
28/01/2025
የወላይታ ዞን አስተዳደር አማካሪዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ታደሰ በሶዶ ከተማ የሚሠሩ የአስፋልት መንገድ ሥራዎችን በሚመለከት ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረጉ።
ወላይታ ሶዶ፣ ጥር 19/2017 (ወቴቪ)
የወላይታ ዞን አስተዳደር አማካሪዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ታደሰ በሶዶ ከተማ የሚሠሩ የአስፋልት መንገድ ሥራዎችን በሚመለከት ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አደረጉ።
አቶ ተመስገን ታደሰ በሶዶ ከተማ ከኮካቴ እስከ ግብርና ኮሌጅ እንዲሁም ከከንቲባ አደባባይ እስከ አረካ ማዞሪያ የሚሠሩ የአስፋልት ሥራ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ በሚሠሩበት ሁኔታ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርገዋል።
በምክክሩ በአዎንታ ከተነሱ ጉዳዮች የተለያዩ ተቋማት እና የከተማው ነዋሪዎች ድጋፍ ማግኘቱ የሚጠቀስ መሆኑ ተነስቷል።
የግንባታ ሥራው በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ለሥራው እንቅፋት የሚሆኑ በመንገድ ዳር ያሉ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት ማንሳት እንደሚገባ የተነሳ ሲሆን የመንገድ፣ የቴሌ የመብራት እና የውሃ ተቋማት መናበብ ያስፈልጋል ተብሏል።
በኮንትራክተሩ በኩል በሙሉ አቅሙ እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት የሚሆኑ ማናቸውም ጉዳዮች እንዳይኖሩ መሠራት እንዳለበትም ተነስቷል።
በማጠቃለያም የዞኑ ዋና አስተዳደር አማካሪዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን በመወጣት ለሥራው ስኬታማነት ርብርብ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
በምክክሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ፣ የሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ፣የየተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ የፕሮጀክቶቹ ተቋራጮች ተወካዮች
እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ
https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/
የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/wolaitatelevision
ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ
https://twitter.com/WolaitaTV?s=09
ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን