23/08/2025
ከመንግስት ተጨማሪ ነገር ከመጠበቅ የራስን ተጨማሪ ገቢ ማፈላለግ በሚለው ቢታይ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
የመንግስት ሰራተኛውና የደመወዝ ጭማሬው ቁጥራዊ ስሌት!
ጀማሪ የድግሪ ደመወዝተኛ - ''ከለውጡ'' ማግስት እስከ ''ማክሮ ኢኮኖሚክ ማሻሻያው'' ቁጥራዊ ንፅፅር!
''ለውጡ'' እያሉ ከሚጠሩት 'የፍዳ-ዘመን' ጅማሮ ማግስት 6940 ብር የድግሪ መነሻ ደመወዝ የሚከፈለው ሰራተኛ 25% የስራ ግብር ፣ 7% የጡረታ በድምሩ 32% ብቻ ተቀናሽ ተደርጎለት ( 15% ዝቅተኛ 35%ከፍተኛ ግብር አማካኝ ወስደን ነው!) ፣ የተጣራ 4719 ብር ይደርሰዋል። ይህም በወቅቱ የ1 ዶላር ዋጋ 20 ብር ገደማ ስለነበር ፣ ለሰራተኛው 235 የአሜሪካ ዶላር ወርሀዊ ደመወዝ ይከፈለው ነበር።
11500 ብር የድግሪ መነሻ ደመወዝ የተባለው በ2017 ዓ.ም ወርሀ ነሀሴ ተግባራዊ ቢደረግ ፣ 25% የስራ ግብር ፣ 7% የጡረታ በድምሩ 32% ብቻ ተቀናሽ ተደርጎለት ፣ ለሰራተኛው የተጣራ 7820 ብር ይደርሰዋል። ይህም በዛሬው ተመን በብላክ ሳይሆን በባንክ የ1 ዶላር ዋጋ 140 ብር ገደማ ስለሆነ ፣ ለሰራተኛው 55.8 የአሜሪካ ዶላር ወርሀዊ ደመወዝ ይከፈለዋል ማለት ነው። መነሻው ደመወዙን ምንም ሳይቆራርጡ በእጁ ቢሰጡት እንኳ ደመወዙ 82 ዶላር ብቻ ነች!
ይህ ጀማሪ የድግሪ ሰራተኛ ያኔ ከአመታት በፊት ይከፈለው ወደነበረው የተጣራ 235 ዶላር ለመመለስና በዚያ ደረጃ ለመኖር 235 ዶላር ×140 ብር = 32,900 ብር የተጣራ ደመወዝ በወር መከፈል ይኖርበታል ማለት ነው!
በብላክ ማርኬት ካሰላነው ጭራሽ ደመወዙ እንደጨው ሟሙታ 40 ዶላርም አትደርስም! አሁናዊው Hyperinflation እና የደመወዝ ጭማሬውን ተከትሎ የሚመጣውን ግሽበት ስናስበው ''ተጨማሪ ደመወዝ'' ሳይሆን '' ተጨማሪ ስጋት '' ማለቱ ይቀላል!
ልጓሙን በጥሶ ከቁጥጥር ውጪ የወጣውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርአትና አሳሳቢውን የዋጋ ግሽበት መግታት ካልተቻለ ፣ መንግስት አይደለም በአምስትና ስድስት አመት በየቀኑ ደመወዝ ቢጨምርም እንኳ የሰራተኛውን ህይወት ፈፅሞ አያሻሽለውም!😥
ተከታዩ ቁጥራዊ መረጃ ደግሞ #ሙሼ #ሰሙ የደመወዝ ጭማሬውን በማስመልከት በፌስቡክ ገፁ ያጋራው ነው!
መንግስት በአዲሱ የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት ለ160 ቢለየን ብር ተጨማሪ ወጭ እንደሚዳረግ ገልጿል። እስኪ የጭማሪውን ፋይዳ ለመረዳት ቁጥሮችን በአንጻራዊ ስሌት እናጢናቸው።
ቋሚ ደሞዝተኛው ገንዘቡ ኪሱ ከመግባቱ በፊት በገቢ ግብር ምክንያት ዝቅተኛው ተከፋይ 15% ከፍተኛው ደግሞ 35% ይቆረጥበታል። ዝርዝሩ ውስጥ መግባት ስለሚያዳግት አማካዩን ቁጥር እንወሰድ።
አማካዩ (15+35)/2 = 25% ይሆናል። ወደፊት እድሜውና ጤናው ከፈቀደለት የጡረታ ተከፋይ የሚያደርገው ቢሆንም ዛሬ ላይ ለጡረታ 7% ከደሞዙ በቀጥታ ይቆረጥበታል። 25%+7% = 32% ይሆናል።
160,000,000,000*0.32= 51,200,000,000 ይሆናል። ይህ ማለት ሃምሳ አንድ ቢሊየን 200 ሚሊየን ብር የደሞዝ ጭማሪው ተቀጣሪው እጁ ከመድረሱ በፊት ወደ መንግስት ካዝና ይመለሳል። በደሞዝ መልክ የሚከፋፉለው ቀሪ 108,800,000,000 ብር ይሆናል።
ደሞዙ እጁ ላይ ከገባ በኋላ ደግሞ በሚሸምተው ቁሳቁስና በሚገዛው አገልግሎት ላይ 15% ቫት ይከፍላል። 108,800,000,000 *0.15 = 16,320,000,000 ይሆናል።
ይህ ማለት ደግሞ ከ160 ቢሊየን ብር ጭማሪ ውስጥ ደሞዝተኛውን ሳያገለግል በገቢ ግብር፣ በጡረታና በቫት ብቻ ወደ መንግስት ካዝና ተመልሶ የሚገባው ብር 67,520,000,000 ሲሆን ጭማሪው ደግሞ 92,480,000,000 ብር ይሆናል።
በመቀጠል ቀሪዎቹን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የግብር ዓይነቶች