Fekadu Zeleke

Fekadu Zeleke ትኩስ ወሬ ለህዝብ የሚያቀብል

ክብርት መሰረት አመርጋ የጉራጌ ቱባ የባህል እሴቶች ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችና ለአለም ለማስተዋወቅ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው
25/09/2026

ክብርት መሰረት አመርጋ የጉራጌ ቱባ የባህል እሴቶች ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችና ለአለም ለማስተዋወቅ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው

የሴቶች መስቀል፦ የጉራጌ ሴቶች የክብር በዓል **********************የአደይ አበባ ፈክቶ፣ የመስቀል ወፍ ብስራትን ተከትሎ፣ በመስከረም ውብ አየር ውስጥ የጉራጌ ምድር ልዩ ድምቀት...
25/09/2026

የሴቶች መስቀል፦ የጉራጌ ሴቶች የክብር በዓል
**********************

የአደይ አበባ ፈክቶ፣ የመስቀል ወፍ ብስራትን ተከትሎ፣ በመስከረም ውብ አየር ውስጥ የጉራጌ ምድር ልዩ ድምቀት ይለብሳል።

መስቀል ለጉራጌ ማኅበረሰብ የበዓላት ሁሉ ዘውድ፣ የታሪክ እና የማኅበራዊ ትሥሥር መገለጫ ነው።

ከዚህ ታላቅ በዓል ጋር በጥብቅ ከተሣሠሩ ውብ ባህላዊ እሴቶች መካከል ደግሞ የመስቀል ዋዜማ ማዕድ የሆነው የጎመን ክትፎ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

በተለይም የ“ሴቶች መስቀል” ወይም “የጎመን ክትፎ ቀን” ተብሎ የእርድ ቀን ከመድረሱ በፊት በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በዓል ድምቀቱ ልዩ ነው።

የመስቀል በዓል ዝግጅት በይፋ በሚጀመርበት በዚህ ዕለት፣ ሴቶች በራሳቸው ወጪና አቅም ማዕድ የሚያዘጋጁበትና በዓሉ በደንብ የሚጎላበት ልዩ ባህላዊ ሥርዓት ይከናወናል።

የጉራጌ ሴቶች ለበዓሉ ካላቸው ታላቅ ክብርና ፍቅር የተነሣ ወጪውን ለመሸፈን ዓመቱን ሙሉ በገንዘብ እና በግብዓት ይዘጋጃሉ፤ በገንዘብም ሆነ በጉልበት የበዓሉን መሰናዶ ወንዶችን ሳይጨምሩ ሴቶቹ ለብቻቸው ይከውኑታል።

የዕለቱ ዋና ማድመቂያ ደግሞ በጥራት የሚዘጋጀውና ከቅቤ፣ አይብ እንዲሁም ከጣፋጭ ቅመሞች ጋር የሚታሸው የጎመን ክትፎ ነው።

ለዚህ ማዕድ የሚመረጠው “ሲሟረ” በመባል የሚታወቀውና እስከ ግንዱ በደቃቁ ተከትፎ የሚዘጋጀው ልዩ የጎመን ዓይነት ነው።

የጎመን ክትፎ የዕለት ተዕለት ምግብ ሳይሆን፣ የክብር እንግዶች በሚሰበሰቡበት፣ የቤተሰብ እና የጓደኝነት ትሥሥር በሚታደስበት ቀን የሚቀርብ የክብር ማዕድ ነው።

በበዓሉ ዕለት፣ የጎመን ክትፎው በቅመማ ቅመም፣ በጥንቃቄ ከተነጠረ እና ከቀለጠ ንጹሕ የላም ቅቤ፣ ሚጥሚጣ እና ኮሮሪማ ጋር ታሽቶ በባህላዊው የሸክላ ዕቃ (ጣባ) ላይ ከቆጮ ጋር ይቀርባል።

ከአይብ ጋር ተቀላቅሎ ወይም ጎን ለጎን ተደርድሮ የሚቀርበው ይህ ማዕድ “ዝማሙጃት” በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ለበዓሉ ልዩ የባህል ግርማ ያላብሰዋል።

የመስቀል ወፍ ብሥራት ይዛ በገባችበት በዚህ ወር፣ የጎመን ክትፎ ማዕድ የጉራጌን ማኅበረሰብ አብሮነት፣ የእናትነት ክብር እና የባህል ባለቤትነት በጥበብ የሚያንጸባርቅ ሀገራዊ ሀብታችን ነው።

25/09/2026

 #አስራታችን በጉ/ሐ/ስ/ በእንደጋኝ ወረዳ ቤተ ክህነት   በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን!!የህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃና ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ የሚያሳይ ምስ...
25/09/2026

#አስራታችን በጉ/ሐ/ስ/ በእንደጋኝ ወረዳ ቤተ ክህነት በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን!!
የህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃና ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ የሚያሳይ ምስል ከስር ተያይዘዋል።

“ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
📖1ኛ ት ሐጌ 1፥8

!

  የመስቀል በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ትውልድ ቄያቸው በሚገቡ እንግዶች ተጨናንቃለች። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፥ አደረሰን!
24/09/2026

የመስቀል በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ትውልድ ቄያቸው በሚገቡ እንግዶች ተጨናንቃለች። እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፥ አደረሰን!

23/09/2026
22/09/2026

እነዚህ በጉራግኛ ጭፈራ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ልጆች በAI የተቀነባበረ አይደለም። የመስቀል ሰሞን በየአካባቢው የሚታይ ትዕይንት ማሳያ ነው

የጉራጌ ባህላዊ ጎጆዎች። ከ125 አመት በፊት ከ1877 እስከ 1886 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የተነሱ ፎቶግራፎች። Guraghe traditional huts over 125 years back som...
13/09/2026

የጉራጌ ባህላዊ ጎጆዎች። ከ125 አመት በፊት ከ1877 እስከ 1886 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የተነሱ ፎቶግራፎች።

Guraghe traditional huts over 125 years back sometime between 1885 & 1894 G.C
Italian Geographical Society Photographic Archive/Dr Leopoldo Traversi Photographs:

from Historic Ethiopia Through The Camera Lens: 1860s - 1990s is in Welk'It'E.

ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር

12/09/2026

ወያ ዘቨር ሸህ ኧቅራ
አፈር ሳቫይ ሰላም ኧህር፣
ትከ ኧትራእ ባሪቅ አግርዝ፣......
በገጣሚ ብርሃኑ አሰፉ መዘጋጀቱን ጠቅሶ የእኖር ኮሚዩኒኬሽን በፌስቡክ ገጽ የተለጠፈ

🌿🌻🌻ቀናት ይቀያየራሉ… ዘመናት ይሻገራሉ… ሥራ ግን ይቀጥላል!የትናንት ጥረት የዛሬን ውጤት ወልዶ፣ የዛሬ ሥራ ደግሞ የነገን ተስፋ ይገነባል።የቀን መቀያየር የጊዜ ዑደት ብቻ አይደለም፤ አዲስ...
11/09/2026

🌿🌻🌻ቀናት ይቀያየራሉ… ዘመናት ይሻገራሉ… ሥራ ግን ይቀጥላል!
የትናንት ጥረት የዛሬን ውጤት ወልዶ፣ የዛሬ ሥራ ደግሞ የነገን ተስፋ ይገነባል።

የቀን መቀያየር የጊዜ ዑደት ብቻ አይደለም፤ አዲስ ራዕይ፣ አዲስ እድልና አዲስ የሥራ ጉልበት የምንጀምርበት አዲስ ገጽ ነው።

ዛሬ የተዘራው በጥረት ከታከለ፣ ነገ የሚታየው ውጤት ይሆናል።
ስለዚህ ጊዜን አክብረን፣ እድልን ተጠቅመን፣ በትጋት እንሥራ።

ቀናት ይቀያየሩ፤ ዓመታት ይለዋወጡ፤ የልማትና የስኬት ጉዞዓችን ግን አይቋረጥም!
ዛሬን በሥራ፣ ነገን በውጤት!🌻🌻💐🌿

🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼

Address

Wolkite
Shewa

Telephone

+251913084971

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fekadu Zeleke posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fekadu Zeleke:

Shortcuts

Share