22/08/2023
ምክንየታዊ ትውልድ :ለሁለንትናዊ ብልጽግና::
************************************
ምክንየታዊነት ትውልድ ማለት ሲሜቱን መምራት ማስተዳድር :መግዛት :መንዳት የሚችል ትውልድ ማለት ነው::
የሚነዳ ምክንያታዊ ትውልድ ::ምክንየታዊ ትውልድ ማለት እያንዳንዱ እንቅስቃሴውን ለምን?
እንዴት? መቼ? በማን? ስለምን? በምን? እያለ የሚጠየቅ :የሚያስጠየቅ :በሀሳብ ልእልና የሚያምን :የተሳሳቱ ሀሳቦችን ሀሳብን የሚያምን ነው::
ምክንያታዊ ትውልድ ያልታረሙ አንደበቶችን በታረሙ አንደበቶች ይተካል:ስሜታዊነትን በአመክንዪ ይቀየራል፤
ገረድነትንና አሽከርነትን በጌትነትና በነጻነት ይለውጣል፤ አስመሳይነትን በግልጽነት ያከስማል፤ ሀሳብ አልባነትን በዕሳቤ የበላይነት ያረጋግጣል፤ ርዕይ አልባነትን በርዕይ ባለቤትነት ይተካል፤ በኢ - ምክንያታዊነት ላይ ምክንያታዊነትን ያነግሳል፡፡
ምክንያታዊ ትውልድ ከትላንት ይማራል፤ በጎውን ከትላንት በመውሰድ ዛሬ ላይ የራሱን አሻራ ያኖራል - ለማኖርም ይተጋል:ለነገና ከነገ ወዲያ በማሰብ ትውልዳዊ መሠረትን በማይናወጥ ዕሳቤ ላይ ይጥላል፡፡ የሰው ልጅ ከምክንያታዊነት ሲርቅ ወደ ሲሜታዊነት ይቀርባል፡፡
ከምክንያታዊነት ይርቃል፡፡ አንደኛው ከሌላኛው ጋር ሕብረት የለውም፡፡ ሊኖረውም አይችልም፡፡ የአንዱ ባህሪያትና ጠባያት ለሌላኛው ባህሪያትና ጠባያት ግጣም መኾን የማይችሉ ተቃራኒ የኹነቶች መገለጫ ናቸው፡፡
ምክንያታዊ ትውልድ በምንም አይነት መንገድ መንጋ አይኾንም፡ለአመክንዮ፣ ለዕውነትና ለዕምነት ግን መንጋ ይኾናል፡፡
ምክንየታዊ ትውልድ የድርገቱን ትክክልኝነት በአድራጊው ማንነትና ምንነት ምክንያታዊ ትውልድ አንድን ድርገት ወይም ሀሳብ ለመቃውም ወይም ለመደገፍ አድራጊው ወይም የሀሳቡ ባለቤት ማነው ብሎ በመንጋ የሚቃውም ወይም የሚደግፍ ሳይሆን ድርጊቱ ወይም ሀሳቡን ከባሌቤቱ ለይቶ በሚዛናዊነትና ለአገርና ለህዝብ ያለው አዎንታዊና አሉታዊ አስተዋጽኦ አመዛዝኖ የሚቃውም ወይም የሚደገፍ ትውልድ ማለት ነው::
ምክንያታዊ ትውልድ አንድን ሀሳብ በመንጋ ሲደግፍ መንጋነቱ በምክንያቱ ላይ ካለው ዕምነት የሚመነጭ እንጂ በአድራጊው ወይም በሀሳቡ ባለቤት ባለው እምነት ወይም ከአድራጊው ወይም ከሀሳቡባለቤት ጋር ባለው ግንኝነት ወይም ዝምድና ላይ ተመርክዞ አይደለም::
ሲሜቱን የሚነዳ ምክንያታዊ ትውልድ እንኳንስ የራሱ ያለፈ ትውልድም ኾነ የሚመጣ ትውልድ አለኝታ ነው! ምክንያታዊ ትውልድ እያንዳንዱን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን በምክንያት በመምራት ያለፈ ትውልድ በጎ ዕሴት ጠባቂና አስጠባቂ፤ የራሱን ትውልዳዊ ኃላፊነት በመወጣት የሚቀጥለውን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚመጣው ትውልድ መኩሪያና አለኝታ ይኾናል፡፡
***************************
ስለ ሲሜታዊ ትውልድ በቀጣይ አቀርባለሁ -----
ምክንየታዊ ትውልድ :ለሁለንትናዊ ብልጽግና::************************************ምክንየታዊነት ትውልድ ማለት ሲሜቱን መምራት ማስተዳድር :መግዛት :መንዳት የሚችል ትውልድ ማለት ነው:: የሚነዳ ምክንያ....