Damot Sore Media-press

Damot Sore Media-press Media expressions well done

የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተመለከተአዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ እቃዎች ዝውውር የሚሳተፉ የመንግሥት አ...
28/11/2023

የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ እቃዎች ዝውውር የሚሳተፉ የመንግሥት አመራሮችን የማጋለጥና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገለጹ።

የኮሚሽኑ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ባለፉት ወራት ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በተሰራው ሰፊ ስራ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።

የኮንትሮባንድ የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎች በተከታታይ እየተሰሩ ቢሆንም ችግሩ አሁንም በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ላይ ተፅዕኖ መደቀኑን ጠቅሰዋል።

በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ መረጃ አሳልፈው የሚሰጡ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉትም እንዲለቀቁ የሚያደርጉና በህግ እንዳይጠየቁ የሚሰሩ አመራሮች እንዳሉም ገልጸዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ለኮንትሮባንድ ዝውውር እጀባ የሚሰጡ አካላት ስለመኖራቸውም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በየአካበቢው ያሉ ኬላዎች የምርት ዝውውርን እያስተጓጎሉና ኮንትሮባንድን እያባባሱ በመሆናቸው እንዲነሱ የተሰጠው አቅጣጫ አለመተግበሩንም ነው ያነሱት።

በየኬላው ችግር የሚፈጥሩ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በማጥራት እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም ኮንትሮባንድን መከላከልና መቆጣጠር የሁሉንም ጥረት በመጠየቁ በተፈለገው ደረጃ ውጤት ያለመገኘቱን ገልጸዋል።

  22 ጠንቋዮች ራሳቸውን አጋለጡወሎ ውስጥ በደላንታ ወረዳ የኢላና ትምህርት ቤት መምህራን ከጣርዳት፣ ከደሀናንና ከዝባን የገበሬ ማኅበራት ጋር በመተባበር በመካከላቸው የተሰገሰጉትን 22 አባ...
02/08/2023



22 ጠንቋዮች ራሳቸውን አጋለጡ

ወሎ ውስጥ በደላንታ ወረዳ የኢላና ትምህርት ቤት መምህራን ከጣርዳት፣ ከደሀናንና ከዝባን የገበሬ ማኅበራት ጋር በመተባበር በመካከላቸው የተሰገሰጉትን 22 አባይ ጠንቋዮች ራሳቸውን አጋልጠው ክቡር ወደሆነው የሥራ መስክ እንዲሰማሩ አደረጉ።

እነዚሁ 22 አባይ ጠንቋዮች በተሰጣቸው ትምህርት አምነው ድቤዎችን (ከበሮዎችን)፣ እንዲሁም በእጃቸው ይገኙ የነበሩትን ልዩ ልዩ የጥንቆላ ዕቃዎችንና መጽሐፍት ለገበሬ ማኅበራቱ በራሳቸው ፈቃድ አስረክበዋል።

አባይ ጠንቋዮቹ ካስረከቧቸው ዕቃዎች ውስጥ በተለይ ከበሮዎቹ በአካባቢው ለሚቋቋመው የኪነት ቡድን መገልገያ እንዲሆን መሰጠቱ ተገልጧል።

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 23 ቀን 1971 ዓ.ም ታትሞ የወጣ

Wolaita S**o Ethiopia!! Wolaita S**o City is the pathway of 7 gates to Addis Ababa, Hawassa, Dilla, Gofa, Gamo, Hosaina ...
02/08/2023

Wolaita S**o Ethiopia!! Wolaita S**o City is the pathway of 7 gates to Addis Ababa, Hawassa, Dilla, Gofa, Gamo, Hosaina and Durame Cities!!

Welcome all passengers and strangers !! You will be profitable if invest here in wolaita S**o plus within wolaita zone!!

Have had a nice day!!

ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀዳሞት ሶሬ፣ጥቅምት 10፣2015 ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ የፊታችን ቅዳሜ በቀን 12/2...
20/10/2022

ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ

ዳሞት ሶሬ፣ጥቅምት 10፣2015 ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ የፊታችን ቅዳሜ በቀን 12/2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪና የስልፉ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ አስታወቁ፡፡

ሰልፉ "ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ!" በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ነው የገለጹት፡፡

የሰልፉ ዓለማ አገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅና ለአገራችን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር ከዜጎች የሚጠበቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ከመንግስታችን ጎን መቆማችንን ማረጋገጥ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

ሽብርተኛው ህወሓት ለ3ኛ ጊዜ የከፈተብንን ጦርነት ለማወገዝና ጦርነቱን በብቃት መክተን የአገራችንን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነቷን ለማጽናት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር ለኢትዮጵያውያን መስጠት ያልፈለጉና ደጋግመው የሚቃወሙ ሀገራትና አካላት ከአገራችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ለማሳሰብ ነው ብለዋል፡፡

ሀገርን ከጥፋት ሀይሎች ለመታደግ የህይወት መሰዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦሩ ጎን በመቆም ደጀንነታና አጋርነታችን መገለጽ አለብን ብለዋል፡፡

የሀገር ሉአላዊነትና የሀገራችንን የግዛት አንድነት ለማፍረስ የተከፈተብንን ጦርነትና የምዕራባዊያን ሀሰት ፕሮፓጋንዳውን በፀኑ የሚያወግዝ ሰልፍ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

መላው የዞኑ ነዋሪዎች ሀገሪቷ የገጠማትን የውስጥ እና የውጭ ጫናዎችን ለመመከት ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በአንድነት መቆም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ሰልፉ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ የገለጹት አቶ ሳሙኤል በዚህ መላው የዞኑ ህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም ጠቅሰዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ በወላይታ ሶዶ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም ይካሄዳል ያሉት አቶ ሳሙአል የዞኑ ነዋሪዎች በዚህ ታርካዊ ሰልፍ ላይ በንቂስ ወጥቶ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

''የጊፋታ በዓል ለወላይታ ከዘመን መለወጫነት ባለፈ የማንነቱ መገለጫ፣ የታሪኩ መጀመሪያ፣ የተስፋና የብርሃን መንገድ መጀመሪያ ነዉ'' ክብርት ወይዘሮ መስከረም ደገፉ የዳሞት ሶሬ ወረዳ መንግ...
20/09/2022

''የጊፋታ በዓል ለወላይታ ከዘመን መለወጫነት ባለፈ የማንነቱ መገለጫ፣ የታሪኩ መጀመሪያ፣ የተስፋና የብርሃን መንገድ መጀመሪያ ነዉ'' ክብርት ወይዘሮ መስከረም ደገፉ የዳሞት ሶሬ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ

ዳሞት ሶሬ፦ 10/01/2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት፣ ሁሉም የወረዳዉ አመራር አካላት፣ የሁሉም ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል አስተዳዳሪዎችና የኃይማኖት መሪዎች በተሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

ክብርት ወይዘሮ መስከረም ደገፉ የዳሞት ሶሬ ወረዳ መንግስት ዋና ተጠሪ በመድረኩ ተገኝተዉ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ጊፋታ ለወላይታ ህዝብ የማንነቱ መገለጫ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ ድልድይ፣ የታሪኩ መጀመሪያና የተስፋና የብርሃን ጉዞ መጀመሪያ እንደሆነ ተናግሯል።

''Gifaataa'' በኩር ወይም የመጀመሪያ/መሠረት/መነሻ/አልፓ የሚል ትርጓሜ እንዳለው የጠቀሱት ወይዘሮ መስከረም ደገፉ አበቦች ፈክተው፣ አዝመራው ደርሶ፣ አርሶ አደሩ፣ ነጋዴዉና በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሠማራው ህዝብ ከድካም አርፈው እንዲሁም ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ መሸጋገርን ላበሰረ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓልም ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።

የ”ጊፋታ” በዓል በወላይታ ብሄር ዘንድ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ ብስራት ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ባህልና ቱርዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በረከት በቀለ ተናግረዋል።

ወይዘሮ በረከት በቀለ ''ጊፋታ'' የወላይታ ብሔር የአንድነት መስተጋብር የማጠናከር አቅም ያለው በመሆኑ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፣ ምሁራንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ገልጸዋል።

የጊፋታ በዓል በወርሃ መስከረም ከቀን 14 እስከ 20 ባሉት ቀናት ውስጥ በሚውል እሁድ የእርድ ቀን ሆኖ ዘንድሮው መስከረም 15 እሁድ እንደሚከበር ተመላክተዋል።

''Gifaataa'' በኩር ወይም የመጀመሪያ የሚል ትርጓሜ እንዳለው የጠቀሱት ወይዘሮ በረከት አበቦች ፈክተው፣ አዝመራው ደርሶ፣ ከድካም አርፈው እንዲሁም ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ መሸጋገርን ላበሰረ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።

የጊፋታ በዓል የወላይታን ብሔር ባህል፣ ታሪክ እንዲሁም ቅርስ በዓለም እንዲተዋወቅ ከማድረግ ባሻገር በቱሪዝም ፍሰት ረገድ ያለው ሚና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የበበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ኃላፊዋ አክለዉ ተናግረዋል።

“ጊፋታ” ተራርቀው የከረሙ የሚገናኙበትና አንድነት የሚጠናከርበት፣ አጎራባች ዞኖችና ከሌሎች አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶች ባህላቸውን የሚተያዩበት እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብር የሚፀናበት እንዲሁም ለህዝቦች ሰላምና አንድነት ምሰሶ ነው ብለዋል።

ለጊፋታ ቀደም ተብሎ ተቀማጭ ገንዘብን ጨምሮ በዓይነት በርካታ ነገሮች የሚቆጠብበት መሆኑን ጠቅሰው፤ የቁጠባ ባህል የሚያስተምርና የሚያጠናክር በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የላቀ እንደሆነ አስረድተዋል።

ለበዓሉ ከሚደረግ ዝግጅት የሰውና የእንስሳት መብልና መጠጥ እንዲሁም በበዓሉ ወቅቶች የሚያስፈልጉ ግብአቶች ቀድመው የሚዘጋጁበት የስራ ክፍፍል ያለው መሆኑ ከስራ ባህልና እኩልነት አኳያ አስተዋፅኦው የላቀ እንደሆነም ተመላክቷል።

አስተያዬት ሰጪዎቹም የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል ካለዉ ታሪካዊ ዳራና ጠቀሜታ አንጻር ሁሉም ባለድርሻ ተረባርብ በመሥራት ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ኖሮት በግለት እየተከበረ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ልሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል።

Yoo Yoo Gifaataa

 #ስበር ዜና!! በደምቢዶሎ ሆስፒታል የተጣበቁ ህፃናት ተወለዱ ።  Conjoined Twins birth in  Ethiopia _________________________________________ ...
12/08/2022

#ስበር ዜና!! በደምቢዶሎ ሆስፒታል የተጣበቁ ህፃናት ተወለዱ ። Conjoined Twins birth in Ethiopia
_________________________________________

በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ

• " እንዲህ አይነት ክስተት የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው " - ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ማስተማሪያ ሆስፒታል 2 ጭንቅላት ያለው ህፃን ተወለደ።

የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ በሰጡት ማብራሪያ ህፃኑ ሁለት ጭንቅላት ኖሮት መወለዱን ተናግረዋል።

ዶ/ር ፀጋዬ ፤ በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለፅም ህፃኑ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወለዱን አስረድተዋል።

በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ እና በእናቶች ማህፀን ውስጥ በሚስተናገዱ እንቁላሎች ብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ አብራርተዋል።

በኢኒስቲትዩቱ የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ በበኩላቸው ክስተቱ በመንታ ምድብ የሚመደብ እና የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ እናትም ሕፃኑም በጥሩ_ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via : Telegram Tikva Ethiopia 👏

ከ6 አመታት በላይ  ዕንቅልፍ ያልተኛው ግለሰብ የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ተመዝግበዋል‼️➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ከስድስት አመታት በላይ  ዕንቅልፍ ያልተኛው ኢትዮጵያዊ የአፍሪቃ ድንቃድን...
28/07/2022

ከ6 አመታት በላይ ዕንቅልፍ ያልተኛው ግለሰብ የአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ተመዝግበዋል‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ከስድስት አመታት በላይ ዕንቅልፍ ያልተኛው ኢትዮጵያዊ የአፍሪቃ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙን አስመዘገበ።

እንቅልፍ በአይኑ ከዞረ ስድስት አመት ተኩል እንደሆነው የሚናገረው አቶ ቁምላቸው አሰፋ ጉዳዩ እንግዳ ነገር በመሆኑ የጤና እክል እየፈጠረበት ቢገኝም ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ያለመተኛትን በአፍርካ የድንቃድንቅ መዝገብ ስሙን በማስመዝገብ የአለም ክብረወሰንን ለመስበር ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ነዋሪ የሆነው አቶ ቁምላቸው አሰፋ ለአዲስ ዘመን እንደገለጸው፤ ከሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረ አጋጣሚ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም። የእንቅልፍ እጦት ቢኖርበትም በምሽት መኝታው ላይ አረፍ ለማለት ሲፈልግ ግን የሰውነት ሙቀቱ እንደሚጨምር እና ጎኑን ውጋት ይሰማዋል። እንግዳ ጉዳዩ ችግር እየፈጠረበት ቢሆንም ግን ለረጅም ጊዜ ያለእንቅልፍ የመቆየት የአለም ክብረወሰን ለመስበር አቅዷል።

ለጉዳዩ መፍትሄ ለማምጣት ከዘመናዊ እስከ ባህላዊ ህክምና እንዲሁም ሐይማኖታዊ መፍትሄዎችን መሞከሩን የሚገልጸው አቶ ቁምላቸው፤ ይሁንና እስካሁን ድረስ እንቅልፍ ማግኘት አለመቻሉን ተናግሯል። በተለያዩ ህክምና ተቋማት በሚሄድበት ወቅት ለጊዜያዊ መፍትሄነት የእንቅልፍ መድሃኒት ቢሰጡትም መድሃኒቶቹ ግን እንቅልፉን ሊመልሱለት አልቻሉም። የጉዳዩ እንግዳ መሆን እና የጤና እክል መፈጠሩ እያሳሰበው መሆኑን ያስረዳል።

በዚህም ምክንያት በመጀመሪያዎቹ የእንቅልፍ እጦት ወራት ለጭንቀት በመጋለጡ እራሱንም ለማጥፋት ጭምር ሙከራ አድርጓል። ይሁንና ከተለያዩ ባለሙያዎች የእንቅልፍ እጦት በእራሱ ችግር አለመሆኑን ምክር ስለተሰጠው ጉዳዩን አምኖ በመቀበል ህይወቱን መቀጠሉን ተናግሯል።

አብዛኛውን ምሽት የእጅ ስልኩን በመነካካት እና ቴሌቪዥን በማየት እንዲሁም የተለያዩ ተግባራትን በመፈጸም እንደሚያሳልፍ የተናገረው አቶ ቁምላቸው፤ እንቅልፍ ባያገኝም የዕለት ተዕለት ስራውን በሰላም ከመከወን እንዳላገደው ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር  ለፍጻሜ  አለፉአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና  በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሶ...
21/07/2022

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜው ውድድር አለፉ።

በርቀቱ ኢትዮጵያን ወክለው ከተካፈሉት አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ እና ዳዊት ስዩም ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ ቶለሳ ቦደና ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።

ማሳለጫ መንገድ (Bypass highway) ለወላይታ ሶዶ ከተማ አስፈልጓታል።  ከላሬና -በኦፋ ሴሬ_በኦቶና-ማራ ጫሬ የሚዘልቅ አማራጭ የመተንፈሻ ማሳለጫ መንገድ ሊሠራ ይገባል።=========...
16/07/2022

ማሳለጫ መንገድ (Bypass highway) ለወላይታ ሶዶ ከተማ አስፈልጓታል። ከላሬና -በኦፋ ሴሬ_በኦቶና-ማራ ጫሬ የሚዘልቅ አማራጭ የመተንፈሻ ማሳለጫ መንገድ ሊሠራ ይገባል።
====================
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ደረጃ ከተሞች መካከል በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች የሚትገኝና ከ500,000 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት የደቡብ ኢትዮጵያዋ ፈርጥ እና የዳሞታ ተራራ ፀዳል፣ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባት የኢኮኖሚ ማዕከል፣ የኮንፈራንስና የስልጠና
ማዕከል፣ ወዘተ የሆነችው ወላይታ ሶዶ ከተማ በከተማው ዳር የሚያልፍ ማሳለጫ መንገድ (Bypass highway) የሚያስፈልግባት የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

የማሳለጫ መንገዱ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እስከ ዞን ዋና አስተዳደር በር ድረስ ያለው የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ፣ የትራፊክ አደጋን በመቀነስ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማሳለጥ፣ የትራፊክና የመንገድ ደህንነትን በማሻሻል፣ የከተማውን ገጽታ በማሻሻል፣ ወዘተ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን ከማስገኘት አንጻር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ከተማችን ሰባት የመግቢያና መውጫ በሮች ቢኖራትም አሁን ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ፣ ከህዝብ ብዛት እና የትራፊክ ፍሰት መጨመርን መነሻ በማድረግ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን በማሻሻል ከላሬና ቀበሌ ጀምሮ ከአርባምንጭ_ ሶዶ ከሚዘልቀው አውራ ጎዳና በስተምስራቅ እና ምዕራብ በኩል ሁለት የማሳለጫ መንገዶችን መገንባት አለበት።

የወላይታ ሕዝብ ለሠርጉ ቀን ስለቆረጠ ባለሀብቶቻችንና ነጋዴዎቻችን ግንባታ ሂደት ላይ ያሉትንና የቆሙ ሕንጻዎችን በአፋጣኝ ብታጠናቅቁ፤ የከተማ አስተዳደሩም የሠርጉን እንግዶችን የሚመጥን ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት የማሟላት ሥራ 24/7 በመሥራት ቅድመ ዝግጅቱን ካሁኑኑ ማጠናቀቅ ያስፈልጋል።

Tekle Toma

ሀገርን ከገጠማት ፈተና ለማላቀቅ የተመራቂ ተማሪዎች ሚና ከፋተኛ ሊሆን ይገባል  - ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴሐምሌ 9/2014 (wolaita TV) ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፉት ሁለት...
16/07/2022

ሀገርን ከገጠማት ፈተና ለማላቀቅ የተመራቂ ተማሪዎች ሚና ከፋተኛ ሊሆን ይገባል - ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ሐምሌ 9/2014 (wolaita TV) ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፉት ሁለት አመታት ሀገሪቱ የገጠማት ችግር ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ይህን ፈተና ለመሻገር የተመራቂ ተማሪዎች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በርካታ ንፁሀን ዜጎች ለረሃብ ፣ ለጦርነት ፣ለመፈናቀል በአሳዛኝ ሁኔታ መዳረጋቸውን ያወሱት ፕሬዝዳንቷ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ሁኔታ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳዘነ መሆኑን አብራርተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ ይህንና መሰል በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ችግሮቾ እና እንግልቶችን በመረዳት የመፍትሔ እና የሰላም አጋር መሆን እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች ስራን ከመንግስት ብቻ ባለመጠበቅ ራሳቸውን ሥራ ፈጣሪ በማድረግ በግልና በቡድን በመደራጀት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

በግላቸው እና በቡድን ተደራጅተው ሥራ ፈጣሪ ለሚሆኑ ተማሪዎች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍና የመስሪያ ቦታ እንደሚያመቻች አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ለተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም በከፍተኛ ጥረትና ትጋት ላስተማሯቸው ቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

29/10/2014ዓ/ም  ሁምቦ ወረዳ  ከወላይታ ሶዶ  ወደ አርባምንጭ የሚጓዝ ሲኖትራክ መኪና  አደጋ በመከሰት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።በጉዳቱ የ2 ሰው  ሾፈሩና፣ ረዳት  ሕይወት...
06/07/2022

29/10/2014ዓ/ም ሁምቦ ወረዳ ከወላይታ ሶዶ ወደ አርባምንጭ የሚጓዝ ሲኖትራክ መኪና አደጋ በመከሰት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።
በጉዳቱ የ2 ሰው ሾፈሩና፣ ረዳት ሕይወት ወድያውኑ ቀጥፏል።
በክርምት አሽከርካርዎች ጥንቃቄ ይሰጥ!!

የሚገርም ነገር በደቡብ አፍሪካ ነው አሉ 🙊🤷‍♂️አንዲት ደቡብ አፍሪካዊ ሴት 'ከራሷ በዕድሜ የምትበልጥ ' የምትመስል ልጅ ወለደች።  የ20 ዓመቷ የአእምሮ ችግር ያለባት ይህች እናት በደቡብ...
15/06/2022

የሚገርም ነገር በደቡብ አፍሪካ ነው አሉ 🙊🤷‍♂️

አንዲት ደቡብ አፍሪካዊ ሴት 'ከራሷ በዕድሜ የምትበልጥ ' የምትመስል ልጅ ወለደች። የ20 ዓመቷ የአእምሮ ችግር ያለባት ይህች እናት በደቡብ አፍሪካ ምስራቅ ኬፕ ግዛት የምትኖር ስሆን ከወለደችም በኃላ በሕይወት ለመኖር አልታደለችም ተብሏል ።

Address

Adis Abeba
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Damot Sore Media-press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share