
12/07/2025
የደከምንበትን "አባካኙ ልጅ" ፊልም ሊለቀቅ ነዉ!!
ዘማሪት ቤተልሔም ተዘራ
ሊቪንግ ዊትነስ አገልግሎት ከሚሰራችው ሰራዎች መካከል አንዱ የሆነውን እና ያለፉትን ረጅም ወራት የደከምንበትን "አባካኙ ልጅ" የተሰኘ፤ በመዝሙር የታጀበ አጭር ፊልም ወደ እናንተ ልናመጣ ጥቂት ቀናት ቀርተውናል።
በዝማሬ የታጀበው አጭር ፊልም በሉቃስ 15 ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ከግሩም መልዕክት ጋር አንጋፋ እና አዲስ ተዋንያን ተሳትፈውበታል። በእግዚአብሔር እርዳታ የፊታችን ሐሙስ ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ እናንተ ይደርሳል።