
12/06/2025
Can't wait
ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ!
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በዘማሪ አቤንኤዘር ፈቃዱ የተዘጋጀውን ቁ. 2 [እጠጋለሁ ወዳንተ] የዝማሬ አልበም ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን በኩል ለራሱ ክብር እና ለቅዱሳን መታነጽ በሚሆኑ የዝማሬ ጸጋን ጨምሮ በተለያየ ጸጋ እየባረከ ስላለ እጅግ ደስ ይለናል።
በዚህ አድካሚ የዝማሬ አልበም መዝሙሮቹን ተቀብሎ በስጦታ ለቤተክርስቲያን ያበረከተውን ዘማሪ አቤንኤዘር ፈቃዱን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርክ ጸሎታችንም ምኞታችንም ነው።
አልበሙ በቅርብ ቀናት ውስጥ በApostolic Songs መተግበሪያ ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬዎቹን በተለያዩ የግዢ አማራጮች በማውረድ ጸጋውን፣ ቤተክርስቲያንን እና አገልግሎቱን ትደግፉ ዘንድ በኢየሱስ ፍቅር እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል
ሰኔ 2017 ዓ.ም