
13/07/2025
ቼልሲ 🏆 ሻምፒዮን ሆኗል !
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከፒኤስጂ ጋር ያደረገውን የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ 3ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኮል ፓልመር 2x እና ጇ ፔድሮ አስቆጥረዋል።
ቼልሲ በታሪክ ሶስተኛውን የፊፋ ክለቦች ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።
ቼልሲዎች በሚቀጥሉት አራት አመታት የክለቦች አለም ዋንጫ አርማ በማልያቸው ላይ አርገው የሚጫወቱ ይሆናል።
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ሁለተኛ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።