
04/04/2025
#ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆሞ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ ኢንጅነር አግኝተው እንዲሰራው ቀጠሩት።
#ኢንጅነሩም ሞተሩን ከታች እስከላይ ከገመገመ በኋላ አነስ ያለች የእቃ ቦርሳውን ከፍቶ ትንሽዬ መዶሻ አወጣ፣ ከዛም በጥንቃቄ በመዶሻው አንዷን ስፍራ መታ መታ አረገና ሞተሩ መስራት ጀመረ።
#ከሳምንት በኋላ የሰራበትን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ሪሲቱን ሰጠው።
"ምን" አለ ባለቤቱ ጭንቅላቱን ይዞ ምን ሰርተህ ነው ይሄን ያህል ብር የምትጠይቀኝ በል ምን እንደሰራህ ዝርዝሩን ጽፈህ ስጠኝ አለው ተናዶ።
#በቀላሉ እንዲህ ጽፎ ሰጠው
በመዶሻ የመታሁበት 200 ብር
የተበላሸበትን ቦታ ላወኩበት ደግሞ 999800 አለው።
#ይሄን ስራ በ30 ደቂቃ ውስጥ ነው የሰራውት ላለፉት 20 አመታት እንዴት በ30 ደቂቃ መስራት እንዳለብኝ ተምሬ ነው፣ የማስከፍልህ ለተማርኩበት አመታት እንጂ #ለሰራውበት ደቂቃ አይደለም አለው ይባላል።
ሁሉም ውጤት የእረጅም ጊዜ ልፋት ነው።