
03/07/2025
!
ወላይታ ሁለንተናዊ የሚዲያ አገልግሎት ማዕከል ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም።
ይህች ከታች በፎቶ ላይ የሚትመለከቷት ልጅ እህታችን ኤደን ለገሠ ትባላለች። ሲዳማ ልማት ማህበርን ጨምር በሲዳማ ክልል ውስጥ የትላልቅ ተቋማት አምባሳደር ናት። የሲዳማ ታሪክ ፤ ባህልና ቋንቋ በዓለም ደረጃ በማስተዋወቅ ረገድ ስሟ ገኗል። ከሲዳማም አልፎ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደተለያዩ ብሔሮች ከተማ እየተዘዋወረች የተለያዩ ብሔሮች ታሪክና ባህል በዓለም አቀፉ ቋንቋ(በእንግሊዝኛ) እየዘገበች ዕንቁ ባህላችን ወደ ዓለም ህዝብ የሚታደርስ ድንቅ ልጅ ናት።
እህታችን ኤዱለገሠ አምላክን የሚትፈራ፤ ሰውንም የሚትወድ፤ የመላውን የኢትዮጵያ ብሔሮችን ታሪክ፤ ቋንቋና ባህል የሚታከብርና ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም የመኖር ባህሪ ያላት የዘመናችን ዕንቁ ሰው ናት።
ነገር ግን ይህችን ትሁት እህታችን በዚህ ሳምንት ከሚትወደው ህዝብ ብርቱ ተቃውሞ ገጥሟታል። ማህበራዊ ሚዲያ ሁሉ እርሷን የሚያሳድድ መረጃ እያሰራጨ ይገኛል። ታዲያ ኤደን ምን አድርጋ ነው የሚትሳደደው የሚል ሰው አይጠፋምና ነገሩ እንዲህ ነው፦
በሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው ውሳኔ በቅጣት የታገዱ ተጫዋቾችን በማሳተፉ ምክንያት የ2017 ኢትዮጵያ ካፕ ሻምፒዮን ተብሎ ዋንጫ የወሰደው የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ በፎርፌ ዋንጫው ለዕለቱ ተጋጣሚው ለወላይታ ዲቻ ይመልስ በሚለው መግለጫ በጣም እንደደነገጠችና በጣም ለሚትወደው ለወላይታ ህዝብ ደግም "የእንኳን ደስ አላችሁ" መልእክት በራሷ ፌስቡክ ፔጇ ለጠፈች። እንስቷ ይህን መልእክት በለጠፈችው በሁለተኛ ደቂቃ ላይ ብሔር ከብሔር ጋር በማጣላት ሥራ የተሰማሩ ወገኖች መልእክቷን በሌላ ተርጎመው screenshot አድርገው ሚዲያ ላይ መሯሯጥ ጀመሩ።
በዩትዩብ፤ በትክቶክና በፌስቡክ የሚከተሏት ወዳጆች unfollow እና unsubscribe እንዲያደርጓት በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የወጡ ሰዎች ቁጥራቸው አሸዋ ነው። ከዚያም አልፎ ኤደን ለገሠ አምባሳደር ከሆነችባቸው ተቋማት ሁሉ አምባሳደርነቷ እንዲነሣም ለማድረግ ብዙዎች እንቅስቃሴ ጀምሯል። በሁኔታው እጅጉን የደነገጠችው ኤደን የለጠፈችውን መልክት በፍጥነት ከፔጇ ላይ በማጥፋትና መላውን የሲዳማ ህዝብና የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎችን ይቅርታ በመጠየቅ ነገሩን ለማረጋጋት ብትሞክርም በሰይጣን የሚመሩ ክፉ ሰዎች ይቅርታዋን ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆኑም።
ቃል በቃል፦ " የጀግናው የካዎ ጦና ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ። ትናንት ከፌዴሬሽኑ ዘግይቶ በመጣው ውሳኔ ስሜታዊ ሆኜ እናንተን ረሳሁና አፉ በሉኝ። ወንድም የሲዳማ ህዝብ ይወዳችኋል፤ እኔ አንዷ ነኝ።" ከሚለው መልእክቷ ውስጥ እንዴት ጠማማ ትርጉም ይውጣል? እንዴትስ ትኮነናለች? ይህች ልጅ እኮ በመጀመሪያ በፌዴሬሽኑ ውሳኔ ስሜታዊ መሆኗን በመግለፅ የታላቁ የሲዳማ ህዝብ ሃዘን እርሷም አዘነች። ደግሞ ከፈጣሪ የተሰጣት የህዝብ ፍቅር አስገድዷት ለወላይታ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ፍቅሯን ገለፀች። በአጭሩ ከሚያዝነው ህዝብ ጋር የሀዘኑ ተካፋይ እንደሆነችና ከሚደሰተው ህዝብ ጋር ደስታቸውን መጋራቷን ገለፀች። ምክንያቱም ልጅቱ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊት ናትና ሁለቱም ህዝቦች ህዝቦቿ ነው። ግን ያለጥፋት ይቅርታ እየጠየቀችና እየወተወተች ላለችው ለዚህች እንስት ሁለቱም ህዝቦች ከጎኗ አልቆሙም። በሲዳማ ህዝብ ስም የሚያባርሩት ጠንክሮ ቀጥሏል። በወላይታ ህዝብ በኩል ደግሞ አንድ ሰው እንኳ ሚዲያ ላይ ወጥቶ አለሁልሽ አላላትም።
በመሆኑም Gifaataa Tube ለመላው የወላይታ ተወላጆች አንድ መልእክት ማስተላለፍ እንፈልጋለን፦ እባካችሁ ሁላችንም ይችን ቀና አመለካከት ያላትን ድንቅ ልጅ በየማህበራዊ ሚዲያዎቿ follow እና subscribe በማድረግ እኛም የወላይታ ህዝብ ከልብ እንደሚንወዳት ፍቅራችን በተግባር ፤ በሥራ እናሳያት።
በወላይታ ሁለንተናዊ ሚዲያ አገልግሎት ተዘጋጅቶ በGifaataa Tube የቀረበ፤ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም።
email - [email protected]
website- http://gifaataatube.blogspot.com
Youtube- https://youtube.com/
Tiktok- https://tiktok.com/.naatu.keettaa
Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EZRVzrQtr/
https://www.facebook.com/share/16t5CTL6jo/
https://www.facebook.com/share/16kTnUc3pQ/
https://www.facebook.com/wolayta.dicha.982731
telegram- https://t.me/gifaataatube