
02/07/2025
💯ፍቅርን ሳታውቁ ትዳርን እንዳታስቡ….✍🏽
✅ላወቀበት ሰው ትዳር የመንግስተ ሰማያት መግቢ በር ነው።የትዳር መሰረቱ ፍቅር ሲሆን የፍቅር ባለቤቱ ደግሞ ፈጣሪ ነው። ፍቅርንና ትዳርን የሚሰጥ ፈጣሪ ሲሆን አክብሮ መያዝ ግን የእኛ ነው።ፈጣሪ ለሰው ልጆች ክቡር ፍጡር የሆነውን ሰውን ነፍስን ከነ ሙሉ አካሉ በስጦታነት ሲሰጠን በፍቅር ተንከባክበን፣አክብረንና ተጠንቅቀን መያዝ ግደታ አለብን።
✅ስለሆነም ፈጣሪ ሩህሩህ አምላክ ነውና ሁሉን በህግና ስርዓት እንደንመራ ፍቅርን እንደት ማክበር እንዳለብን በመፅሀፍ ቅዱስ 1 ቆሮንቶስ 13 ጠቅሶ ስለ ፍቅር እንደሚከተለው አስተምሮናል።አንብባችሁ ተጠቀሙበት..✍🏽
“1) በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።
2) የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ ምስጢርን ሁሉና ዕውቀትን ሁሉ ባውቅ፣ ተራራንም ከቦታው የሚነቅል እምነት ቢኖረኝ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
3) ያለኝን ሁሉ ለድኾች ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት ብዳርግ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
4) ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤
5) ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።
6) ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።
7) ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።
8)- ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።
9) ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምንናገረውም በከፊል ነው።
10) ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል።
11) ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር።ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ።
12) አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤በዚያ ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያ ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።
13) እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው!!”
💯ፍቅርን ኑሩት እንጅ አታስመስሉበት!!
✅ሁሉም ሰው ያውቀው፣ይረዳውና ይማርበት ዘንድ ሸር አድርጉት!!🫶🏽🕊️
እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን🙏እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።
©️Zelalem Teshome