ጀግና ሴት ናት!!

በአፋር ክልል በበርሀሌ ተወልዳ በአሰብ ያደገች ናት (አሰብ የቀይ ባህር ዳርቻ ወደብ ከመሆኑ በተጨማሪ በታሪክ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው)።

ሲቪል ኢንጂነሪንግ ተምራለች፣ በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ ማስተርስ ዲግሪ አላት፡፡

በ2018 ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት መከላከያ ሚኒስትር ሆና አዲስ ታሪክ ፈጥራለች።

ከዚያ በኋላ ሌሎች ሚኒስቴር ቦታዎች ላይ አገልግላለች፣ በ2024 እንደገና ወደ መከላከያ ሚኒስቴር ተመልሳለች (አሁንም በዚህ ቦታ ላይ ናት)።

በእርግጥ የሴቶች እና የአፋር ሕዝብ ኩራት ናት! ብዙ ሴቶችን በመምራት እና በፖለቲካ መስክ በመሳተፍ ታላቅ ምሳሌ ናት፡፡

Aisha Mohammed M***a 🫡🫡🫡🫡

አሰብ እና ምጽዋ የኢትዮጵያ ሉአላዊ ድንበር ናቸው። *********************የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በ1950 አሰብ አስተዳደር ግዛት እና የምጽዋ ወደብ የኢትዮያጵያ ድንበር እን...
08/01/2026

አሰብ እና ምጽዋ የኢትዮጵያ ሉአላዊ ድንበር ናቸው።
*********************
የተባበሩ መንግስታት ድርጅት በ1950 አሰብ አስተዳደር ግዛት እና የምጽዋ ወደብ የኢትዮያጵያ ድንበር እንዲሆን ወስኗል። ኤርትራ ደሞ በፌድሬሽን ራሷን ችላ እንድትተዳደር የፈቀደ ሲሆን ይሄንንም ጉዳይ ህግ በደንብ የተብራራ ስለሆነ አንብረን እንመልከት። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህግ መሠረት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌድሬሽን እንዲገናኙ የፈቀደ ሲሆን ወደቦቹ ማለትም ምጽዋ እና አሰብ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ድንበር እንዲሆኑ የተወሰነ ነው። ለኤርትራ ህዝብ የራስ አስተዳደር መመስረት መብት በፌድሬሽኑ ውስጥ የፈቀደ መሆኑንም ይገልጻል።

የተባበሩ መንግስት ዋና ውሳኔ (390 A (V) ይባላል
*********************
1) በ1950 በፈረንጆች ቀን አቆጣጠር ጥር 2 ዩኔን ጠቅላላ ምክር ቤት ውሳኔ 390 A (V) ብሎ የተባለውን ውሳኔ የሰጠበት ሲሆን “ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን አስተዳደር ስር የራሷ ነጻ የአስተዳደር ክልል ኑሯቸው በኢትዮጵያ መንግስት ሥልጣን ስር ትሆናለች” ይላል።

2) በዚህ ውሳኔ ውስጥ ኤርትራ ምን ያህል ራሷን በራሷ ታስተዳድራለች የሚለውን እና ኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ ያለው ሉዓላዊ ሥልጣን ምን እንደሚመስል በዝርዝር የሚወስን ነው “Federal Act” ተብሎ የተጠራ የመሠረታዊ ህግ ክፍል አለው።

ኤርትራ የፌዴሬሽኑ እንዴት ማዋቀር እንዳለበት ይገልጻል
********************
3) ኤርትራ ክፈለ ሃገር ውስጣዊ ጉዳይ ላይ የራሷ ህጎችን ማውጣት፣ መንግስታዊ አስተዳደር እና ፍርድ ቤቶች የማቋቋም መብት እንዲኖራት ይፈቅዳል እናም ''የአስተዳደር ነጻነት” እንዳለት ይገልጻል።

4) ሁኖም ግን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ መከላከያ ሰራዊት፣ ሃገራዊ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ጨምሮ አጠቃላይ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ስልጣን ማለትም በኢትዮጵያ መንግስት ስር እንደሆነ ተደንግጓል።

የኤርትራ ራስ በራስ አስተዳደር መብቶች ላይ እንዲህ ይላል
**********************
5) በኤርትራ ክፍለ ሃገር ውስጥ ያለው አስተዳደር ጉዳይ ህግ (የትምህርት፣ የቋንቋ አጠቃቀም፣ መንግስታዊ አቅርቦት እና አገልግሎት) ወዘተ ለኤርትራ ክፈለ ሃገር አስተዳደራዊ መንግስት እንዲመራው መብት ይሰጣል ስለዚህም በኤርትራ ውስጥ በህዝብ የተወከለ ሕጋዊ ምክር ቤት እንዲኖራት ይደነግጋል፤ በፌድራል ደረጃ ደሞ ከኤርትራ ተመራጮች እንዲወከሉ ደንግጓል።

6) ኤርትራ ክፈለ ሃገር የራሷን አስተዳደር የምታቋቁመበት ህግ መንግስት እንዲኖር ይፈቅዳል። ከፌድራል ህግ መንግስት ጋር የተናበበ እና የማይጣረስ እናም ይሄን ለመምራት በየዩኤን ኮሚሽነር መሪነት የእንግሊዝ እና የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል።

ዜግነት እና ሉአላዊነት በተመለከተስ?
****************
7) የኤርትራ ፌዴሬሽኑ ሲቋቋም “አንድ ዜግነት” ማለትም በኢትዮጵያ ዜግነት ስር እንዲቀጥሉ ይፈቅዳል እናም በኤርትራ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ የፌዴሬሽኑ ባለቤት እና የአንድ ኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸው ወስኗል።

8) ሁኖም ግን በኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ዜግነት ያላቸው የፌዴሬሹ አባል መሆን እና አለመሆን ዜግነት ምርጫ እንዲወስዱ የመምረጫ ግዜ ገደብ የሚፈቅድ ህግም ተቀምጧል። ምን ማለት ነው? በኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ የሌላ ሃገር ዜጎች ነበሩ (ጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ የመን፣) ወዘተ እናም ከትውልድ ሃገራቸውን ዜግነት ቀይረው በኤርትራ ስራ የኢትዮጵያን ዜግነት ይወስዳሉ የሚለውን ለማየት የተካተተ ነው።

9) በመጨረሻም 1952 መስከረም 11 በፈረንጆች ቀን አቆጣጠር የፌዴሬሽኑ ምስረታ ህጋዊ ሁኔታ ተመዘገበ። በዩኤን መዝገብ መሰረት “ከኢትዮጵያ ጋር የኤርትራ ፌዴሬሽን ተቋቋመ” ብሎ በቀጥታ አረጋግጧ ጉዳይ አጸደቀው።

እንግዲህ ዩኤን ህጋዊ ማስረጃ መሰረት ከሄድን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሥልጣን ሳይነካ ኤርትራን በውስጥ አስተዳደር ራሷን እንድታስተዳደር ይፈቅዳል እንጂ አሰብ እና ምጽዋ የኢትዮጵያ ህጋዊ ድንበር እንደሆኑ በነጭ እና በጥቁር ቀለም በደማቅ ተጽፎ ይገኛል። ተጨማሪ ንባብ ለሚፈልግ ከስር ያሉ pdf ፋይሎች ከፍቶ ማንበብ ይችላል። መለስ ዜናዊ የሚባል ሰውዬ ብቻ 👎

1) Eritrea: Report of the United Nations Commission for Eritrea https://www.refworld.org/legal/resolution/unga/1950/en/7687

2) Ethiopia/Eritrea: UN General Assembly Resolution 390 A (V) of 2 December 1950 https://citizenshiprightsafrica.org/ethiopia-eritrea-un-general-assembly-resolution-390-a-v-of-2-december-1950/

3) Eritrea and Ethiopia - The Federal Experiencehttp://www.diva-portal.org/smash/get/diva2:272775/FULLTEXT01.pdf

4) General Assembly-Fifth Sessionhttps://www.worldlii.org/int/other/UNGA/1950/119.pdf

5) Transcending the Ethio-Eritrean Conundrum: A Vision for a ... https://hornreview.org/2025/07/25/transcending-the-ethio-eritrean-conundrum-a-vision-for-a-better-tomorrow/

6) report of the United Nations Commissioner in Eritrea https://www.refworld.org/legal/resolution/unga/1952/en/10199

7)1952 UN Yearbook the United Nationshttps://cdn.un.org/unyearbook/yun/pdf/1952/1952_271.pdf

8) Understanding Eritrea's Status: A Historical Perspective https://eastafricanreview.com/2025/01/28/ethiopia-eritrea-federation-history/

9) General Assembly-Fifth Sessionhttps://digitallibrary.un.org/record/666499/files/A_RES_390(V)%5BB%5D-EN.pdf

10) General Assembly-Fifth Session https://docs.un.org/en/A/RES/390(V)

Adresse

Vienna

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Awusa.com erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Teilen