
24/07/2025
#እግዚአብሔር!!
☞እግዚአብሔር ነገሮችህን ሳይሆን እምነትህን ያያል
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
♦️እግዚአብሔር ከእኛ ነገር ይልቅ በእርሱ ዘንድ ያለን የእኛን እምነት ይፈልጋል።ያለ እምነት ጌታን ደስ ማሰኘት የማይቻል እንደሆነ ነው ከቅዱስ ቃል የምንረዳው።
👉“መጽሐፍም፦ አብርሃምም ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።”
— ያዕቆብ 2፥23
👉ሮሜ 4
20-21፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ እንጂ በአለማመን ምክንያት ።
22፤ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።
23፤ ነገር ግን፡— ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ እንጂ፤
♦️አዎ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ የተባለው በእግዚአብሔር ላይ ያለው የተስፋ ቃሉን በማመኑ ነው።እግዚአብሔር በእኛ እምነት ይደሰታል፣በእርሱ የሚያምኑ አያፍሩም ተተብሏልና።
➣ችግር ልኖረን ይችላል
➣በሽታ ልሞከረን ይችላል
➣በእጦት ልንሰቃይ እንችላለን
➣ከሌሎች ተለይተን ተሰድደን ይሆናል
ይህ ሁሉ ባይኖረን እንኳ እግዚአብሔር ከዚህ ስቃይ በላይ ኃያል እንደሆነ በመረዳት በደስታ ልንውጥ ያስፈልገናል።
ለምሳሌ ዕንባቆምን ስንመለከት በወቅቱ የከበቡት ተግዳሮቶች በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ትልቅ የእምነት ደስታውን ሊያሸረሸረው አልቻለምና።👇👇
👉ዕንባቆም 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፤ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፤ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ እጠብቃለሁ።
¹⁷ ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
¹⁸ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
👉ማርቆስ 2
3፤ አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት።
4፤ ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፥ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ።
5፤ ኢየሱስም ሽባውን፡— አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ፡ አለው።
♦️እግዚአብሔር እናንተ ደካሞች ሸክም የከበደባችሁ ወደ እኔ ኑ ይላል።ይህ ማለት እኛ በራሳችን አቅም መፍታት ያቃተንን ነገር ሁሉ በእርሱ ላይ እንድንጥል ነው።ስለዚህ
➣ችግራችንን አንይ ➛አምላካችንን እንየው
➣ፈተና፣መከራ አያስጨንቀን➛በኢየሱስ እናምን
➣በያለቁብን ነገር ተስፋ አናቆርጥ➛በኢየሱስ እናምን
➣ዓላማው ላይ ቆመን ወደ ኢየሱስ ከቀረብን በእምነታችን ልክ እንድሁ መዳናችን ይሆናልና🙏
👉ማቴዎስ 9
2፤ እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፡— አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ፡ አለው።
20፤ እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤
21፤ በልብዋ፡— ልብሱን ብቻ ሆነ፥ እድናለሁ፡ ትል ነበረችና።
22፤ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አያትና፡— ልጄ ሆይ፥ አይዞሽ፤ ፡ አላት። ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምራ ዳነች።
♦️እግዚአብሔር የእኛን ነገር ጊዜ ሳይወስድ ልሰራና ልያስተካክለን ይፈልጋል::