
25/10/2022
ስለ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከክፍል አንድ የቀጠለ....
የሳባታሚት ቆይታችንና ትዝብታችን:-
👇👇👇👇👇👇
እነርሱን ለመጠየቅም ብቻ ሳይሆን የራሱን ሰው ከጠየቀ በኃላ ወደ እርሱ ጎራ የሚለውና አይዞህ የሚሉት የሰው ብዛት ቁጥር ስፍር የለውምና በነፃነት ለመጨዋወት ይከብዳል ከ 5 እስከ 90 ዓመት ሞለክሴ እየመጡ አይዞህ በርታልን ይሉታል ህፃናቶች በፍቅር እንደ ወጉ ጉልበት ይስማሉ ህፃናቶቹ በመገረም አይን ከላይ እስከታች ይገላምጡታል ቆይ ሳድግ ልክ እንዳንተ ነው በሚል አስተያየት ይመስላል ተገርመው ያዩታል::
ምን አይነት የሰው ፍቅር ነው?
ውጪ ህዝቡ ለልፋቱ ከከፈለው ውለታና ዋጋ በላይ በጥቂት በእስር በሚገኝባቸው ጊዜያቶች ለመክፈል የወሰነና የቆረጠ ይመስላል:: እርሱም ምን ያህል የህዝብ ልብ ውስጥ እንዳለ እና የአማራ ሕዝብ የትግል ምልክት እንደሆነ እንዲያውቅና እንዲሁም ሃሳቡን ምን ያህል እንደሸጠ እንዲረዳቸው ዘመነነት ከግለሰብም አልፎ አስተሳሰብ እንደሆነ ለማሳየት በሚመስል መልኩ ከየአቅ ጣጫው በፍቅርና በክብር በሚመጡ እግሮች እየገለፁለት ለቀጣ ይ ትግሉ ትልቅ የቤት ስራ እየሰጡት ይሄዳሉ::
አንድ በጣም ልባችንን የነካንን ነገር እናጫውታችሁ እንዳልኳቹሁ ከልጅ እስከ አዋቂ ፍቅሩን እየገለፀ ያለውን ሳንቲም እንደ አቅሙ ለሻይ እያለ የፍቅሩን መገለጫ እያስጨበጠው ይሄዳል በዝህ መሃል እድሜው ገና 14-15 የሚሞላው አንድ አዳፋ ፎጣ የለበሰ ብላቴናና የቆሎ ተማሪ የሚመስል ሌሎች ሲሰጡ አይቶ እርሱም ያለችውን ሁለት አስር አስር ብር ሃያ ብር አስጨብጦት ሄደ እንባ ተናነቀንና ድንገት እርስ በእርስ መተያየት ጀመርን ዝምታውም ሰፈነ እንደ ምንም ስሜታችንን ተቆጣጥረን ዘሜ እስካሁን ከመጣህበት መንገድ የቀጣዩ ይበረታብሃልና ለከባዱ ሃላፊነት ራስህን አዘጋጀው አልነው::
ይህ ሁሉ ሰው ከሰላምታ ጀምሮ መልካም ምኞቱን እንዲሁም ያለውን ስባሪ ሳንቲም እንደ አቅሙ እያደረገ ያለው አንተ ቸግሮህ ወይም እርዳታቸውን ጠይቀህ ወይም ፈልገህ ሳይሆን ብቸኛውና መዳኛው መንገድ አንተና የአንተ አስተሳሰብ መሆንህን ስለተረዳ በርታልን ከጎንህ ሚሊዮኖች አለን እያሉህ ነው እና አደራ ይህንን ህዝብ ነፃ ሳታወጣ ጉልበቶችህ እንዳይዝሉ ስንለው "ጏዶች እመ ኑኝ ቅድምም እንዳልኳቹሁ ላንጨርስ የጀመርነው አንዳች ትግል የለም ዘመነን በማሰር የሚቀጣጠል ትግል እንጂ የሚቀዛቀዝ ትግል አልጀመርነውም እርምጃችን አንዴ አስር አንዴ አምስት አንዴም አንድ ሊሆን ይችላል እንጂ ሁሌም ወደፊት ብቻ ነው ብቻ እናንተ በርቱልኝ ብሎ ሌላ ተስፋና አደራ እንዲሁም ኃላፊነት አሰነቀን::
በትግል ጏዶቹ ተከ*ዳ በሚለውና ተያዘ በተባለበት ዙሪያ በአንዳ ንድ ሚዲያ ላይ በተለቀቁት ውዥ*ንብሮች ጉዳይ እንዲሁም በእ ስር*ቤት ስላለው ጉዳይ በመጨረሻውና በክፍል ሦስት ይጠብቁን.....