Shuaib seydmeki

Shuaib seydmeki ያንተ የሆነን ነገር አትጠይቅ

23/07/2025

ጋዛዎች በረሀብ እያለ*ቁ ነው

እነዚህ ፎቶዎች እ.ኤ.አ. በ1940ዎቹ ከተከሰተው የአፍሪካ ረሃብ ወይንም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መዛግብት የተወሰዱ አይደሉም።ይልቁንም ከዛሬዋ ጋዛ በዚህ ወቅት የተነሱ ምስሎች ናቸው

ህፃናት አይናችን እያየ ያለ መድሀኒት፣ ያለ ምግብ ፣ይህን ሲዖል ለማስቆም ምንም አይነት ድምፅ ሳይሰማ በረሀብ እየተበሉ ነው::

የንፁሀን አፅሞች የራሳቸውን ሞት ከማስታወቃቸው በፊት የሰው ልጆች ህሊና መሞቱን ቀድመው እያስታወቁ ናቸው::

እንዚህ አሰቃቂ ምስሎች በተባበሩት መንግስስታት መግቢያ በሮች ላይ ሊሰቀሉ፣ በየትኛውም የሰብዓዊ መብቶች ፎረም ላይ ሊታዩ፣ እኩልነትን፣ ገለልተኝነትን እና ደብል ስታንዳርድ ለሚሰብኩ ሁሉ ፊታቸው ላይ ያዩት ዘንድ ሊወረወር ይገባል::

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ."

ከዚህ በላይ ምን አይነት ጅምላ ፍ*ጅ*ት ይሆን ወንጀል ሊሰኝ የሚችለው?

ምን አይነት ምክንያታዊነት ይሆን ይህን በአይን ካዩ ቡኃላ ሊቀርብ የሚችለው?

ዝምታም ከዚህ ወንጀል ጋር መተባበር ነው!

መዘግየትም ወንጀል ነው!

ጋዛ እየተጣራች ነው.....

የሁላችንንም ምላሽ ትሻለች

እያንዳንዳችን አላህ ፊት ከመጠይቅ አንድንም:: የአዛኙ ነብይ ኡመት እዝነት ጠፍቶበታል:: ምንም ማድረግ ባይቻል እንኳን አላህ እንዲረዳቸው በዱዓ እናስታውሳቸው:: ለወንድሞቻችን ሁላችንም ማድረግ የምንችለው ቀላሉ ነገር ዱዓ ነው:: ልጆቻችንን ፣ እራሳችንን በነሱ ቦታ አድርገን በማየት ህመማቸውን እንታመም:: ፈረጃው ቅርብ እንዲሆንላቸው ወደ አላህ እጃችንን አንስተን እንማፀን::

21/07/2025
03/06/2025
01/06/2025
01/06/2025
22/04/2024

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

የመናዊው እውቅ አሊም የነበሩት ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ በ82 አመታቸው ወደ አኼራ ሄደዋል::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ በ1942 በሰሜናዊ የመን የተወለዱ ሲሆን በአባታችን መልካም አስተዳደግ ኢስላማዊ እውቀትን በተያዩ የሀገራቸው አሊሞች ተዘዋውረው ቀስመዋል:: በሀገረ ግብፅም ከኢስላማዊ እውቀት በተጨማሪ ኬሚስትሪ እና ባዬሎጂን አጥንተዋል::

ሼይኹ ከጥልቅ የምርምር ስራዎቻቸው በተጨማሪ ሁለገብ አሊም ነበሩ::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ በእስልምና ውስጥ ያሉ ሳይንሳዊ ተዓምራቶች ዙሪያ በርካታ ጥናቶችን በማድረግ ለንባብ ያበቁ ሲሆን በዚህ ስራቸውም በመላው አለም ለሚገኙ ቁጥራቸው በርካታ ለሆኑ ሳይንቲስቶች እና ተመራማሪዎች ወደ እስልምና እንዲገቡ ሰበብ መሆን ችለዋል::

በሳውዲ አረቢያ በቆዩበት ዘመንም ከሳኡዲ አረቢያ ሙፍቲ ከሼይኽ አብዱልአዚዝ ኢብኑ ባዝ እና ከሼይኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አልኡሰይሚን ጋር መገናኘት የቻሉ ሲሆን ለሰሯቸው በርካታ ኢስላማዊ ስራዎች እና የኢስላማዊ ድንጋጌዎች ብያኔዎችን በብዛት እንደ ማጣቀሻ ሁለቱን አሊሞች ይጠቀሙ እንደነበር ይነገራል::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ የአለም ኡለማዎች ምክር ቤትን ከመሰረቱት ኡለሞች መካከል ሲሆኑ በቁርኣን እና በሳይንስ ዙሪያ የሚያካሂዱትን የምርምር ስራ የሚያግዝ በየመን የኢማን የኒቨርሲቲንም ማቋቋም የቻሉ አሊም ነበሩ::

በተለይ በሰው ልጅ አፈጣጠር እና በፅንስ እድገት ዙሪያ ቁርኣን ውስጥ የሚገኙ አንቀፆችን በማብራራት ከሳይንሱ በፊት ቁርኣን ምን ያህል ለሰው ልጆች ሂደቱን እንዳብራራ በማስተማር በርካታ እውቅ ተመራማሪዎችን ወደ ኢስላም ማስገባት ችለዋል::

በሳኡዲ አረቢያም በጅዳ በሚገኘው የንጉስ አብዱልአዚዝ ዩኒቨርሲቲ ስር የተቋቋመው የሙዓሰሳ አልኢጃዝ አልኢልሚ ሱፕርቫይዘር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በቁርዓን ሳይንሳዊ ተዓምራት ዙሪያ በበርካታ የሳኡዲ አረቢያ ዩኒቨርሲቲዎች እና ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ማቅረብ ችለዋል::

የአለም ሙስሊሞች ሊግም እንዲመሰረት ምክረ ሃሳብ ያቀረቡ አሊም ሲሆኑ በተቋሙ ስር የምርምር ክፍሉን በመምራት የመጀመሪያው ለመሆን በቅተዋል::

በርካታ መፅሃፍቶችንም ለህትመት በማብቃት ለንባብ ያበቁ ሲሆን ከስድስት ያላነሱ ያልታተሙ መፅሀፍቶችንንም አበርክተዋል::

እኚህ ታላቅ አሊም በተወለዱ በ82 አመታቸው በሀገረ ቱርክዬ ወደ አኼራ የሄዱ ሲሆን በህይወት ዘመናቸው ለኢስላም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ትውልዱ ዘወትር የሚዘክራቸው ይሆናል::

ሼይኽ አብዱልመጂድ ቢን አዚዝ አዘንዳኒ አላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸው

Ⓞ➁
22/04/2024

Ⓞ➁

Address

Alaba K'Ulito
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shuaib seydmeki posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Shuaib seydmeki:

Share