Benc' Unity Media Network

Benc' Unity Media Network Benc' max At Dubd The main goal is to preserve the unity of our people and work on the culture, traditions, and customs of our nation.

In addition, it is an association established to ensure the overall benefit of our nation.

28/09/2026

የቤንች ባህላዊ የሀዘን መግለጫ በጥቂቱ ተመልከቱ፤
ባህላችን የማይጠገብ ብዙ ያለተነገረለት ድንቅ ነው።
ከአዋቂ እስከ ህፃናት የለቅሶ ስራአት አለው።

የቤንች ብሔር የአንድነትና የምስጋና አውደ ዓመት "ቢስት ባር"“ቢስት ባር” የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል። ከጥንት ዘመን ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ፣ የቤን...
27/09/2026

የቤንች ብሔር የአንድነትና የምስጋና አውደ ዓመት "ቢስት ባር"

“ቢስት ባር” የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል። ከጥንት ዘመን ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ፣ የቤንች ሕዝብን ታሪክ፣ ባህል፣ እሴትና ማንነት በሙሉ የሚያንጸባርቅ ታላቅ ሕዝባዊ በዓል ነው።

ቢስት ባር በዓመት አንድ ጊዜ የሚከበር በዓል ብቻ አይደለም፤ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ቤተሰብን ከቤተሰብ፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያገናኝ የአንድነት ድልድይ ነው። ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክር፣ የጋራ መተሳሰብን የሚያድስና የማኅበረሰቡን አንድነት የሚያጸና ባህላዊ መድረክ ነው።

1️⃣ቢስት ባር የምስጋና በዓል፣ የምርት በዓል

ቢስት ባር አርሶ አደሩ ዓመቱን ሙሉ የደከመበትን፣ በጉልበቱና በትጋቱ ያፈራውን የበኩር ምርት በጋራ የሚቀማመስበት ታላቅ የምስጋና ዕለት ነው። የምድር ለጋስነትን፣ የፈጣሪን በረከትና የሰው ልጅን ጥረት በአንድ ላይ የሚያወድስበት የምርት በዓል ነው።

በዓሉ ሲከበር የጎሳ መሪዎች፣ ታላላቅ አባቶችና መንፈሳዊ መሪዎች የዓመቱን ምርት አስመልክተው ምርቃትና ምክር ይሰጣሉ። እያንዳንዱ አባወራ ያመረተውን ምርት ለብቻው አይቀምስም። ቤተሰቡን፣ ጎረቤቱንና ታላላቅ አባቶችን ይጋብዛል። ታላላቆች ቀድመው በመቅመስ ለፈጣሪ ምስጋና እንዲያቀርቡና ለቀጣዩ ዘመን በረከት እንዲመኙ ይደረጋል። ከታላላቆች ምርቃት በኋላ እናቶችና ልጆች እንደየዕድሜያቸው በተራ ይቀምሳሉ።

ይህ ሥርዓት በቤንች ባህል ውስጥ ለአባቶችና ለታላላቆች የሚሰጠውን ከፍተኛ ክብር በግልጽ ያሳያል። ልጆች አባታቸውን፣ ሚስት ባሏን፣ ታናናሾችም ታላላቆቻቸውን “ይንቲ” ብለው የመጥራትና የማክበር ግዴታ አላቸው። ይህ “አንቱነት” ጾታን ሳይለይ ለሰው ልጅ በክብር የሚሰጥ እሴት ሲሆን፣ መነሻውም ከቢስት ባር ሥርዓት ጋር የሚያያዝ ባህላዊ እሴት ነው።

2️⃣ከቢስት ባር ዋዜማው እስከ ዋናው የበዓሉ ዕለት

የቢስት ባር ዋና አከባበር በጥር ወር ቢሆንም፣ ዋዜማው ከምርት ከማሳ መሰብሰብ ወቅት፣ ከኅዳር ወር ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ማብቂያ ድረስ በተለያዩ ኩነቶችና ሥነ-ሥርዓቶች ይከበራል። የአከባበሩ ሥርዓትም በሁለት ዋና ዋና ደረጃዎች ይከናወናል።

1.የመጀመሪያው ቀን፦የቤንች መነሻ በታሪካዊው ዣዥ ይከበራል

የመጀመሪያው የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት በሼይ ቤንች ወረዳ፣ “ዣዥ” በተባለውና የቤንች ብሔር በቀዳሚነት የሰፈረበት ታሪካዊ ስፍራ ይከበራል።

በዚህ ታሪካዊ ስፍራ የቤንች ብሔር የነገድ መሪዎች ቤንችቴት፣ ሼይቴትና ሜርቴት በተገኙበት ለፈጣሪ ምስጋና ይቀርባል። ለቀጣዩ ዘመን እርሻው እንዲባረክ፣ ምርት እንዲበዛ፣ በሽታና ጦርነት እንዲርቅ፣ ሰላምና በረከት እንዲሰፍን ምኞትና ልመና ይቀርባል።

2.ሁለተኛው ቀን ፦ በኮሚትኬስ ማስታወሻ በአማን ሜዳ ፤ በቢስት ባር ሜዳ ይከበራል

ሁለተኛውና ዋናው የበዓሉ ክብረ በዓል በሚዛን አማን ኮሚትኬስ የቀድሞ አየር ሜዳ በቢስት ባር ሜዳ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
በዚህ ታላቅ የባህል መድረክ የነገድ መሪዎች ቤንችቴት፣ ሼይቴትና ሜርቴት፣ መላው የቤንች ብሔር አባላት፣ የከተማው ማኅበረሰብ፣ ከአጎራባች ብሔረሰቦች የሚመጡ እንግዶች ካፋ፣ ሸካ፣ መኤንት፣ ዲዚ እና ሌሎችም እንዲሁም የመንግሥት አመራሮች በአንድ ላይ ይገኛሉ። ይህም ቢስት ባር የአንድ ብሔር በዓል ብቻ ሳይሆን፣ የሕዝቦች ወዳጅነትና አብሮነት መገለጫ መሆኑን ያሳያል።

3️⃣ቢስት ባር የታሪክና የትውልድ አሻራነት

ቢስት ባር ለቤንች ሕዝብ የሥልጣኔ፣ የታሪክ፣ የባህልና የትውልድ አሻራ ነው። በጥንት ዘመን በስፋት ይከበር የነበረው ይህ በዓል በመሃል በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል።

ሆኖም መንግሥት ብሔረሰቦች ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ማንነታቸውን እንዲያሳድጉና እንዲያስቀጥሉ በሰጠው መብት መሠረት፣ በ2016 ዓ.ም የቢስት ባር ዳግም ንቅናቄ ተፈጥሮ በድጋሚ መከበር ጀመረ። ይህም የተቋረጠውን የባህል ትስስር ለመመለስና የትውልድ አሻራን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ እርምጃ ነው።

4️⃣ቢስት ባር የሰላም፣ የፍትሕና የእኩልነት መገናኛ

ቢስት ባር የቤንች ብሔር አንድነትን ከማጠናከር ባለፈ፣ ሰላምን፣ ፍትሕንና እኩልነትን የሚያበረታታ ባህላዊ መግባቢያ ነው።

በዓሉ ያለፈውን ዓመት መጥፎነት እና ጥሩነገሩን በመመዘን ለቀጣዩ ዘመን የሚያስፈልጉ ጥሩ እሴቶችን የሚያጠናክርበት የምክክር መድረክም ነው። ትጉ አርሶ አደር የሚሸለምበት፣ ስንፍና የሚወገዝበት፣ ማኅበረሰቡም ለቀጣዩ ዓመት የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚነሳሳበት የጋራ መድረክ ነው።

5️⃣የቢስት ባር ማኅበራዊ ፋይዳው

የቢስት ባር ማኅበራዊ ፋይዳ እጅግ ሰፊ ነው። ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር በወንድማማችነት አብሮ መብላትና መጠጣት የሕዝቦችን ትስስር ያጠናክራል። ወጣቶች የሚተዋወቁበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ችግረኞችና አቅመ ደካሞች የሚደገፉበት አጋጣሚ ይፈጥራል።

በዚህም በዓሉ ማኅበረሰቡን ከማዝናናት ባለፈ፣ የመተሳሰብ፣ የመቻቻል፣ የይቅር ባይነትና የጋራ ኃላፊነት እሴቶችን ያድሳል።

6️⃣የቢስት ባር የምጣኔ ሀብት ፋይዳ

ቢስት ባር የባህል በዓል ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴንም የሚያነቃቃ የገበያ መድረክ ነው። ጤፍ፣ ስንዴ፣ አይቢ፣ ከቺና፣ ማርና ሌሎች የአካባቢው ምርቶች ለቅምሻ ይቀርባሉ። ጥንታዊ ዕደ-ጥበባት፣ ቡናና ቅመማ ቅመሞችም ለገበያ ቀርበው የአርሶ አደሩንና የአምራቹን ገቢ ለማሳደግ ያግዛሉ።

ከዚህ በላይ ቢስት ባር እንደ ቱሪስት መስህብ በሚገባ ተደራጅቶ ከተሠራበት፣ ለአካባቢው ሕዝብ ትልቅ የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ የቤንች ባህልን ለሀገርና ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ አቅም አለው።

7️⃣የቢስት ባር የኪነ-ጥበብና የባህል ድምቀት

ቢስት ባር ወጣቶች ፣ እናትና አባቶች በአደባባይ ተውቦና ተጊጦ የሚከበር የኪነ-ጥበብ መገለጫም ነው። ቤቶች በደማቅ ቀለማት ተቀብተው ይዋባሉ፤ ወጣቶችም በባህላዊ የጸጉር አሠራርና በባህላዊ አልባሳት ደምቀው በበዓሉ ይሳተፋሉ።

የባህላዊ ዘፈን፣ ጭፈራ፣ አልባሳትና ሌሎች የኪነ-ጥበብ መገለጫዎች የቤንች ብሔርን የበለጸገ ባህላዊ ሀብት ለማሳየት ዕድል ይፈጥራሉ። ይህም ወጣቱ ትውልድ የቀደሙትን ባህላዊ እሴቶች እንዲያውቅና እንዲጠብቅ ያግዛል።

8️⃣ቢስት ባር የአዲስ ዘመን አዲስ መንፈስ

ቢስት ባር ከባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳው ባለፈ የሥነ-ልቦና ጠቀሜታም አለው። ማኅበረሰቡ ያለፈውን ዓመት ቂም፣ ቅራኔና አለመግባባት ትቶ በአዲስ ተስፋና በአዲስ መንፈስ ዘመኑን እንዲጀምር ያበረታታል።

ለጋስነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ መቻቻልንና ሰላምን ያስተምራል። በተቃራኒውም እንደ ሌብነት፣ ስንፍናና ውሸት ያሉ ማኅበራዊ ደዌዎችን ያወግዛል። በዚህም ማኅበረሰቡ ካለፈው ዓመት ልምድ በመማር ወደ አዲሱ ዘመን በተሻለ መንፈስ እንዲሸጋገር ያግዛል።

9️⃣ቢስት ባር የቤንች ማንነት ሕያው ምስክር ነው

ባጠቃላይ፣ ቢስት ባር የቤንች ብሔርን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና የጋራ እሴቶች በሙሉ የሚወክል ሕያው የባህል ቅርስ ነው። የምስጋና በዓል ነው፤ የምርት በዓል ነው፤ የአንድነት በዓል ነው፤ የሰላምና የዕርቅ መድረክ ነው፤ የትውልድ ቅብብሎሽ መስክ ነው።

ከቤንች ብሔር ድንበር ባለፈም የያዘው ሰብዓዊ እሴት ለሰው ልጅ ሁሉ የሚጠቅም ነው። እርስ በርስ መከባበር፣ በጋራ መብላት፣ ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረብ፣ ታላላቆችን ማክበር፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ ደካሞችን መደገፍና ለአዲስ ዘመን በአዲስ ተስፋ መነሳት እነዚህ ሁሉ ከዘመናት በፊት የተወረሱና ዛሬም ዋጋቸው ያልቀነሰ ሰብዓዊ እሴቶች ናቸው።

ስለዚህ ቢስት ባርን ማክበር ያለፈውን ብቻ ማስታወስ ሳይሆን፣ ለወደፊቱ ትውልድ የሚተላለፍ ባህላዊ ውርስን መጠበቅ ነው። ማስተዋወቅም የቤንች ሕዝብን ታሪክና ማንነት ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፣ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመቻቻልና የምስጋና እሴቶችን ለዓለም ማካፈል ነው።

በዚህ ሁሉ ምክንያት “ቢስት ባር” እንደ አንድ ታላቅ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ በተገቢው ሊጠበቅ፣ ሊመረመር፣ ሊመዘገብና ለቀጣዩ ትውልድ ሊተላለፍ የሚገባው የቤንች ብሔር ታላቅ የባህል ሀብት ነው።

በተጨማሪም ባህላዊ እሴቱ፣ ማኅበራዊ ፋይዳውና የቱሪዝም አቅሙ በሚገባ ተጠንቶ ለዓለም የባህል ማህበረሰብ እንዲተዋወቅ ማድረግ ይገባል።

Benc' Unity Media Network

፣ ፣ !

የቤንች ማጥ-አት ሲቪክ ማህበር የመስቀል እና የደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትእንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!የመስቀል እና የደመራ በዓል...
26/09/2026

የቤንች ማጥ-አት ሲቪክ ማህበር የመስቀል እና የደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የመስቀል እና የደመራ በዓልን ስንቀበል በየማኅበረሰቡ የሚደረገው ዝግጅት የእምነት፣ የባህልና የማኅበራዊ አንድነታችን ህያው መግለጫ ነው። እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታና አቅም የሚዘጋጁት ደመራዎች አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በዓሉን ጠረን እንዲላበስ የሚያደርጉ ሲሆን፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ የደስታና የተስፋን ብርሃን ይፈነጥቃሉ። ከታላላቅ የሕዝብ አደባባዮች እስከ መንደሮች ድረስ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁት እነዚህ ደመራዎች የሕዝባችንን የጠበቀ ትስስር እና አብሮነት በግልጽ ያሳያሉ።

በዚህ የቤንች ማጥ-አት ሲቪክ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አብርሃም ታደሰ በመልዕክታቸው "የመስቀል ደመራ በዓል የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ እና የአብሮነት በዓል ነው። እኛም የቤንች ማጥ-አት ማህበር በተለይ ሕዝቦች ባህላዊ እሴቶቻችውን ጠብቀው በማክበር አብሮነትን በማዳበር፣ በአንድነትና በፍቅር ለአካባቢያችን እና ለአገራችን ዕድገት እንድንተጋ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ፤ መልካም በዓል!" በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል።

የደመራ በዓል አከባበርና አካባቢው የተላበሰውን ውብ ድምቀት ይበልጥ በመጋራት የበዓሉን ፍስሐ አብረን እናክብር።

መልካም በዓል!

የቤንች ማጥ-አት ሲቪክ ማህበር

23/09/2026

ማሽቃሮ በቦንጋ ከተማ በንጉሥ ሜሪቴት በዚህ መልኩ ደምቋል!!

የቤንች ህዝብን ክብርና ማንነት ለነካ ድርጊት አፋጣኝ ህጋዊ ምላሽ ይሰጥ!​አቤል ጥላሁን የተባለው ግለሰብ በታላቁና በክቡሩ የቤንች ህዝብ ላይ የፈፀመው አስጸያፊና ጸረ-ህዝብ ተግባር በፍጹም ...
21/09/2026

የቤንች ህዝብን ክብርና ማንነት ለነካ ድርጊት አፋጣኝ ህጋዊ ምላሽ ይሰጥ!

​አቤል ጥላሁን የተባለው ግለሰብ በታላቁና በክቡሩ የቤንች ህዝብ ላይ የፈፀመው አስጸያፊና ጸረ-ህዝብ ተግባር በፍጹም ተቀባይነት የሌለውና የሚወገዝ ነው።

ቤንች ማጥ-አት ማህበር (Benc' Unity Media association) የተቋቋመው የቤንችን ህዝብ አንድነት፣ ከባቢያዊ እሴቶች እና ታሪካዊ ማንነቱን ለማስከበርና ለማስተዋወቅ በመሆኑ፤ ይህንን ህዝብ ያዋረደና የነካ ፀያፍ ድርጊት አበክሮ ያወግዛል።

​የሚመለከተው የህግ አካል ግለሰቡን በአፋጣኝ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉ የተሰማ ቢሆንም፣ ይሄ የከፋ የድፍረት ተግባር የህዝብን ሞራል የሚፈታተን በመሆኑ ዳኝነቱ ግልጽና ህዝባዊ መሆን አለበት።

​ኢትዮጵያዊያን የተከበሩባቸውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሁም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መብቶችን የሚመለከቱ ህጋዊ ማዕቀፎች ግለሰቡ በፈፀመው ፀረ-ህዝብ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆንባቸውን አግባቦች በግልጽ አስቀምጠዋል።

​የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ-መንግስት (አንቀጽ 29 እና 39) ማንኛውም ዜጋ የመናገርና ሃሳብን በነፃ የመግለጽ መብት ያለው ቢሆንም፣ ይህ መብት የሌሎችን ሰብአዊ ክብር፣ መልካም ስም፣ ሰላም እና የህዝብንሞራል ማክበር እንዳለበት ይደነግጋል። እንዲሁም የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ማንነታቸውን የማስከበር፣ የማዳበርና የማስተዋወቅ መብታቸው በህገ-መንግስታዊ ዋስትና የተጠበቀ ነው።

​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህገ-መንግስት የክልሉ ህዝቦች አብሮነት፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ክብር በማንኛውም መልኩ እንዳይነካና በህግ ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል።
​
በማንኛውም ህዝብ ወይም ማህበረሰብ ላይ ጥላቻን የሚቀሰቅስ፣ ብሔርን መሰረት አድርጎ የሚያዋርድ፣ የሚሰድብ ወይም የቡድኑን ክብር የሚነካ ፀያፍ ተግባር የሚፈጽም አካል በወንጀል ህጉ መሰረት በቡድን ስድብ፣ የክብር ንክኪ እና የህዝብን ሰላም ማወክ ወንጀሎች ተከሶ አስተማሪ እና ጠንካራ የህግ ቅጣት ሊቀበል ይገባል።
​
​ህዝባችን እንደዚህ አይነት ፀያፍ ድርጊቶች ዳግመኛ እንዳይደገሙ እና ሞራላቸው የተጎዳው የቤንች ህዝቦች ይፋዊ እውቅና አግኝተው አስተማሪና ጠንካራ ህጋዊ ቅጣት በሰዳቢው ላይ እንዲወሰን አበክረን እንጠይቃለን።

​የፀጥታ አካላትና የሚመለከታቸው የህግ አስፈፃሚዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አፋጣኝ እና ግልጽ ምላሽ እንዲሰጡን እንጠይቃለን!

​


Benc' Unity Media Network
አንድነት ሀይል ነው!!

በቅርቡ ማህበራችን ሚዲያ ተደራሽነቱን ለእናንተ ለተመልካች የጋራ ዕሴት የሆኑ ባህልን፥ወግን፥ ዕሴትን እና ጥበብን በተመለከተ በመለጠፍ ወደ እናንተ በማድረሱ ወድዳችሁ ወዳጅነታችሁን በመግለፅ ...
20/09/2026

በቅርቡ ማህበራችን ሚዲያ ተደራሽነቱን ለእናንተ ለተመልካች የጋራ ዕሴት የሆኑ ባህልን፥ወግን፥ ዕሴትን እና ጥበብን በተመለከተ በመለጠፍ ወደ እናንተ በማድረሱ ወድዳችሁ ወዳጅነታችሁን በመግለፅ ላሳያችሁን መልካም በጎ ተፅኖ በማህበሩ ስም ከልብ እናመሰግናለን! share &like & follows በማድረግ 3k_5k በቅርቡ እንደምታደርሱን እናምናለን!!

19/09/2026

ባህል ማለት የማንነት መግለጫ ሲሆን ትውልዱ የጥንቱን የአባቶቹን ባህል፣ እሴት እና ስነ-ምግባር የሚማርበትና ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍበት ህያው መድረክ ነው።
#ቤንች #ሚዛን #አማን
fans Benc' Unity Media Network

ባህላችን ውበታችን ነው!!
19/09/2026

ባህላችን ውበታችን ነው!!

19/09/2026

ደንቢ 14/05/2018 ዓ.ም የሚያስፈልገንን በዚህ መልኩ ከአደራ ጋር ተሰጥቷል።

Address

Mizan-Aman
Mizan Teferi
5140

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benc' Unity Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share