03/04/2021
ሄፓታይተስ ቫይረስ እና የጉበት በሽታ
Hepatatis Virus Infection
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)
ጉበት ከአንጎል ቀጥሎ ስራ ብዙ የሆነ የአካል ክፍላችን ሲሆን ኬሚካላዊ ሂደቶች የሚከናወኑበት በጣም አስፈላጊው የሰውነታችን ክፍል ነው::
የጉበት በሽታ በተለምዶው የወፍ በሽታ በመባል ይታወቃል::የአልኮል መጠጥ፣
መጠናቸው የማይታወቁ የባህል መድሃኒቶች፣የጉበት ቫይረስ ከብዙዎቹ የጉበት በሽታ ምክንያቶች ዋነኞቹ ናቸው።
በዛሬው ትምህርታችን ስለ ጉበት ቫይረስ በሽታ በሰፊው የምንመለከት ይሆናል::
የሄፓታይተስ ቫይረስ በዓይነት ብዙ ቢሆኑም በቀዳሚነት አደጋ የሚያደርሱት አምስቱ ,B,C,D እና E የሚባሉት ናቸው::በዚህም ምክንያት 325 ሚልዮን የሚሆነው የምድራችን ህዝብ በ ሄፓታይተስ ቫይረስ ይኖራል::(WHO,July 2019)
🔹ስንት አይነት የጉበት ቫይረስ በሽታ አይነቶች አሉ?
-ሁለት ሲሆን ጊዜያዊ(Acute) እና ዘላቂ(Chronic)ተብለው ይከፈላሉ::
በተወሰኑት ላይ ደግሞ የማይመለስ/የማይስተካከል እና የጉበት ካንሰር በማምጣት ለሞት ይድራጋሉ::
🔸ጊዜያዊ(Acute) የጉበት ቫይረስ በሽታ ምልክቶች?
-የሁሉም የጉበት ቫይረሶች ምልክት ተመሳሳይ ሲሆን ማቅለሽለሽ ፣ትኩሳት፣
ድካም ድካም ማለትና #የአይን እና የሰውነት ቆዳ ቢጫ መሆን/በተለምዶው የወፍ በሽታ የምንለው ነው።
🔸ጊዜያዊ(Acute) የጉበት ቫይረስ በሽታ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
-ከ ሁለት እስከ አራት ሳምንት ባለው ጊዜው ውስጥ በራሱ ይድናል።
🔹ስር ሰደድ እና አሳሳቢዎቹ የቫይረስ አይነቶች የትኞቹ ናቸው?
-ሄፓታይተስ B እና C
🔹ሄፓታይተስ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
-ሄፓታይተስ A እና E ቫይረስ ንፅህና ባለመጠበቅ( በአመጋገብ /የምግብ ውሃ )የሚተላለፍ ሲሆን በብዛትም ድሃ ተብለው በሚጠሩ ሃገራት በሽታው ይበዛል::
-ሄፓታይተስ B ቫይረስ በደም ንክኪ፥በግብረስጋ ግንኙነት ፥በእርግዝና ወቅት ከ እናት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል::ባንፃሩ ደግሞ ሄፓታይተስ C ቫይረስ በደም ንክኪ ይተላለፋል::