የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ /Boloso Sore Prosperity Party

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ /Boloso Sore Prosperity Party

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ /Boloso Sore Prosperity Party Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ /Boloso Sore Prosperity Party, Media, Boloso Areka, Sodo.

ሰላማችን የህልውናችን ቁልፍ፤ የብልፅግናችን መሰረት !!የሀገርን ሉዓላዊነትና የህዝባችንን አንድነት ለማስጠበቅ መስዋዕትነት ጭምር ለመክፈል ወደ ኋላ የማንል ኢትዮጵያውያን ሙሉ አቅማችንን አቀ...
17/04/2024

ሰላማችን የህልውናችን ቁልፍ፤ የብልፅግናችን መሰረት !!

የሀገርን ሉዓላዊነትና የህዝባችንን አንድነት ለማስጠበቅ መስዋዕትነት ጭምር ለመክፈል ወደ ኋላ የማንል ኢትዮጵያውያን ሙሉ አቅማችንን አቀናጅተን ድህነት ላይ ለመዝመት ለዘላቂ ሰላማችን የማንከፍለው ዋጋ አይኖርም።

ከጦርነት አዙሪት በመውጣት ሰላማዊት ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ማውረስ ያለፈው ትውልድ የባከነ ቁጭት የዚህ ትውልድ ደግሞ ምርጫውና ተስፋው ነው።

ሰላማችን የህልውናችን ቁልፍ የብልፅግናችን መሰረት በመሆኑ ከግጭት ጠማቂዎች ድግስ ባለመታደምና ሁሉም የሰላም ዘብነቱን በማጠናከር ስለ ሰላም መዘመር እንዲሁም ከፀጥታ ሀይላችን ጎን በመሰለፍ አስፈላጊውን ዋጋ መክፈልን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

ለሰላም የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ የህይወት መስዋዕትነትን፣ የንብረት ውድመትን፣ መጎሳቆልን፣ መሰደድን፣ ተስፋ መቁረጥን የመሳሰሉ የጦርነትና ተያያዥ ችግሮችን ስለሚያስቀር ስለሰላም የቱንም ያህል ብንፈጥን የቱንም ያህል መስዋዕትነት ብንከፍል ያንስ ይሆናል እንጂ ስለማይበዛ ሁሉም የፓርቲያችን አባላት፣ ደጋፊዎች እና መላው ህዝባችን ሰላምን በኑሯችን ሁሉ ልንተረጉመው ይገባል።

የወላይታ ዞን አደረጃጃት ዘርፍ ኃላፊዎች እና የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አመራሮች ከ200 ሺህ በላይ የሚዲያ ተከታዮች ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቀሉ ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ ...
17/04/2024

የወላይታ ዞን አደረጃጃት ዘርፍ ኃላፊዎች እና የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አመራሮች ከ200 ሺህ በላይ የሚዲያ ተከታዮች ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቀሉ

ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 9/2016 የወላይታ ዞን አደረጃጃት ዘርፍ ኃላፊዎች እና የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አመራሮች ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቅለዋል።

አሁን ያለውን የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ የሚሻገር ጠንካራ አመራርና አባሉን ለማፍራት ንቅናቄው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተገልጿል።

እንደዞን ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ ዘመቻ በይፋ ተጀምሮ እየተሰራ ይገኛል።

ንቅናቄው በዋናነት ፓርቲያችን ብልፅግና አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ዳር ለማድረስ የዲጂታል ሚዲያው አዎንታዊ ሚናን ያበረክታል። ለዚህም መላው አመራርና አባል ለማሳተፍ ያለመ ነው።

ንቅናቄው ግቡን እስከሚመታ ድረስ በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ለተግባሩ ስኬታማነት ሁሉም የፓርቲው አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች የጀመሩትን የነቃ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የሁምቦ ወረ...
17/04/2024

ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የሁምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ

ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዚያ 09/2016 በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ያልተቋረጠ የባህር ዛፍ ነቀላ ከእርሻ ማሣ እና ከዉሃ ምንጮች ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ዘመቻው በንቅናቄ ከተጀመረበት ጀምሮ በእርሻ ማሳ አጠገብ የሚገኝ ባህረዛፍ በሰብል ምርት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖን በሚመለከት የአርሶአደሩ ግንዛቤ እየተለወጠ እንደሆነ የገለፁት የሁምቦ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደመ፣ የአከባቢውን ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችንና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ እንዳልሆነ አሳሰቡ።

አቶ ተገኝ ታደመ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በቦሳ ዋንቼ ቀበሌ ከአርሶ አደር እርሻ ማሳ አጠገብ የሚገኘውን እና በምርት እና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያደረሰውን ባህር ዛፍ በመንቀል በምትኩ በማሳው የሙዝ ተከላ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በወረዳዉ የግብርናዉን ዘርፍ ለመደገፍ የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ እና ዉሃ ምንጮች አቅራቢያ ለማንሳት ታስቦ የተጀመረዉ ሥራ በአርሶ አደሩ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትንና ድጋፍ ያገኘ ተግባር ሆኗል።

በዚህም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለ ከሳይንሳዊ እዉቅና በእርሻ መሃል እና ዉሃ ምንጮች ላይ ተተክለዉ ለምርትና ምርታማነት ጸር በመሆን አምራች አርሶ አደርን ለርሃብ እያጋለጠ ያለዉን ባህር ዛፍ ከእርሻ ማሳ የማስወገድ ሥራ ተያይዘዋል።

አንድ የባህር ዛፍ ብያንስ የማገር ደረጃ ለመድረስ የሚፈጀዊ ጊዜ፣ ከከርሰምድር የሚመጠዉ የዉሃ መጠን እና በሥሩ አማካኝነት የሚወስዳቸዉ ማዕድናት እጅግ በጣም ለእርሻ ማሳ አስጊነቱን የሚገልጡ ናቸዉ።

እንደ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለጻ በዘንድሮው ምርት ዘመን በወረዳው ከ43 ሄ/ር በላይ ባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ለመንቀል ታቅደው ወደ ተግባር በመግባት በሁሉም ቀበሌያት በአጭር ጊዜ ውጤታማ ተግባር ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በዛሬው እለት በቦሳ ዋንቼ ቀበሌ በንቅናቄው የተሳታፉ አርሶአደሮችም ለምርትና ምርታማነት እንዲሁም ለምንጭ ማጎልበት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ባህር ዛፍ ከእርሻ ማሳ ዘመቻውን ሳይጠብቁ ለመንቀል ተስማምተዋል።

በዘመቻው የሁምቦ ወረዳ ም/አስተዳደር እና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደመን ጨምሮ ለሎች የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ደጋፊ አመራር አቶ ዘላለም ለማ እና ለሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል በማለት የወረዳው ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ዘግቧል።

የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።ሚያዝያ 8፤2016 ዓ.ም የዞኑ ምክትል አስተዳ...
16/04/2024

የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ሚያዝያ 8፤2016 ዓ.ም የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅት ተመልክተዋል።

በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበውን ተጨባጭ ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ምክትል ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል።

በወረዳው በበልግ እና በመኸር ወቅት ብቻ 11 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ብቁ ዕቅድ ተዘጋጅቶ እየተሠሩ ያሉና የተከላ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ተሰፋ ሰጪ እንደሆነም አቶ መስፍን ጠቁመዋል።

ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠ በመሆኑ ዝግጅቱ የተጠናከረ ሊሆን እንደሚገባም አመላክተዋል።

በተባበረ ክንድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል እንደሀገር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ትልቁ ማሳያ ሊሆን የሚችል ነው ብለዋል።

ለሚያዝያ አረንጓዴ አሻራ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ኃይለገብርኤል ካሣዬ ተናግረዋል።

በ2016 በጀት ዓመት አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅት በበልግና በመሄር የተለያዩ ችግኝ ዓይነቶች ለመትከል መታቀዱንም አክለዋል።

በወረዳችን ባሉ በተለያዩ ችግኝ ጣቢያ 11.5 ሚሊዮን ችግኝ በማፊላት ለተከላ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የወረዳው አከባቢና ደን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳርጌ ላቃሴ ጠቁመዋል።

ለተከላ ከተዘጋጀው 6 ሚልዮን ለበልግና 5 ሚልዮን ለመኼር እንደሆነም የተገለፀ ሲሆን በሁሉም ቀበሌ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ የሚያስችል የጉድጓድና የተለያየ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም የጽ/ቤቱ መረጃ ይጠቁማል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቀሉ ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ...
16/04/2024

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቀሉ

ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ለማፍራት በተጀመረው ንቅናቄ ተቀላቅለዋል።

ንቅናቄውን የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ፣ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አለማየሁ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ በጋራ በመሆን አስጀምረዋል።

አሁን ያለውን የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ የሚሻገር ጠንካራ አመራርና አባል ለማፍራት እጅግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጿል።

እንደዞን ከ200 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ለማፍራት ዓላማ ያደረገ ዘመቻ በይፋ ተጀምሮ እየተሰራ ይገኛል።

ንቅናቄው በዋናነት ፓርቲያችን ብልፅግና አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ወደ ዳር ለማድረስ የዲጂታል ሚዲያው አዎንታዊ ሚናን ያበረክታል። በመሆኑም ንቅናቄው መላው አመራርና አባል ለማሳተፍ ያለመ ነው።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ  የሚጠቀም የፓርቲ አመራርና አባል ቁጥር ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።ሚያዝያ 8፤2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ...
16/04/2024

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ የሚጠቀም የፓርቲ አመራርና አባል ቁጥር ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

ሚያዝያ 8፤2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በሴቶች ሊግ መሪነት የፓርቲ ማህበራዊ ድረገጾች ተከታይ ብዛት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በንቅናቄው መድረክ ሴት አመራሮች፣ የቀበሌ ሴቶች ሊግ እና ተፀዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሴቶች ተሳትፈዋል።

የንቅናቄው መድረክ ማህበራዊ ድረገጾችን ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል አጠቃላይ የፓርቲ አመራሮች እና አባላት በየደረጃው ያሉ የፓርቲ ገጾችን ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

ሴቶች በሀገር መንግሥት ግንባታ ያበረከቱት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ በቴክኖሎጂውንም ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲጠቀሙ የተለመደውን በጎ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ መልዕክት ተላልፏል።

በተያያዘ እንደሀገር የተጀመረውን ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከምግቤ በሚል ሀሳብ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እንደወረዳ ሴቶቹ የሚዲያ ንቅናቄውን እያከናወኑ የሌማት ትሩፋት ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ወሳኝ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ለሊቃ ትምህርት ቤት እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ (1) ወር ደመወዝ ለመለገስ ቃል ገቡ።ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 ዓ....
16/04/2024

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ለሊቃ ትምህርት ቤት እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ (1) ወር ደመወዝ ለመለገስ ቃል ገቡ።

ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ለሊቃ ትምህርት ቤት እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ (1) ወር ደመወዝ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

አመራሮቹ ለሊቃ ትምህርት ቤት እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ከወር ደመወዝ ተቆርጦ ገቢ እንድሆን ወስነዋል።

የወላይታ ልማት የኔም ነው፤ አሻራዬ ማረፍ አለበት፣ሊቃ ትምህርት ቤት በመደገፍ ወደ ልህቀት ማዕከል የማድረስ እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ንቅናቄ መሳተፍ ታሪካዊ ዕድል ጭምር ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ገንዘቡ ከወር ደመወዝ ተቆርጦ በአግባቡ ለልማት ማህበሩ እና አንድ መጻሐፍ ለአንድ ተማሪ ዓላማ በተገቢው መተላለፍ እንደሚገባ አስገንዘበዋል።

ጠንካራ ፓርቲን ለመትከል አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፦ ወ/ሮ መስከረም ደገፉቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ የ...
16/04/2024

ጠንካራ ፓርቲን ለመትከል አደረጃጀቶችን የማጠናከር ስራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፦ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ

ቦሎሶ ሶሬ ፤ ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ የዘጠኝ ወር የዘርፉን አፈጻጸም ገምግሞ በቀሪ ወራት ዕቅድ ላይም መክረዋል።

ማጠቃለያ ሀሳብና ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ለፓርቲው ጀርባ አጥነት መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዘርፉ በፓርቲ መሪነት የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሳለጥ ሞተር እንደሆነም ወ/ሮ መስከረም ገልጸዋል።

የተከለሰ ዕቅድ ማዘጋጅትና የሚሰሩ ተግባራትን መለየት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ መስከረም የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አቅዶ መስራት ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ከአባል ጀምሮ የሚዘና ስርዓቱ መጠናከር እንደሚገባ ያሳሰቡት ወ/ሮ መስከረም ጥራት ያለው አመራር፣ አባልና አደራጃጀት መፍጠር እንደሚገባም አመላክተዋል።

የፓርቲው ህልውናን የሚያስጠብቅ ጠንካራ ተቋም መገንባት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ መስከረም መሠረታዊ ድርጅትና ህዋሳት የማጠናከር ስራ መጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጠራ አመራርና አባል ለመፍጠር በአመለካከት ላይ መስራት እንደሚገባና የኮር አመራር የመፍጠር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ክፍተቶችን በማረም ጠንካራ ፓርቲን ለመገንባት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአሠራርና አደረጃጀት መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ዘካሪያስ መመሪያው ተግባራዊ ለማድረግ ንቅናቄ ስራ ተሰርቶ የተግባር አካል ተደርጎ መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የፓርቲው ሀብት አሰባሰብ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ያሳሰቡት አቶ ዘካሪያስ የታቀደውን ግብ ለማሳካት ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የዘርፍ ኃላፊዋ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ጋር በቀጣይ በ10 ቀናት ዕቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በመድረኩ የፓርቲው ስራ አመራር አካላት፣ የወረዳና ከተማ የዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ከዞን የመጡ ባለሙያዎች ...
16/04/2024

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ከዞን የመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ ነጋዴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠና መድረክ የተገኙ አሰልጣኞች ሰልጣኞች ግብርን በደንብና መመሪያ መሠረት ወቅቱን ጠብቀው እንድከፍሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ሰልጣኞችም ግብርን ህግን ተከትለው በወቅቱ መክፈል የዜግነት ግዴታ መሆኑን አምነው አስተያየት ሰጥተዋል።

የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት አለበት፦ አቶ ተመስገን አለማየሁወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ "የማህበረሰብ መ...
16/04/2024

የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት አለበት፦ አቶ ተመስገን አለማየሁ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ "የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከል በሚል መሪ ቃል ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁ የኤች አይቪ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

በሽታውን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የጋራ አቋም መያዝ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የበሽታውን ሰርጭት ለመታደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በትኩት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የኤች አይቪ/ኤድስ በሽታ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ ያለውን መቀዛቀዝ ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ብርቱ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ከተደቀነው አደጋ ህዝባችንን የመከላከል ስራ ቀዳሚ አጀንዳችን ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የሚኒሚዲያ እና የተለያዩ ውይይት መድረኮች መጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመስገን ዛሬ የተጀመረው ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን ርብርብ መደረግ ይገባል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ የኤች አይቪ ስርጭትን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነቱን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በሽታውን ለመከላከል የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፀጋዬ መከላከል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

አሁን በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው መዘንጋቱ በሽታው እንዲባባስ አድርጓታል ያሉት አቶ ፀጋዬ ህብረተሰቡ የኤች አይቪ አስከፊነቱ በሚገባ በመረዳት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

"ቴክኖሎጂ ላይ የምንሠራቸውን ሥራዎች ለማሳካት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክሂሎት ልንታጠቅ ይገባል" አቶ ምህረቱ ሳሙኤል የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላ...
16/04/2024

"ቴክኖሎጂ ላይ የምንሠራቸውን ሥራዎች ለማሳካት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክሂሎት ልንታጠቅ ይገባል" አቶ ምህረቱ ሳሙኤል የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 09/8/2016 የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ዘርፍ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ቴክኖሎጂ ላይ የምንሠራቸውን ሥራዎች ለማሳካት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክሂሎት ልንታጠቅ ይገባል የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ሳሙኤል ገለጹ።

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ሳሙኤል ይህን የተናገሩት መምሪያው ባዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መክፈቻ ባደረጉበት ንግግራቸው ነው።

ሳይንስ ያለፈጠራ አይታሰብም ያሉት አቶ ምህረቱ በፈጠራ የታገዘ ልማት ለማምጣት ታዳጊ ፈጣሪዎችን የማብቃት፣ የመደገፍና የማበረታታት ሥራ አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ምህረቱ አክለውም ቴክኖሎጂ ላይ የምንሠራቸውን ሥራዎች ለማሳካት ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክሂሎት ልንታጠቅ ይገባል ሲሉ የሥልጠናውን አስፈላጊነት አስረድተዋል።

ሠልጣኞችም በሥልጠናው ያገኙትን ክሂሎት እና ዕውቀት ወደተግባር ለመለወጥ እንዲተጉ ጠይቀው በኃላፊነት ሥልጠናውን እንዲከታተሉም አሳስበዋል።

በሥልጠናው የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ማኔጅመንት የትምህርት እና ጤና መምሪያዎች፣ የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ተወካዮች፣ የወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎች እና የአቅም ግንባታ ዳይረክቶሬት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመታገል የሀገራችንን ብልፅግና እውን እናድርግ! ሰላምን እውን የማድረግም ሆነ ሰላምን  የማጣት  ወሳኙ እኛው ራሳችን ነን።  ዛሬ በእጃችን ያለው ሰ...
16/04/2024

ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመታገል የሀገራችንን ብልፅግና እውን እናድርግ!

ሰላምን እውን የማድረግም ሆነ ሰላምን የማጣት ወሳኙ እኛው ራሳችን ነን። ዛሬ በእጃችን ያለው ሰላም ነገም በአስተማማኝ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው ሁሉም ለሰላም ተግቶ ሲሰራና ሰላምን የሚያፈርሱ ነገሮችን ያለ ምህረት ሲታገል ብቻ ነው፡፡

ሰላምን ከሚያደፈርሱ ነገሮች አንዱ ደግም ጽንፈኝነት ነው። ጽንፈኝነት ከመደመር ሳንካዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ሲሆን የራስን ፍላጎት በሌሎች ላይ የመጫን ወይም የማስገደድ አባዜ የተጠናወተው ጫፍ የሚይዝ የኋላቀርነት መገለጫ ነው፡፡

መነሻው በተናጠል ፍላጎቷቶች ላይ የሚመሰረትና የሌሎችን መስተጋብሮች ለመቀበል የሚቸገር ነው።

ኢትዮጵያ ደግም ብዝሃ ሀሳብ፣ ብዝሃ ባህል፣ ብዝሃ ቋንቋና ብዝሃ ሃይማኖት ባለቤት ናት።

በመሆኑም የአዲሱ የብልፅግና እሳቤ መሰረት የሚያደርገው የመደመር ትውልድ አስተሳሰብ ትርክቱ የትስስር ትርክት፣ የአብሮነት ትስስር ነው፤ በማናቸውም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች እኔም፣ እኛም፣ በአጠቃላይ ሁላችንም በጋራ መጠቀም አለብን ማለት መቻል አለብን።

በመሆኑም ከጽንፈኝነት በመራቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ እና መንከባከብ አማራጭ የሌለው የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ሰላም ከሆነች የምንናፍቀውን ብልጽግና በአጭር ጊዜ እውን ከማድረግ የሚከለክለን ምድራዊ ሀይል አይኖርም።

ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመከላከል የሀገራችንን ብልፅግና እውን እናድርግ!

"ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል...
16/04/2024

"ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በምሰረታ ፕሮግራሙ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በሕዝቦች ፍቃድ መስርተን በርካታ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እየሰራን በሚንገኝበት በዚህ ወቅት በክልሉ የቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጉባኤ ማካሄዱ ለክልሉ መንግስት እና ህዝብ አስደሳች ዜና ነው ብለዋል።

ቀይ መስቀል "ለሕዝቦች ከሕዝቦች በሕዝቦች" የሚል መርህ ለአለም ሕዝብ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሰው ልጆችን በቅንነት ለማገልገል ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በሚል የደከመውንም፣ የተራበውንም፣ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋ፣ በጦርነት ለተጎዳው ለሁሉም የሰው ልጆች እኩል የሚያገለግል ማህበር መሆኑን ገልፀዋል።

የማህበሩ መመስረት ክልሉ መደጋገፍን መርህ አድርጎ ለሚሰራው ስራ አጋዥ እንደሆነ ጠቅሰው በአዲስ መልክ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይመስቀል ማህበር በመመስረቱ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ማህበሩ ህዝብን በአግባቡ ማገልገል እንዲችል ጠንካራ አባላትን በማፍራት በተጠናከረ መንገድ ማደራጀት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በምስረታ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች መገተቸዉን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላከታል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ በመጀመሪያ ዙር ያስለጠናቸው 1 ሺህ 35 እጩ የፖሊስ መኮንኖች በወላይታ ሶዶ ከተማ እያስመረቀ ነውወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ...
16/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ በመጀመሪያ ዙር ያስለጠናቸው 1 ሺህ 35 እጩ የፖሊስ መኮንኖች በወላይታ ሶዶ ከተማ እያስመረቀ ነው

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ በመጀመሪያ ዙር ያስለጠናቸው 1 ሺህ 35 እጩ የፖሊስ መኮንኖች በወላይታ ሶዶ ከተማ እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃው ስነስርዓት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ጨምሮ ሌልች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

፡ህብረተሰቡ የኤች አይቪ ስርጭት እየጨመረ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛ አሳሰቡወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ጤና...
16/04/2024

፡ህብረተሰቡ የኤች አይቪ ስርጭት እየጨመረ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛ አሳሰቡ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016 የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ "የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከል በሚል መሪ ቃል ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

ንቅናቄው መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛ ኤች አይቪ ላለፋት ሶስት አስርት ዓመታትና ከዚያ በላይ የሀገራቱ ዋነኛ የጤና ችግር ምክንያት ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ባለፉት ዓመታት የበሽታውን ስርጭት፣ ህመም እና ሞትን ከማስቀረት አኳያ በርካታ ስራዎች መሰራቱን የገለጹት አቶ አሳምነው አሁን ላይ መዘንጋት እየታየ ይገኛል ብለዋል።

በሽታው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እንደሚያስከትልም አስገንዝበዋል።

በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ በተለይም የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት፣ የፈጻሚ ባለሙያውን ቴክኒካል ድጋፍ እና የህዝቡ ባለቤትነት ያካተተ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት በተካሄደው የኤች አይቪ ምርመራ 176 አዳዲስ ሰዎች ኤች አይቪ በደማቸው መገኘቱን ገልጸዋል።

በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ድጋፍ እንደሚጠይቅ አመላክተዋል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁ፣ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላን ጨምሮ የዞኑ አጠቃላይ አመራር፣ የወረዳና ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ወቅታዊ ተግባራት ያለበት ደረጃ ተገመገመሚያዝያ 08/2016ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።በመድረክ...
16/04/2024

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ወቅታዊ ተግባራት ያለበት ደረጃ ተገመገመ

ሚያዝያ 08/2016ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረክ ተገኝተው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኃይለገብርኤል ካሳዬ እንደገለጹት በወረዳ ውስጥ እየተሰበሰቡ ያሉ መደበኛም ሆነ ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ፣ ወላይታ ሊቃ ት/ቤት ና አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ የሚደረግ ድጋፍ እና አጠቃላይ የበልግ ሥራ ያለበት ደረጃ በትኩረት መሠራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

አክለውም በየቀበሌያት የተመደቡ ደጋፊ የወረዳ አመራር አካላት ከላይ በተነሱ ነጥቦች ላይ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ ትኩረት ሰጥተው በጥልቀት መሥራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት ይገባል ያሉት አቶ ኃይለገብርኤል ለዚህም የተማሪ መማሪያ መጽሐፍ ለማሳተም የተጀመሩ ንቅናቄ ተግባር አጠናክረን መሠራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ሞሊሶ በበኩላቸው በየቀበሌያት ያሉ የፓርቲ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የህብረተሰብን ፖሌቲካዊና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ እንዳለብን ተናግረዋል።

በጉድለት የታዩ ተግባራትን በፍጥነት አርመን ጥንካሬዎችን አጎልበትን የፓርቲ እና የመንግሥት ተግባራትን ከግብ ለማድረስ ሊንሰራ እንደሚገባ አበክረው ተናግረዋል።

ከህብረተሰብ ዘንድ የሚነሱ የልማትና መልካም አሰተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የገቢ አቅማችን ማሳደግ እንደሚገባ የገለፁት አቶ መለሰ ለዚህም አመራሩ በቁርጠኝነት መሠራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

በስብሰባው የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት በተነሱ ነጥቦች ላይ በትኩረት ሰርተን ጉድለት የታዩ ተግባራትን አርመን ጥንካሬዎችን አጎልብተን መጓዝ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የቀድሞ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ምክትልና URRAP ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ በረከት በቀለ አድስ ለተሾሙት ለአቶ አጥናፉ ይገዙ የሥራ ርክብክብ አድርገዋል።       ...
16/04/2024

የቀድሞ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ምክትልና URRAP ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ በረከት በቀለ አድስ ለተሾሙት ለአቶ አጥናፉ ይገዙ የሥራ ርክብክብ አድርገዋል።

መልካም የሥራ ጊዜ እንድሆንላቸው ተመኘን !

የቀድሞ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ከበደ ካምፔሶ አድስ ለተሾሙት ለአቶ አያኖ ኦሮቤ የሥራ ርክብክብ አድርገዋል።          መልካም የሥራ ጊዜ እን...
16/04/2024

የቀድሞ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ከበደ ካምፔሶ አድስ ለተሾሙት ለአቶ አያኖ ኦሮቤ የሥራ ርክብክብ አድርገዋል።

መልካም የሥራ ጊዜ እንድሆንላቸው ተመኘን !

Address

Boloso Areka
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ /Boloso Sore Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category