03/10/2026
በጣም አስቸኳይ የትራፊክ አደጋ እና የእርዳታ ጥሪ‼
ዛሬ ጧት ከአዲስ አበባ ወደ ሚዛን ሲጓዝ የነበረ «ዋልያ ባስ» የህዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ «አዋሽ በሎ» ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 51 ሰዎችን ይዞ በመገልበጡ አሰቃቂ አደጋ ደርሷል።
በስልክ በተገኘ መረጃ መሠረት፡
በአደጋው አሁንም በመኪናው የተጫኑና ያልወጡ ተሳፋሪዎች ይገኛሉ።
የተሳፋሪዎች ህይወት በከፍተኛ አደጋ ላይ ስለሆነ አስቸኳይ የህክምና እና የነፍስ አድኖ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የአካባቢው ህዝብ የቻለውን ያህል ሰዎችን ለማውጣት ቢሞክርም መኪናውን ማንሳት ባለመቻሉ ተጨማሪ የከባድ መኪና/ማንሻ እርዳታ ያሻቸዋል።
ጥሪ ለሚመለከታቸው አካላት፡
በአካባቢው (አዋሽ በሎ/በአቅራቢያው) የምትገኙ፡
የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች
የጤና ባለሙያዎችና የአምቡላንስ አገልግሎቶች
የአካባቢው አስተዳደርና ነዋሪዎች
እባካችሁ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው በመድረስ የተጎዱትን ወገኖቻችንን እንድትታደጉ እና የህክምና እርዳታ እንድታደርሱላቸው በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን!
ሲሉ የተጎጅ ቤተሰቦች ተማፅነዋል።
መስከረም 23/2019 ጠዋት 2:45 የተፃፈ
Wasu Mohammed - Mereja