
28/06/2025
ይህ ለእኛ እንደ ሰበር ዜና ይቆጠራል!
የእኛም ምኞት፣ ህልማችን ሆነው የነበረው ይህ ነበረ። እሱም ትልቁ የሃዲያ ህዝብ እና አመራር አንድ ሆነው፣ አንድ ተነግረው ለአንድ ዓለማ፣ ለአንድ ልማት ለአንድ ሀገር መቆም አለበት የሚለው ጉዳይ ነበርን።
ለሀድያ ህዝብ አንድነት፣ ለሀድያ ህዝብ ልማት፣ ለሀዲያ ህዝብ እድገት ስናወራም እንደ ወንጀለኛ የተቆጠረነውም ይህ ነበር። ወንጀል እንደሰራን መጥሪያ በማውጣት ልንታሰር የተፈለገነውም ለእዚህ ዓለማ ነበረ። ይህ ዓይነት ስብስብ የናፈቅን፣ ያማረንም ነበረ።
በሀገራችን ደረጃ እንኳን በከፍተኛ ሁኔታ የገንዘብ ካፒታል ካሉት አካባቢዎች ውስጥ አንዱ የነበረው የሀዲያ ይህ ነው የማይባል የሚታይ ነገር ማዬት ያቃተን ህዝቡ፣ ወጣቱና አመራሩ አንድ ሆነው በመወያየት ችግሮችን መፍታት፣ መምከር ባለመቻሉ ነው።
አንድ ሀዲያን በሰፈር በጎሳ የመለያየት ስራዎች እየተሰራ በመቆየቱ ነው። አሁንም ጠንካራ ማህበር እንደነበረን መቀጠል ከፈለግን ይህ ዓይነት አንድነት መቀጠል አለበት።
@ፍፁም ተስፋዬ(Erbeeto)