
23/07/2025
“አእምሮህን ተጠቅመህ ነገህን ፍጠር!”
- ዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ
| የኒዩሮ ሳይንስ አመራር መጽሐፍ
***
ለአንድ ተቋም ስኬታማነትም ሆነ ውድቀት በቅድሚያ ጣት የሚቀሰረው ወደ መሪው እንደመሆኑ “በሁሉም ነገር ምሉእ የሆነ መሪ” ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? መሪውስ ምን ዓይነት ባሕርያት ሊኖሩት ይገባል? ሥራዎቹስ ምን መምሰል አለባቸው? መሪውን ከሌላው ማኅበረሰብ የተለየ ምን ዓይነት ክህሎት ቢኖሩት ነው፥ የሚመራው ተቋም የሚገጥሙትን ፈተናዎች እና ተግዳሮች ተቋቁሞ በስኬታማነት ሊወጣ የሚችለው? ለሌሎች አርዓያ በመሆን የተቋሙን ስምና ዝና ጠብቆ ማቆየት እንዴት ይችላል?
የንግድ ተቋማት ተወዳዳሪ ሆነው እንዲዘልቁ ምን ዓይነት ስትራቴጂዎችን መንደፍ እና መተግበር ይኖርባቸዋል? የሚሉና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን እያነሣ ምላሹን እጅግ ማራኪ በሆነ መንገድ የሚያቀርበው፣ በእውቀት የደረጀ፣ ከዚህ ቀደም በተግባር ተሞክሮ ውጤታማነቱንን ያስመሰከረ፣ “የኒዩሮ ሳይንስ አመራር” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ እንደበቃ ሰምተዋል?
ይህ የዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ፣ “ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ” ቅጽ አንድ መጽሐፋቸውን ተከትሎ ለንባብ ያበቁት ቅጽ ሁለት መጽሐፋቸው ሲሆን፣ ዶ/ር ያሬድ፣ በአገረ አሜሪካን ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው ኬይ ዌስት ዩንቨርሲቲ፣ የስትራቴጂክ ውሳኔ አሰጣጥና ችግር አፈታት እንዲሁም የአስተዳደር ኮርስ አስተማሪ ሲሆኑ፣ ሥራ ፈጣሪ፣ የካፒታል ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና የስኬታማ ኩባንያዎች ባለቤትም ናቸው።
ዶ/ር ያሬድ፣ ለዓመታት ካካበቱት የትምህርት ዝግጅታቸው እና የስኬታማ ኢንቨስትመንት አመራራቸውን መነሻ አድርገው፣ ለሀገሬው ልጆች፣ “የኒዩሮ ሳይንስ አመራር” የተሰኘውን፣ ስኬታማ ሥራ አመራር ላይ ትኩረት ያደረገ፣ በዓይነቱ ለየት ያለ መጽሐፋቸውን “የአመራር ልህቀትን በኒዩሮ ሳይንስ የማጎልበት ሂደት” በማለት ለንባብ አብቅተዋል።
መጽሐፉ በ237 ገጾች የተቀነበበ፣ 3 ክፍሎች፣19 ምዕራፎችን ያካተተ፣ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የታተመ ሲሆን፣ ከሐምሌ 2-2017 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች እየተሸጠ ይገኛል።
***
ዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ፤ በአገረ አሜሪካን ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኘው ኬይ ዌስት ዩንቨርስቲ፣ የስትራቴጂክ ውሳኔ አሰጣጥና ችግር አፈታት እንዲሁም የአስተዳደር ኮርስ አስተማሪ ሲሆኑ፣ ሥራ ፈጣሪ፣ የካፒታል ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና የስኬታማ ኩባንያዎች ባለቤትም ናቸው።
ዶ/ር ያሬድ፣ ለዓመታት ካካበቱት የትምህርት ዝግጅታቸው እና ስኬታማ ሥራዎቻቸውን መነሻ አድርገው፣ ለሀገሬው ልጆች፣ “ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ” የተሰኘውን፣ ውጤታማ የሥራ ፈጠራ ላይ ትኩረት ያደረገ፣ በዓይነቱ ለየት ያለ መጽሐፋቸውን ለንባብ አብቅተዋል።
ዶ/ር ያሬድ፣ “ኒዩሮ ሳይንስ ለሥራ ፈጠራ” ቅጽ አንድ መጽሐፋቸው፣ የስኬታማ ሥራ ፈጣሪነት ዋነኛው ምሥጢር የሆነውን የአእምሮን ሥነ ሕይወታዊና ግብረ አካላዊ ባሕርያት በማስረዳት፣ ሥራ ፈጣሪው በአግባቡ እና በብቃት እንዲጠቀመው፣ የሚገጥሙትን ፈተናዎች ምንነት በተገቢው ሁኔታ እንዲገነዘብና መፍትሔዎቻቸውን በመፈለግ ረገድ የተዋጣለት፣ ከሌሎች የተሻለ ስኬታማ ሊያደርገው የሚችለውን በመጽሐፋቸው በስፋትና በጥልቀት አቅርበውል።
መጽሐፉ በ310 ገጾች የተቀነበበ፣ 12 ምዕራፎችን ያካተተ፣ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የታተመ ሲሆን፣ ከሐምሌ 2-2017 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሁሉም የመጻሕፍት መደብሮች እየተሸጠ ይገኛል።
“አእምሮህን ተጠቅመህ ነገህን ፍጠር!” (ዶ/ር ያሬድ ኢሳያስ)