
16/06/2025
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን በሾኔ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት አዘጋጅነት"በተደረጀ የአመራርና የህዝብ ባለቤትነት እና ተሰትፎ ህዝባችንን ከመዘናጋት እናውጣ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የኤች,አይ,ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የሾኔ ከተማ አስተ/ር ጤና ጽ/ቤት ሰኔ 09/2017 ዓ.ም ሾኔ
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሾኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበራ በዶሬ በንግግራቸው ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በመንግሥት፤ በሕዝብና በአጋር አካላት በተደረጉ ጥረቶች እንደ ሀገር አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ማህበረሰቡም ይሁን አስፈፃሚው አካል ለበሽታው ያላቸው ትኩረት በመቀነሱ ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት በ2030 ለመግታት ከታቀደው አንፃር በሚፈለገው መጠን እንዳልቀነሰ አስታውሰው በቀጣይ ሁሉም ባለድርሻ አካል ከገባበት መቀዛቀዝና መዘናጋት እንዲወጣ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ መሆኑን በመግለጽ የዕለቱን መድረክ ከፍተዋል።
የንቅናቄ ሰነዱን ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ የዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ ምላሽ ሂደት ተወካይ አቶ አማረ ማርቆስ ሲሆኑ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግና በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶቾና ቀበሌያት ላይ ተመሳሳይ ውይይት እንዲደረግ የተቋረጠው 0.5 % HIV ፈንድ ለማስቀጠል ሁሉንም የመንግስት ሰራተኛ ማሳመንና ማስቆረጥ እንደሚገባ አቅጣጫ በመያዝ የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።
የሾኔ ከተማ አስተ/ርጤና ጽ/ቤት ሰኔ 09/2017 ዓ.ም
ሾኔ