01/08/2023
መርዶክዮስ በንጉሱ በር ላይ ተቀምጦ እግዚአብሔር ያዘዘለትን እና ያዘጋጀለትን ቀን ይጠባበቅ ነበር እግዚአብሔርም በቀጠረው ጊዜና ሰዓት ለመርዶክዮስ መጣለት መርዶክዮስንም ከፍከፍ አደረገው የመርዶክዮስን ውድቀትና ሞት የሚጠባበቁ የመርዶክዮስ እና የአይሁድ ጠላቶች የመርዶክስን እና የአይሁድን ውድቀት እና ሞት አላዩም በተቃራኒው የእነሱን ከፍታ ነው ያዩት እግዚአብሔር ግን ለምንድነው መርዶክዩስን ከፍከፍ ያደረገው? እግዚአብሔር ሁለም ቅን ፈራጅ ነው የተዋረዱትን ማንሳት ልምዱ ነው ።
አስቴር 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ሐማም ገባ፤ ንጉሡም፦ ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ምን ይደረግለታል? አለው። ሐማም በልቡ፦ ንጉሡ ከእኔ ይልቅ ማንን ያከብር ዘንድ ይወድዳል? አለ።
⁷ ሐማም ንጉሡን እንዲህ አለው፦ ንጉሡ ያከብረው ዘንድ ለሚወድደው ሰው እንዲህ ይደረግ፤
⁸ ንጉሡ የለበሰው የክብር ልብስ፥ ንጉሡም የተቀመጠበት ፈረስ ይምጣለት፥ የንጉሡም ዘውድ በራሱ ላይ ይደረግ፤
⁹ ልብሱንና ፈረሱንም ከንጉሡ አዛውንት በዋነኛው እጅ ያስረክቡት፤ ንጉሡም ያከብረው ዘንድ የሚወድደውን ሰው ያልብሱት በፈረሱም ላይ አስቀምጠውት በከተማይቱ አደባባይ ያሳልፉት፤ በፊቱም፦ ንጉሡ ያከብረው ዘንድ ለሚወድደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል ተብሎ አዋጅ ይነገር።
¹⁰ ንጉሡም ሐማን፦ ፍጠን፥ እንደ ተናገርኸውም ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡም በር ለሚቀመጠው አይሁዳዊ ለመርዶክዮስ እንዲሁ አድርግለት፤ ከተናገርኸውም ሁሉ ምንም አይቅር አለው።
ጠላቶቻቹ ሞታቹን እና ውድቀታቹን የሚጠባበቁ የናንተን ክብር እና ከፍታ ሳያዩ አይሞቱም።
ሐማ የመርዶክዮስን ክብር እና ከፍታ በአይኑ ካዬ በኋላ ለመርዶክዮስ በዘጋጀው ግንድ ላይ ተሰቅሎ ሞተ።
አስቴር 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ንጉሡም አርጤክስስ ንግሥቲቱን አስቴርን፦ ይህን ያደርግ ዘንድ በልቡ የደፈረ ማን ነው? እርሱስ ወዴት ነው? ብሎ ተናገራት።
⁶ አስቴርም፦ ያ ጠላትና ባለጋራ ሰው ክፉው ሐማ ነው አለች። ሐማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ።
⁷ ንጉሡም ተቈጥቶ የወይን ጠጅ ከመጠጣቱ ተነሣ፥ ወደ ንጉሡም ቤት አታክልት ውስጥ ሄደ። ሐማም ከንጉሡ ዘንድ ክፉ ነገር እንደ ታሰበበት አይቶአልና ከንግሥቲቱ ከአስቴር ሕይወቱን ይለምን ዘንድ ቆመ።
⁸ ንጉሡም ከቤቱ አታክልት ወደ ወይን ጠጁ ግብዣ ስፍራ ተመለሰ፤ ሐማም አስቴር ባለችበት አልጋ ላይ ወድቆ ነበር። ንጉሡም፦ ደግሞ በቤቴ በእኔ ፊት ንግሥቲቱን ይጋፋታልን? አለ። ይህም ቃል ከንጉሡ አፍ በወጣ ጊዜ የሐማን ፊት ሸፈኑት።
⁹ በንጉሡም ፊት ካሉት ጃንደረቦች አንዱ ሐርቦና፦ እነሆ ሐማ ለንጉሡ በጎ ለተናገረው ለመርዶክዮስ ያሠራው ርዝመቱ አምሳ ክንድ የሆነው ግንድ በሐማ ቤት ተተክሎአል አለ። ንጉሡም፦ በእርሱ ላይ ስቀሉት አለ።
¹⁰ ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት፤ በዚያም ጊዜ የንጉሡ ቍጣ በረደ።