Sheka TV

Sheka TV This is the official Sheka TV page - where you can get all the latest news in Amharic, Sheki Noono, Majang.

ከሕዳሴው ግድብ ጎን ለጎን ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስኬታማ ጉዞበማንሠራራት ቀን የሀገራችንን የልማት ምዕራፍ ስናበስር፣ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ግዙፍ የኃ...
07/09/2026

ከሕዳሴው ግድብ ጎን ለጎን ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስኬታማ ጉዞ

በማንሠራራት ቀን የሀገራችንን የልማት ምዕራፍ ስናበስር፣ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ የሆነው የኮይሻ የውሃ ኃይል ፕሮጀክት አጠቃላይ ግንባታ አፈጻጸም ሀገራዊ ተስፋን በፈጠረበት ዓመት ነው።

201 ሜትር ቁመት ያለው ይህ ግዙፍ ግድብ 6.4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የአፈር ቁፋሮ ማካሄድ የተቻለበት ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ኃይል የማመንጨት አቅም ወደ አዲስ ከፍታ የሚያሸጋግር ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው።

የግንባታው አፈጻጸም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ግድቡ ከሚፈልገው 7.72 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ውስጥ 81.2 በመቶው ማለትም 6.27 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

የኃይል ማመንጫ ቤቱ የቁፋሮ ሥራ እንዲሁም የሲቪል ሥራው የመጀመሪያ ደረጃ የኮንክሪት ሙሌት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ሙሉ ፕሮጀክቱን በታቀደው ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ወደ ሥራ ለማስገባት የሌት ተቀን ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

የ1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የማይነቃነቅ የኃይል ማዕከል የሚያደርጋት ቀጣዩ ታላቅ የልማት ማሳያ ነው።

ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላቱም በላይ የኤሌክትሪክ ኤክስፖርት አቅማችንን በማሳደግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ማንሠራራት በጽኑ መሠረት ላይ የሚተክል ይሆናል።

የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በጥራት ቁጥጥር ስራ ላይ ትኩረት ማድረጉን የዱይና ቡና ልማት ፕሮጀክት አስታወቀፕሮጄክቱ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክ...
07/09/2026

የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በጥራት ቁጥጥር ስራ ላይ ትኩረት ማድረጉን የዱይና ቡና ልማት ፕሮጀክት አስታወቀ

ፕሮጄክቱ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ተጠይቋል።

ፕሮጀክቱ የ2017/18 የምርት ዘመን አፈጻጸምና የ2018/19 የምርት አሰባሰብ ዕቅድ ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ አካሂዷል ።

በተጠናቀቀው የ2017/18 የምርት ዘመን በቡና ጥራት ቁጥጥር ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ አንደኛ ደረጃ የታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መላክ መቻሉ ተመላክቷል ።

በምርት ዘመኑ 33 ሺህ 1 መቶ አስራ አምስት ኩንታል ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን 25 ሺህ 762 በመሰብሰብ የዕቅዱን 77 በመቶ ማሳካት መቻሉን አቶ ስንታየሁ መሸሻ በፕሮጀክቱ የቡና ሴርትፍኬሽንና አሰራር ስርዓት ማሻሻያ ክፍል ኃላፊው ተናግረዋል ።

የቡና ጥራትን ለማምጣት ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ማሽን በማስገባትና የምርት ቁጥጥር ግብረ ኃይል በማቋቋም እንዲሁም ለዘርፉ ባለሙያዎች ተከታታይ የክሂሎት ስልጠናዎችን በመስጠት ውጤታማ ስራ በመከወን በአለም አቀፍ(Rainforest Alliance ) እና ሬይንፎረስት አሊያንስ እና ካፈ ፕራክቲስ የእውቅና ሰርትፍክት ማግኘቱንም ተናግረዋል ።

በቀጣይ የምርት ዘመንም የተሻለ ጥራት ያለውን ቡና ለመሰብሰብ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውንም አንስተዋል።

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ አያና በበኩላቸው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ሟሟላት የሚችል ቡና ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በድርጅቱ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ፍቅሩ ከድርጅቱ ሰራተኞች ባሻገር የአካባቢው ማህበረሰብ፣የአጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የመንግስት አካላት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ነው የገለጹት።

ያደሩ የአካባቢው ነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ፕሮጀክቱ እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

በተለይም በምርት አሰባሰብ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ልማቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

የአንድራቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ በርናባስ ደሰኖ በበኩላቸው ልማቱ ከኢንቨስትመንት ባሻገር ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት የሚሰራ ድርጅት በመሆኑ በመደጋገፍ መሥራቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው የተናገሩት አቶ በርናባስ በተጨማሪም ያልተጠናቀቁ የህዝብ ጥያቄዎችን ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክቱ መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።

በመድረኩ የሸካ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አስታውሰኝ አይሞ፣በሆራይዘን ፕላንተሽን የሰኩሪትና ደህንነት ክፍል ኃላፊው ረ/ኮሚሽነር ፋሲል አሻግሬን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ: ተሻለ ተካልኝ

"የጽናት ቀን" የደኅንነት እና ጸጥታ ተቋማትን ቁመና በሚዘክር እና ለቀጣይ ተልዕኮ በሚያነቃቃ መልኩ ይከበራል - ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታበኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላ...
07/09/2026

"የጽናት ቀን" የደኅንነት እና ጸጥታ ተቋማትን ቁመና በሚዘክር እና ለቀጣይ ተልዕኮ በሚያነቃቃ መልኩ ይከበራል - ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የተቋሙ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ እንደገለጹት በነገው ዕለት ጳጉሜን 3 የሚከበረው "የጽናት ቀን" የደኅንነት እና ጸጥታ ተቋማት የደረሱበትን ጠንካራ ቁመና በሚዘክርና ለቀጣይ ሥራም በሚያበረታታ መልኩ በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል።

የደኅንነት እና ጸጥታ ተቋማት ማንኛቸውንም ፈተናዎች እና አደጋዎች በጀግንነት በመመከት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የሕዝብ አንድነት፣ የአየር ክልል እና የየብስ ግዛት ማስከበር መቻላቸውን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራሉ ገልጸዋል።

ሠራዊቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተደቀኑ ማንኛቸውንም ፈተናዎች እና አደጋዎች በጀግንነት የመመከት እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን፣ የሕዝብ አንድነትን፣ የአየር ክልል እና የየብስ ግዛትን የማስከበር ታሪካዊ ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታጥቀው የሀገርን ዳር ድንበር እና የሕግ የበላይነት እያስከበሩበት ያለውን ቁመና በሚያሳይ መንገድ ቀኑ እንደሚከበር ጠቁመዋል።

ተቋማቱ ያከናወኗቸውን መልካም ሥራዎች በማንሳት፣ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የብጥብጥ ሥጋት ተላቅቃ ወደ ተሻለ የሰላም እና የአንድነት ደረጃ የምትሸጋገርበትን አቅጣጫ ለመላው ሕዝብ በወጉ በማብራራት ጭምር ይከበራል ነው ያሉት።

የመከላከያ ሠራዊት በጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት ላይ የተገነባ፣ የሀገር ዋልታ እና ትልቅ ባለውለታ ተቋም በመሆን ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ማስከበር መቻሉን አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስም አደረጃጀቱን ዘመናዊ በማድረግ እና በቴክኖሎጂ በመታጠቅ ወንጀልን የመከላከል፣ የመመርመር እና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ሌሎች የደኅንነት ተቋማትም ራሳቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሰው ሠራሽ አስተውሎት በማደራጀት ሀገርን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ ተነስቷል።

ነገ ጳጉሜን 3 የሚከበረው "የጽናት ቀን"፤ ለሰላም እና ደኅንነት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የጸጥታ አካላት ላበረከቱት አገራዊ አገልግሎት ምስጋና የሚቀርብበትና ለቀጣይ ተልዕኮ በጽናት እንዲዘጋጁ ጥሪ የሚተላለፍበት ዕለት ይሆናል።

07/09/2026

የቀን 01/13/2018 ዓ.ም የአማርኛ ዜና ሸካ ቴሌቭዥን

የኢትዮጵያ ማንሰራራት፦ ሉዓላዊነትን በላብ እና በምርታማነት የማጽናት ምዕራፍኢትዮጵያ በታሪክ ውጣ ውረዶች እና በዘመናት ፈተናዎች ውስጥ በብስለት አልፋ፣ ለከፍታዋ እና ለገናናነቷ የሚመጥነውን...
07/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት፦ ሉዓላዊነትን በላብ እና በምርታማነት የማጽናት ምዕራፍ

ኢትዮጵያ በታሪክ ውጣ ውረዶች እና በዘመናት ፈተናዎች ውስጥ በብስለት አልፋ፣ ለከፍታዋ እና ለገናናነቷ የሚመጥነውን የታላቅነት እና የማንሰራራት ጉዞ ጀምራለች።

አሁን ላይ በታሪካችን አይተን የማናውቃቸውን አዳዲስ ሀሳቦች ወደ ተግባር በመቀየር እና ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ እናት ሀገርን አጽንተን ለትውልድ እንደምናስረክብ በተግባር እያሳየን እንገኛለን።

በተለይም የጳጉሜን ወር ስንቀበል ያለፈውን የምንገመግምበት፣ ክፍተታችንን የምናርምበት እና ለቀጣዩ የብልጽግና ጉዟችን ተስፋ የምንሰንቅበት ልዩ ታሪካዊ መድረክ ነው።

የዘንድሮው የጳጉሜ ቀናትም "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል መከበሩ፣ ሀገራችን ከነበረችበት አዝጋሚ ጉዞ ተላቃ በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአገልግሎትና በቱሪዝም ዘርፎች እያስመዘገበች ያለውን ሁለንተናዊ የሪፎርም ስኬት የሚያንጸባርቅ ነው።

ታሪካችንን ወደኋላ መለስ ብለን ስንቃኝ፣ ኢትዮጵያውያን የህልውና አደጋ ባጋጠመ ቁጥር ውድ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ግን ይህ አውድ እና መንገዱ ተቀይሯል። በዚህ ውስብስብ ዘመን በደም የተከበረ ነፃነት እና በአጥንት የተረጋገጠ ሉዓላዊነት በላብ ካልጸና፣ ጠንክሮ በማምረት ካልታጀበ ውጤቱ የታሪክ ተናጋሪነት ብቻ ሆኖ ይቀራል።

የላብ ዋጋ ጠንካራ ተጽዕኖን የሚፈጥርበት ጽኑ መንገድ በመሆኑ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የህልውናዋ ማረጋገጫ ዳርድንበርን ከመጠበቅ ባሻገር ከምግብ ጥገኝነት መላቀቅ፣ ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚ መሰረት መገንባት እና በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ መሆን ነው።

ይህንን የላብ እና የትጋት ፍልስፍና በተግባር ያሳየንበት ትልቁ ማሳያ፣ “አይችሉም” የሚለውን ትርክት የሰበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው።

ያለማንም የውጭ እርዳታ፣ በራሳችን ሀብት፣ ድካም እና ዕውቀት የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ እና ተከታታይ የኃይል ማመንጫዎችን ወደ ሥራ በማስገባት ለምሥራቅ አፍሪካ ብርሃን ፈንጥቀናል። ግዙፍ ማምረቻዎቻችንንም በታዳሽ ኃይል ለማንቀሳቀስ አቅም ፈጥረናል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ግብርና ከዝናብ ጥገኝነት እና ከእጅ ወደ አፍ አኗኗር ወጥቶ፣ ዓመቱን ሙሉ በማምረት ወደ ገበያ ተኮር ስርዓት ተሸጋግሯል።

የሌማት ትሩፋት፣ የክላስተር ግብርና እና በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ያጸደቅነው የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄዎች የምግብ ሥርዓታችንን ከማዘመንም አልፈው፣ የዜጎችን የስራ ባህል ቀይረዋል።

በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተመዘገበው ትርፍ አምራችነት ኢኮኖሚያችንን በእጅጉ ደግፎታል።

በማዕድን ዘርፉም እንደ ወርቅ፣ ኦፓል እና የድንጋይ ከሰል ያሉ ሀብቶችን ከህገ-ወጥ አሠራር በማላቀቅና የድንጋይ ከሰል እጥበትን ሀገር ውስጥ በማስፋፋት የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ የኢኮኖሚያችን ዋልታ እየሆኑ ነው።

የቱሪዝም ኢንዱስትሪውም ተፈጥሯዊ ሀብትን ከማስጎብኘት ባለፈ፣ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚመጥኑ እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሃላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ እና የንጋት ሐይቅ ያሉ ግዙፍ መዳረሻዎችን በላቀ ደረጃ አልምቷል።

ከዚህም ባሻገር በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ስኬት እና በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ አማካኝነት ሀገራችንን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ በማሸጋገር ላይ እንገኛለን።

እነዚህን ድሎች ስንመለከት፣ ለዘመናት የነበሩ ቁርሾዎች እና የታሪክ ስብራቶች የልማት ህልማችንን እንዴት ወደ ኋላ እንደጎተቱ በተግባር አይተነዋል።

ይህንን ታሪክ ለመቀየር እና ዘላቂ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ ሰፊ ውይይቶችን ማካሄዱ የዘመናችን ትልቁ ድል እና የማንሰራራታችን ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።

በዚህ የማንሰራራት መንፈስ ነው የዘንድሮዉን የጳጉሜ ቀናት የምናከብረው። በአዲሱ ዓመት፣ ምርታማነታችንን አጎልብተን፣ ኅብረታችንን አጠናክረን፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ ሁላችንም በትጋት ልንሠራ ይገባል! ነጋችንን በዛሬው ስኬታችን ላይ በላባችን እንገነባለን!

‎ፈጣንና ጥራት ያለው ፍትህ በመስጠት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ።‎‎የሸካ ዞን ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 5ኛ ዙር 1...
07/09/2026

‎ፈጣንና ጥራት ያለው ፍትህ በመስጠት የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ።

‎የሸካ ዞን ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት ሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤ የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና 2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም በጀት ላይ መክሯል።

‎የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ያቀረቡት የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ አስረስ እንደተናገሩት ተቋሙ ነፃ ገለልተኛና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በፍትህ ዘርፉ የህብረተሰቡን እርካታ በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

‎ፍርድ ቤቶች ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እውን መሆን ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው መሆኑን ገልፀው በበጀት ዓመቱ በሁሉም መዋቅሮች የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ጠቅሰዋል።

‎የዞኑን ፍርድ ቤት ተልዕኮ ለማሳካት ቁልፍ ተግባራትን አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም የተመዘገበው ውጤት የተሻለ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

‎ የተፋጠነ ፍትህ ለተገልጋዮች ከመስጠትና የውሳኔ ሰጪነትን ቅልጥፍና ማሳደግ ካለፈው በጀት ዓመት ሲነፃፃር ውጤቱ የተሻለ እንደሆነም አቶ ተሾመ ጠቅሰዋል።

‎በ2018 በጀት ዓመት ለፍርድ ቤቱ የቀረቡ መዝገቦችን መርምሮ ውሳኔ ከመስጠት አንፃር የተሻለ አፈፀፀም ማስመዝገቡን የገለፁት ኘሬዚዳንቱ በቀጣይም የፍትህ ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

‎በፍርድ ቤቶች ልዩ ትኩረት ከሚሰጥባቸው የሴቶችን ጥቃት ለመከላከልና ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ ውሳኔ እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎ፍትህን ለሁሉም ዜጋ ለማድረስ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶችንና ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን የማጠናከር ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

‎የዞኑ ፍትህ ጥምር ኮሚቴ ተግባራትን በቅንጅት ከመምራት አንፃር በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ በመፍታት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በቀረበው የዕቅድ አፈፃፀምና 2019 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከምክርቤቱ አባላት አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ጥምር ፍትህ ስርዓቱን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።

‎የፍርድ ቤት ተግባር የሁሉም ተቋማት የጋራ ተግባር በመሆኑ ለፍትህ ተግባር ሁሉም ተቋማት ድርሻውን መወጣት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

‎የችሎት ምልከታና ተቋማዊ ልምድ ልውውጥ በተቋሙ የሚሰሩትን ተግባራት አሰራሩን ለማዘመን የተሻለ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰዋል።

‎በፍርድ ቤቶች የተጀመረው ባህላዊ ዳኝነት ስርዓት የማጠናከር ስራ እያሳየ ካለው የተሻለ አፈፃፀም በሁሉም አካባቢዎች ለተግባራዊነቱ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎ህገወጥ የደን ወረራን ለመግታትና የደን ሀብቱን ለመጠበቅ ወንጀለኞችን የማስጠየቅ ስርዓት በትኩረት መመራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

‎የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም በጀት ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል ።

‎ ዘጋቢ: ነፃነት ኃይሌ

‎እየተተገበሩ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ የሚያሳዩ ብስራቶች በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተባለ።‎ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ በሸካ ዞን የሚመለከታ...
07/09/2026

‎እየተተገበሩ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ የሚያሳዩ ብስራቶች በመሆናቸው አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተባለ።

‎ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ በሸካ ዞን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ለውጦችንና በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ የልማት ስራዎችን በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

‎ባለድርሻ አካላቱ በሰጡት አስተያየት፣ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩ ሀገራዊ ለውጦች ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ጎዳና እየመሩ በመሆኑ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና በቀጣይም በተሻለ አፈጻጸም ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

‎ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተከናወኑ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የሚጠበቅባቸውን ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይም የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠቱ ከኢኮኖሚ ምንጭነት ባለፈ ለሀገር ኩራት የሆነ ታላቅ ስኬት ነው ብለዋል።

‎የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ዳግም የዓድዋ ድል ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ተጀምረው የተጠናቀቁና በሂደት ላይ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የእድገት ጉዞ የሚያበስሩ ውጤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎እነዚህ ሀገራዊ እንቅስቃሴዎች ከልማት በዘለለ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ለዜጎች ተጨማሪ የገቢና የሥራ ዕድል እየፈጠሩ በመሆኑ፣ የተጀመሩ ስራዎችን በቁርጠኝነት ማጠናከርና ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

‎በሌላ በኩል፣ በሀገሪቱ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ጉዳይ ላይ በራሳቸው ለመምከር ምቹ መደላድል መፍጠሩን ጠቅሰው፣ የመነጋገር፣ የመደማመጥና በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶችን የመፍታት ባህልን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እየተገበራቸው ያሉ የገጠር ሞዴል መንደር ግንባታ፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎችና ሌሎች የልማት ተግባራትም የሀገሪቱን ገጽታ እየቀየሩና የዜጎችን ክብር እያስጠበቁ መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል።

‎ኢትዮጵያ ከተረጂነትና ከጥገኝነት ተላቃ፣ በራስ አቅም የመቻልን እሳቤ በመከተል ራሷን በማልማት ብቻ ሳይወሰን ለሌሎች አገራትም ተምሳሌት ለመሆን የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል።

‎ዘጋቢ: ነፃነት ኃይሌ

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ “ህንግጫ” በዓል መከበር ጀመረ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋ...
07/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ “ህንግጫ” በዓል መከበር ጀመረ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ “ህንግጫ” በዓል በአመያ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

“ህንግጫ” የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች ካለፈው ዓመት በአለመግባባት፣ በጥላቻና በክፋት የተፈጠሩ ችግሮችን በእርቅ በመፍታት፣ በፍቅርና በሰላም አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት ባህላዊ እሴት የተላበሰ በዓል ነው።

“ህንግጫ” ሰዎች በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ ስሜት እና በአንድነት ወደ አዲሱ ዓመት የሚሸጋገሩበት የአንድነት፣ የእርቅና የሰላም በዓልም ጭምር ነው።

በክብረ በዓሉ የኮንታ ብሔርን ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚያሳዩ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት፣ ምግቦችና ሌሎች ባህላዊ ቁሳቁሶች ቀርበው የበዓሉ ታዳሚዎች የብሔሩን ባህላዊ እሴቶች በቀጥታ እየተመለከቱና እየጎበኙ ይገኛሉ።

በዓሉ የኮንታ ባህልና ማንነት የሚያንፀባርቁ ኩኔቶችና ባህላዊ ውዝዋዜዎች እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ማርች ባንድ አባላት ታጅቦ እየተከበረ የሚገኝ የበዓሉ አጠቃላይ ድባብም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) እና በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም የ“ህንግጫ” በዓልን አጠቃላይ ኩነቶች በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለተከታዮች በቀጣይነት የሚያደርስም ይሆናል።

በበዓሉ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ከአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የኮንታ ብሔር ተወላጆች፣ የኮንታ ወዳጆች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው።

‎የሸካ ዞን የ2019 በጀት ከ3 ቢሊዮን 963 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ።‎‎የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ሲሆን፣ የ20...
07/09/2026

‎የሸካ ዞን የ2019 በጀት ከ3 ቢሊዮን 963 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ።

‎የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ሲሆን፣ የ2019 በጀት ዓመት የዞኑን የበጀት ዕቅድ ከ3 ቢሊዮን 963 ሚሊዮን 971 ሺህ 924 ብር በላይ በማድረግ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

‎በጉባኤው በሁለተኛ ቀን ውሎ የቀረበው የበጀት ዕቅድ፣ ከምክር ቤት አባላት ሐሳብና አስተያየት በኋላ ነው የጸደቀው።

‎የሸካ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተግባሩ እንዳሻው እንደገለጹት፣ የተያዘው የገቢ ምንጭ ከመደበኛ ገቢ፣ ከጤናና ከትምህርት ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤቶች ገቢ እንዲሁም ከክልሉ መንግስት ድጎማ የተጠናቀረ ነው።

‎ይህም ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1 ቢሊዮን 458 ሚሊዮን 125 ሺህ 363 ብር ወይም በ63 ነጥብ 01 በመቶ የጨመረ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

‎በጀቱ ከጸደቀ በኋላ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር እርከኖች የተመደበላቸውን ሀብት በቅድሚያ ለህዝብ አገልግሎትና ለመንግስት ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች እንዲያውሉ ተጠይቀዋል።

‎ኃላፊው በተለይም የተመደበው ገንዘብ የወጪ ፍላጎትን በሚያሟላና ፍትሐዊነትን በጠበቀ መልኩ እንዲጠቀሙበት፣ በቁጠባም በመመራት የተጠቃሚውን ህዝብ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።

‎ዘጋቢ፡ ካሳሁን ደንበሎ

የዘመናት እንቅልፍ አብቅቷል፤ መሬት እና ማዕድን ለአገራዊ ብልጽግናበሀገር ልማት ውስጥ «አራቱ የኢኮኖሚ ሀብቶች» ወይም የምርት ማሳለጫዎች የሚባሉት ለየትኛውም ምርት እና አገልግሎት መፈጠር ...
06/09/2026

የዘመናት እንቅልፍ አብቅቷል፤ መሬት እና ማዕድን ለአገራዊ ብልጽግና

በሀገር ልማት ውስጥ «አራቱ የኢኮኖሚ ሀብቶች» ወይም የምርት ማሳለጫዎች የሚባሉት ለየትኛውም ምርት እና አገልግሎት መፈጠር መሠረት የሆኑት ዋና ዋና ሀብቶች ናቸው። ከእነዚህም ዋነኛው መሬት (Land) ሲሆን በውስጡ ማንኛውንም የተፈጥሮ ሀብት ያጠቃልላል። የሚታረስ መሬት፣ ደኖች፣ የውሃ አካላት እንዲሁም ወርቅና ነዳጅን የመሰሉ ማዕድናት በሙሉ በዚህ ሥር ይመደባሉ።

ይህንን ሀቅ ይዘን የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ጸጋ ስንመለከት አገራችን ከጥንታዊ ሥልጣኔዋ ጀምሮ በከርሰ ምድሯ ያቀፈችው የማዕድን ሀብት ለዘመናት ይህ ነው የሚባል የኢኮኖሚ እሴት ሳይፈጥር መቆየቱ በእጅጉ ያስቆጫል።

በማዕድን ዘርፉ ለዘመናት የነበረው ጉዞ ውጣ ውረድ የበዛበት ነበር። በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን በውጭ ኩባንያዎች ላይ ብቻ የተንጠለጠለ አሠራር፣ በደርግ ዘመን ሀብትን ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያደረገና በጦርነት የተስተጓጎለ ጉዞ እንዲሁም በኢህአዴግ ዘመን ለግል ባለሃብቶች በሩ ቢከፈትም ዘርፉ ለሀገራችን አጠቃላይ ምርት ያለው አስተዋፅዖ ከ0.8 በመቶ በታች ሆኖ የቆየበት ጊዜ ነበር።

ዛሬ ግን የመደመር መንግስት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሀብቱ በመሬት ውስጥ ተቀብሮ እንዳይቀር፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ትብብርን በማጠናከርና የዲጂታል ካዳስተር ሥርዓትን በመዘርጋት ዘርፉን ወደ ዘመናዊ የእሴት ሰንሰለትና የቴክኖሎጂ ሽግግር አድርሶታል።

በዚህ የእመርታ ጉዞ ውስጥ በወርቅ ገበያ ሪፎርም የተገኘው ውጤት የለውጡ ሞተር ሆኗል። ሕገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠርና የግብይት ሥርዓቱን በማሻሻል በተወሰደው ርምጃ ቀድሞ 100 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የነበረው ገቢ በማሳደግ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት ተችሏል። በዚህም የኩርሙክ፣ የቱሉ ካፒ፣ የሚድሮክ መተከልና የኤትኖ ማይኒንግ ግዙፍ ፕሮጀክቶችም ይህንን የወርቅ ምርት እመርታ ይበልጥ ወደ ላቀ ምዕራፍ እያሸጋገሩት ይገኛሉ።

ከወጪ ንግድ ባሻገር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ፖሊሲው ሌላው ትልቁ የእመርታ ማሳያ ነው። በዓመት ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ይወጣበት የነበረው የድንጋይ ከሰል በአርጆ ማቀነባበሪያና በሌሎች አራት አዳዲስ ፋብሪካዎች አማካኝነት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ችሏል።

በሲሚንቶ ኢንዱስትሪውም «ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ» ወደ ምርት በመግባት የሀገራችንን የሲሚንቶ ፍላጎት 50 በመቶ ሲሸፍን፣ የዳንጎቴ ሲሚንቶ የማምረት አቅሙን እጥፍ ለማድረግ እየሠራ ነው።

በግንባታና ሴራሚክስ ዘርፍም የባይጂያ እና የግራንድዩር ሴራሚክስ ፋብሪካዎች የተፈጥሮ ጋዝ ኃይልን ጭምር በመጠቀም ኢንዱስትሪውን እያዘመኑት ነው።

የኢኮኖሚ አቅምን በማሳደግ ረገድ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶች የፈጠሩት መነቃቃት እጅግ የጎላ ነው። በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ተፋሰስ የሚገኘው የካሉብ የፈሳሽ ነዳጅ ፕሮጀክት በመጀመሪያው ምዕራፍ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር እያመረተ ሲሆን በቀጣይ እስከ 1.33 ቢሊዮን ሊትር ለማድረስ እየተሠራ ይገኛል።

ከዚህም ጋር የ108 ኪሎ ሜትር የጋዝ ቧንቧ መስመር፣ የ1,000 ሜጋ ዋት የጋዝ ኃይል ማመንጫ እንዲሁም የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያና በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን የሚያመርተው የዳንጎቴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፕሮጀክቶች የዚህ እመርታ ተጨባጭ ፍሬዎች ናቸው።

በተጨማሪም እንደ ሊቲየምና ታንታለም ያሉ ወሳኝ ማዕድናት እንዲሁም ኤመራልድና ሳፋየርን የመሳሰሉ የጌጣጌጥ ድንጋዮችም ዓለም አቀፍ የገበያ ትኩረትን እየሳቡ ይገኛሉ።

ይህ ሁሉ ስኬት በዘፈቀደ የመጣ ሳይሆን ዘርፉን ከሚደግፉ የተጠናከሩ የመሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦትና የአካባቢ ጥበቃ ሪፎርሞች ጋር የተሳሰረ ነው። የዛሬው የእመርታ ጉዞ መነሻ እንጂ መድረሻ አይደለም፤ ማዕድንን ከመሬት ማውጣት ብቻ ሳይሆን ምርትን ወደ ኢንዱስትሪ፣ ኢንዱስትሪን ወደ ብልጽግና የመቀየር ሂደት ነው።

ልክ የዛሬዉ ጳጉሜን 1 አዲስ ተስፋን ሰንቆ ወደ አዲስ ዘመን እንደሚያሻግረን ሁሉ፣ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍም የተፈጥሮ ሀብትን በእውቀትና በቴክኖሎጂ አዋህዶ የዜጎችን ሕይወት ወደሚቀይርበት እውነተኛ የእመርታ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

Address

Sheka Zone
Masha
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sheka TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category