
10/04/2025
እማማ ባሎቴ ይባላሉ፤ ከባለቤታቸው ለወንጌል ከተሰው ወንጌል አርበኛ ኦሞጨ ኡኩለ ጋር ወንጌልን ይዞ ከወላይታ ወደ ጎፋ የሄዱ የመጀመሪያ ሴት ወንጌላዊት ናቸው ። ከባለቤታቸው ጋር ወንጌልን እየሰበኩ እያሉ ባለቤታቸው በወንጌል ምክንያት በሰው እጅ ከተገደለ በኋላ ወደ ቤት እንዲመለሱ ተጠይቆ እንብ እንደ ባለቤቴ ለወንጌል መሞትን እመርጣለሁ በማለት ወንጌልን ያስቀጠሉ ጀግና የወንጌል አርበኛ ናቸው። እንደ ደመና ስለከበቡን ወንጌል አርበኞች ክብር ለጌታ ይሁን!
ከቃለ ሕይወት ታሪክ ማህደር የተገኘ ፎቶ፤