
12/07/2025
የኢሕአፓው ተስፋዬ ደበሳይ የደርግ ወታደሮችን ሸሽቶ አንድ ዶክተር ጓደኛው ቤት ህቡዕ ገብቶ(ተደብቆ) እየኖረ ነው። አንድ ቀን ተስፋዬ ለዶክተሩ ጓደኛው ቄስ አጎቱ ከገጠር ሊጠይቁት እንደሚመጡ ይነግረዋል። ጓደኛውም በሀሳቡ ይስማማ እና ቄሱ ወደ ቤታቸው ተስፋዬን ለማየት ይቀላቀላሉ። የተስፋዬ ደበሳይ አጎት ጠዋት እና ማታ ዳዊት ከመድገም እና ለማዕድ ሲቀርቡ ቆርሶ ባርኮ ከመስጠት ውጪ ብዙ የማይናገሩ ዝምተኛ ቄስ ነበሩ። ሲያወሩ የንግግር ዘዬያቸው የሚያምር የባላገር አይነት ነው። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ቀናት ይቆያሉ። ተስፋዬም አጎቱን እያጫወተ መፅሀፍ እያነበበ እና ከጓደኛው ጋር ቼዝ እየተጫወተ ጊዜውን ያሳልፋል። አንድ ቀን ምሽት ላይ እንደተለመደው ተስፋዬ ደበሳይ እና ዶክተሩ ጓደኛው ቼዝ እየተጫወቱ ቄሱ ዝም ብለው ይመለከታሉ። ጨዋታውም እየተጋጋለ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ይደርሳል። ዶክተሩ ጓደኛው ተስፋዬን ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሷል። ተስፋዬም ላለመሸነፍ በከፍተኛ ተመስጥኦ ውስጥ ሆኖ ያሰላስላል። ቄሱም እንደተጫዋቾቹ ተመስጠው ቼዙ ላይ አፍጥጠዋል።እንዴት ቢሄድ ከመሸነፍ እንደሚድን ሲያብሰለስል የነበረው ተስፋዬም በጭንቀት አንዱን የቼዝ ፈረስ በዘፈቀደ አንስቶ ይሄዳል።ይሄኔ በተመስጦ ሲያዩ ከነበሩት የባላገር ቄስ ከአፋቸው አንድ ቃል ይወጣል "wrong move"🤝
ተስፋዬ እና ዶክተሩ ጓደኛው በከፍተኛ ድንጋጤ ወደ ባላገሩ ቄስ ይዞራሉ። ቄሱም ደንግጠው መልሰው ያፈጣሉ። እኚያ ቄስ ትክክለኛ ቄስ ሳይሆኑ የኢህአፓው ታጋይ የነበረው ሊቁ ጸጋዬ ገብረመድህን(ደብተራው) ነበር። ተስፋዬ የትግል አጋሩን ዶክተር ጓደኛው ቤት ለመደበቅ ከደብተራው ጋር ተመካክረው ያወጡት እቅድ ነበር።
እግረ መንገድ