ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef "በጎ ሥራ ከፍቅር ይወለዳል።"
↪️ https://t.me/Hailemariamderese

"...አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ።" ብለን ስንዘምር ምን ማለታችን ነው?+++++++++++++✍️ "ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ። ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምር...
27/10/2025

"...አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ።" ብለን ስንዘምር ምን ማለታችን ነው?
+++++++++++++
✍️ "ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ። ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ። አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ። አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ። ወለኪሰ ይሰግድ ውእቲ።"

➾ትርጉም፦ የጊዮርጊስ የስሙ(የሰማዕትነቱ) ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፤
ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቍ ይልቅ የጠራ የክብር ጌጥ የኾንሽለትና በክብር የነገሠብሽ የክብር አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለጊዮርጊስ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፥ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።

➦"ቀጸላ" በብዙ ቍጥር ቀጸላት ሲባል በቁሙ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት፤

➻አክሊል ዘውድ፣ ኵፌታ ቆብ መጠምጠሚያ፣ ባርኔጣ ኹሉ ቀጸላ ሊባል ይችላል።

➦ዕጨጌዎችና አበ ምኔቶች በቆባቸው ላይ የሚለብሱት፤ የሚከናነቡት ሻሽ ነጠላ ቀጸላ ይባላል።

➦"በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥..." ራእ. 9፥7 የሚለውን ግዕዙ "ወዲበ ርእሶሙ ቦሙ ቀጸላ በአምሳለ ወርቅ።" ይላል።

➥"በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥" ራእ. 12፥3 በግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ "ሰብዐቱ ቀጸላት" ይላል።

➤ቀጸላ ቅጽል ኾኖ በስምና በግብር የሚጨመር ቃል ሲኾን የአካልንና የግብርን አኳኾን ጠባዩን መልኩን የሚገልጥና የሚያስረዳ ነው። ነዊኅ፥ ሠናይ፥ ጸዐዳ እንደማለት ነው።

➔አክሊል የክብር ምልክት፥ የክብር መጨረሻ ነው። የሚቀዳጁትም ትልቅ ማዕርግና ታላቅ ክብር ያላቸው ሰዎች ናቸው።

➾ እግዚአብሔር አሮንን እና ልጆቹን ለክህነት ከለያቸው(ከመረጣቸው) በኋላ መፈጸም የሚገባውን ሥርዐት ለሙሴ ሲነግረው፦ "ወታነብር አክሊለ ዲበ ርእሱ፥ ወታነብር ቀጸላ ዘወርቅ ዲበ አክሊሉ፦ መጠምጠሚያውንም በራሱ ላይ ታደርጋለህ፥ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ።" ዘጸ.29፥6። ይኽም ስለ ሊቀ ካህናቱ ክብር ነው።

➬ስለ ታቦቱ ክብርም፦ "በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት።" ዘጸ.25፥11

➲ አክሊል(ዘውድ) የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው። የብዕለ ሥጋ ፍጻሜው ዘውድ እንደኾነ ኹሉ የብዕለ ነፍስ ፍጻሜ አክሊል(ዘውድ) የምትባል መንግሥተ ሰማያት ናትና። "ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።" 2ኛ ጢሞ. 4፥8።

➔"ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት፦ መንግሥተ ሰማያትን አወርሳለሁ።" ሐተታ፦ አክሊል አላት፤ የብዕለ ሥጋ ፍጻሜ ዘውድ እንደ ኾነ የብዕለ ነፍስም ፍጻሜ መንግሥተ ሰማይ ናትና።" እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።" ራእ.2፥10 እንዲል።

➺እመቤታችን አክሊል ተቀዳጅታ መታየቷ ከፍጥረታት ኹሉ በላይ የኾነውን ክብሯን፥ ማዕረጓን የሚመሰክር ነው። መልዕልተ ፍጡራን መትህተ ፈጣሪ ናትና።

➛በሌላ በኵል ደግሞ የነቢያት የሐዋርያት የጻድቃን የሰማዕታት የሊቃውንት የካህናትና የምእመናን አክሊል እርሷ ናት።

➦ቅዱስ ኤፍሬም "አክሊለ ምክሕነ፥ ወቀዳሚተ መድኃኒት፥ ወመሠረተ ንጽህነ፦ የመመኪያችን ዘውድ፥ የድኅነታችን መጀመሪያ፥ የንጽህናችንም መሠረት"[ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ]

➔"ለራስ ጌጥ ቀጸላ ሁኚኝ የምስጋናሽ ፍጻሜ ወዳለበት እደርስ ዘንድ በክንፈ ሕሊናዬ ወደ አየር ተነጠቅሁ።"[አርጋኖን ዘሠሉስ]

➺"ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ።"[መጽሐፈ ሰዓታት]

➦"ለሚጋደሉ ኹሉ አክሊላቸው ድንግል ሆይ የመሃይምናን(የምእመናን) የሃይማኖታቸው ቀጸላ የቅዱሳን ሽልማት የነቢያት ልጃች የሐዋርያት እናታቸው የሰማዕታት መመኪያቸው የደናግል የመነኮሳት ጌጣቸው።" [አርጋኖን ዘሐሙስ]

➺"ሰላማዊት ሆይ፥ ለተጣሉት አስታራቂያቸው ለተራቆቱትም የደስታ ልብሳቸው አንቺ ነሽ። ለቀረቡት መዳኛቸው፤ ለራቁትም አክሊላቸው ነሽ።" [የማክሰኞ እንዚራ ስብሐት]

➦"የሰማዕታት የክብር አክሊላቸው የሕጻናት እናታቸው የአብያተ ክርስቲያናት መመኪያ፤ የደናግልና የመነኮሳት የንጽህናቸው መሠረት በሁለት ወገን ድንግል የምትኾኚ ማርያም ሆይ ነይ..."[መዓዛ ቅዳሴ ዘደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ]

➦ሐራሴ ወንጌል(የወንጌል ገበሬ) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተሰሎንቄ ክርስቲያኖችን "የመመኪያችን ክብር" ብሏቸዋል። "ወአክሊለ ምክሕነ፦ የመመኪያችን ክብር ማነው?" "...የትምክህታችን አክሊል ማን ነው?" 1ኛ.ተሰ.2፥19 እንዲል።

➺"የመሐይምናን(የምእመናን) እናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትኾን አባታቸው እግዚአብሔር ነው"[መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ዘሮም፤ ምዕራፍ 10፥44]

ምንጭ © ዘማርያም ዘለቀ

https://t.me/Hailemariamderese
ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

27/10/2025
የሕልማችሁ እውነተኛነት ማረጋገጫ!➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የገንዘብ አቅም በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የእውቀት ደረጃ በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡➫ ሕልማችሁ ካላችሁ ...
25/10/2025

የሕልማችሁ እውነተኛነት ማረጋገጫ!

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የገንዘብ አቅም በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የእውቀት ደረጃ በላይ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ካላችሁ የሰው-ለሰው ግንኙትና የእውቅና ብዛት ያለፈ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ አሁን ካላችሁበት የኑሮ ሁኔታ ያለፈ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

➫ ሕልማችሁ ያለ የሌላችሁን አቅም ተጠቅማችሁ እንኳን የሚወጥራችሁ ካልሆነ ሕልም አይደለም፡፡

የሕልማችሁ ጉዳይ ከባድ ሆኖ ሲታያችሁ፣ የማትደርሱበት ሲመስላችሁና ሩቅ እንደሆነ ስታስቡ እውነትም ሕልማችሁ “ሕልም” ነውና ደስ ይበላችሁ፡፡

ዝም ብላች አቅዱ፣ ራሳችሁን አሻሽሉ፣ ወደ ሕልማችሁ ተራመዱ!

ይሆናል! ይሳካል!

© Dr.Eyob mamo

https://t.me/Hailemariamderese
ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

ጥቅምት 14 አቡነ አረጋዊ የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!! የአቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!https://t.me/Hailemariamdereseቤ...
23/10/2025

ጥቅምት 14 አቡነ አረጋዊ የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡
እንኳን አደረሳችሁ!! የአቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

https://t.me/Hailemariamderese
ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት ፲፪አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ። በዚ...
22/10/2025

ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት ፲፪

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ። በዚችም ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና የዳዊት አባት ወደሆነ በቤተ ልሔም ወደሚኖር ወደእሴይ ቤት ይሔድ ዘንድ በቂስ ልጅ በሳኦልም ፈንታ ለእስራኤል ልጆች እንዲነግሥ ልጁ ዳዊትን ይቀባው ዘንድ አዘዘው ።

ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሔዶ ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ ብለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና ።

ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ በአደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም ። ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን አለው ዕሴይም በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው ።

ሳሙኤልም ደግሞ ዕሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው ። እሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ ዐይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቅባው አለው ። በዚያንም ጊዜ ሳሙኤል የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይአደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ ።

ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገድለውና የእስራኤልን ልጆች እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው ።

ስለዚህም የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተክርስቲያን መምህራን አዘዙን ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመላእክት አለቃ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።

https://t.me/Hailemariamderese
ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል (ጥቅምት ፭) አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን የተቀበሉበትን ጥቅ...
14/10/2025

እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል (ጥቅምት ፭) አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!

የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቃል ኪዳን የተቀበሉበትን ጥቅምት ፭ ቀን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

https://t.me/Hailemariamderese
ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

✝️ ጥያቄ-፩፡ ፩. “ጸፍናት ፐዕናህ” ማለት ምን ማለት ነው ?፪. ለማን የተወጣ ስም ነው ?፫.“ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስሙን ያወጣው ማነው?ምልሱን በhttps://t.me/hailederese2...
14/10/2025

✝️ ጥያቄ-፩፡

፩. “ጸፍናት ፐዕናህ” ማለት ምን ማለት ነው ?
፪. ለማን የተወጣ ስም ነው ?
፫.“ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስሙን ያወጣው ማነው?

ምልሱን በhttps://t.me/hailederese21 ላይ ላኩልኝ።

ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

ጽጌንቦች የሚቀስሟት፥ ዝንቦች የሚርቋት ጽጌ ይህች ናት።ሶምሶን ከአንበሳ አፍ ውስጥ ያገኘው ማር የተቀሰመባት ጽጌ/አበባ ድንግል ማርያም ናት። ማሩ ጌታችን ክርስቶስ ነው። Alamrew.ቤተ ዮ...
13/10/2025

ጽጌ
ንቦች የሚቀስሟት፥ ዝንቦች የሚርቋት ጽጌ ይህች ናት።
ሶምሶን ከአንበሳ አፍ ውስጥ ያገኘው ማር የተቀሰመባት
ጽጌ/አበባ ድንግል ማርያም ናት። ማሩ ጌታችን ክርስቶስ ነው።

Alamrew.

ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef

Address

Shewa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቤተ ዮሴፍ - Bete Yosef:

Share