በወላይታ ሶዶ ከተማ የዋዱ አምባ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች የፌደሬሽን፣የክንፍና የማህበር አደረጃጀት መዋቀር።

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • በወላይታ ሶዶ ከተማ የዋዱ አምባ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች የፌደሬሽን፣የክንፍና የማህበር አደረጃጀት መዋቀር።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የዋዱ አምባ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች የፌደሬሽን፣የክንፍና የማህበር አደረጃጀት መዋቀር። To develop youth mind poletically, economically and socially to stand for their own country they must have right mind-set.

10/09/2025
10/09/2025
10/09/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 8 መቶ 53 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 8 መቶ 53 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ርዕሰ መስትዳድሩ እንደገለጹት፤ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው።

የህግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የይቅርታው ተጠቃሚዎች ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ፤ በጤና ችግር፤ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረዉ የታሰሩ እንዲሁም ከተፈረደባቸው ሲሶ (1/3) እና ከግማሽ (1/2) በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ይቅርታው ከተደረገላቸው 8 መቶ 53 የህግ ታራሚዎች መካከል:- 8 መቶ 41 ከእስር የሚፈቱ ሲሆን፥ ቀሪ 12 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑን ርዕሰ መስትዳድሩ ጨምረው ገልጸዋል።

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 54 ሴቶች ሲሆኑ፥ 7 መቶ 99 ደግሞ ወንዶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።

ርዕሰ መተዳድሩ የይቅርታው ተጠቃሚ የሆኑ የህግ ታራሚዎች የይቅርታን እሴት ተላብሰው ሰላም ወዳድ፣ ለሕግ ተገዥና አምራች ዜጋ በመሆን የበደሉትን ህብረተሰብ በማገልግል በልማት ልክሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም በይቅርታ የተለቀቁት የህግ ታራሚዎች በፈፀሙት ጥፋት የተፀፀቱና በአግባቡ ታርመው የወጡ መሆኑን በመረዳት መልካምና አምራች ዜጋ ይሆኑ ዘንድ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

10/09/2025

የምናከብረው የዓመትን መለወጥ ብቻ አይደለም የታሪክን መለወጥ ጭምር ነው:-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ያለፈው ዓመት ፈጣሪ ከጎናችን፣ ስኬት በደጃችን መሆኑን ያየንበት ዓመት ነበር፡፡ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ይሄንን ይመሰክራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ያህል ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንን ያህል ሕዝብ ይዘን በትጋት ከሠራን፣ ከዚህ በላይ ድል ልናሳካ እንደምንችል ምስክራችን የሕዳሴ ግድብ ነው፡፡

ከእርግዝና ወራት ሁሉ እጅግ አስቸጋሪዎቹ፣ እጅግ አስፈሪዎቹ እና እጅግ ፈታኞቹ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት ናቸው ይባላል፡፡ በሕዝብ ልብ ውስጥ ለዘመናት የተጸነሰውን የሕዳሴውን ግድብ ኢትዮጵያ እንድትወልደው ብዙ ፈተናዎችን መሻገር ግድ ነበር፡፡ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትን ማለፍ ይገባ ነበር፡፡ አያሌ አስፈሪ ተግዳሮቶችን መቋቋም ወሳኝ ነበር፡፡ በተለይም የመጨረሻዎቹ ጊዜያት ወገብን አሥሮ፣ ሐሞትን አምርሮ፣ ወኔን ቋጥሮ፣ ወጥመድን ሰብሮ፣ ሞትን ተሻግሮ መሄድ የሚያስፈልግባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ከፈጣሪ ጋር፣ በሕዝባችን ጽናት፣ በፕሮጀክት ሠራተኞቻችን ብርታት፣ በጸጥታ አባሎቻችን መሥዋዕትነት ያን ሁሉ አልፈን ለምርቃቱ በቅተናል፡፡

የምናከብረው የዓመትን መለወጥ ብቻ አይደለም፡፡ የታሪክን መለወጥ ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ገጽታ፣ የኢትዮጵያ ትርክት፣ የኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ቁመና ተቀይሯል፡፡ ቀደምቶቻችን ሲመኙት፣ አያቶቻችን ሲያስሱት፣ አባቶቻችን ሲጠብቁት፣ እኛ ስንታገልለት የነበረው የኢትዮጵያ ማንሠራራት እውን ሆኗል፡፡ ይሄ ለሺ ዘመን የከፍታ ጉዟችን መነሻ እንጂ መዳረሻ አይደለም፡፡ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም፡፡ እኛ በዐቅምና በአቋም ከተደመርን፣ ሀገራችን ባለ ብዙ ጸጋ ናት፡፡ ለአፍሪካ እና ለዓለም የሚተርፍ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ተፈጥሯዊ ሀብት ሞልቷታል፡፡

2018 የኢትዮጵያን ማንሠራራት የበለጠ ሥር እና መሠረት የምናስይዝበት ዓመት ነው፡፡ በአንድ እጃችን ፈተናዎቻችንን እየተቋቋምን፣ በሌላው እጃችን ታሪካችንን እየቀየርን እንጓዛለን፡፡ ንሥር ከምድር ሲነሣ ብዙ ወፎች እና ነፍሳት አብረውት ሊነሡ ይችላሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም አብረውት ይበራሉ፡፡ የተወሰነ ሰዓትም ሊሸፍኑት ይደርሳሉ፡፡ የበለጠ ወደ ላይ በመጠቀ ቁጥር ግን ብዙዎቹ ወደታች ይቀራሉ፡፡ በመጨረሻም በሕዋው ላይ የሁሉንም ታሪክ እየተመለከተ ንሥር በድል መጓዙን ይቀጥላል፡፡

እኛም ለኢትዮጵያ ንጋት እና ምጥቀት ያስፈልገናል፡፡ 2018 የኢትዮጵያ ታላቅነት የበለጠ እየነጋ፣ የበለጠ እየበራ፣ የበለጠ እየፈካ የሚሄድበት ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብን ባየን ቁጥር የኢትዮጵያን አይበገሬነትና ቻይነት እናስታውሳለን፡፡ ሐይቁን ባየን ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያን ንጋት እናስባለን፡፡ “ንጋት ሐይቅ” የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ ግድቡ እስካሁን የነበረውን ይናገራል፡፡ ሐይቁ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ያበሥራል፡፡

ንሥር ከትንሽ ከትልቁ ጋር በሆነ ባልሆነው አይከራከርምም፤ አይነጋገርም፡፡ ወደላይ በመጠቀ ቁጥር ፈተናው እየቀነሰ፣ ዐቅሙ እየጨመረ፣ ታሪኩ እየተቀየረ እንደሚሄድ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህም ከግራ ከቀኝ የሚወረወረው እየቻለ ወደ ላይ ይመጥቃል፡፡ እኛም ወደ ላይ ከፍ ባልን ቁጥር ፈተናችን እየቀረ፣ ድላችን እየተጨመረ እንደሚሄድ ዐውቀን፣ አእምሯችንን እና እጆቻችንን ለሥራ ማሰለፍ አለብን፡፡ ኢትዮጵያን የሚቀይራት የልጆቿ ፍጥነትና ፈጠራ ነው፡፡ የዓባይን ታሪክ የቀየረው ሥራ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚቀይረውም ሥራ ነው፡፡

በየቢሮው፣ በየእርሻው፣ በየግንባሩ፣ በየድርጅቱ፣ በየትምህርት ቤቱ፣ በየተቋማቱ ያለን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልባችንን፣ ሐሳባችንን፣ ዕውቀታችንን እና ጉልበታችንን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እናውለው፡፡ ስንሠራ ምን እንደምንቀይር ከሕዳሴው ግድብ አይተናል፡፡ እኛ ለስኬት ስንረባረብ ፈጣሪ ምን ያህል እንደሚረዳን እኛው ምስክር ነን፡፡ የሺ ዘመናትን ጥያቄ እንድንመልስ ኃይል የሰጠ ፈጣሪ፣ የዓመታትንና የወራትን ጥያቄ ለመመለስ አይሳነውም፡፡ 2018 ዓመት ይሄንን ይበልጥ የምናረጋግጥበት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

ዛሬ ዓይኞቻችን ያዩትን ለማየት፣ ጆሮዎቻችንም የሰሙትን ለመስማት እንዲችሉ መሥዋዕትነት ለከፈላችሁት ሁሉ እጅ እንነሳለን፡፡ በሁሉም መስክ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ኢትዮጵያ ታከብራችኋለች፡፡ ከጎናችን የነበራችሁትን ወዳጅ ሀገሮች እና ሕዝቦች ሁሉ በኢትዮጵያ ስም እናመሰግናችኋለን፡፡ ዕድገትና ብልጽግና የቅብብሎሽ ውጤት ነው፡፡ የጀመራችሁ፣ ያስቀጠላችሁ፣ ለፍጻሜ የታገላችሁ ስማችሁን በሕዳሴ ግድቡ ላይ ጽፋችኋል፡፡ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሚዲያ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሞያ፣ ወዘተ. የምትችሉትን ያበረከታችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሆናችሁ በታሪክ ሠፍራችኋል፡፡

ይህ ተጋድሏችን፤ ይህ ትብብራችን፤ ይህ ለብሔራዊ ጥቅም በአንድነት መቆማችን፤ ይህ ለራሳችን፣ በራሳችን፣ ከራሳችን መሥራታችን ነገም መቀጠል አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ ይገባታል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ታላላቅ ሥራዎች ይጠብቋታል፡፡ ይሄንንም አብረንና ተባብረን ልናሳካላት ይገባል፡፡

አዲሱ ዓመት የኢትጵያ ማንሠራራት የበለጠ መሠረት የሚይዝበት እንደሚሆን አምናለሁ::

በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት ይሁን

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም

10/09/2025
10/09/2025
10/09/2025
10/09/2025
10/09/2025
10/09/2025

እንኳን ለ 2018 አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰላም አደረሰን !

የዘንድሮው አዲስ ዓመት በብዙ መልኩ የተለየ ነዉ። በትናንትናው ዕለት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መርቀን ሀገራዊ የማንሰራራት ጉዟችንን በይፋ አስጀምረናል።

ዓመቱ በታደሰ ሀገራዊ ቁመና፣ በአራቱም አቅጣጫዎች በተበሰረ ሀገራዊ የማንሰራራት ልዕልና የተጀመረ ነዉና መላዉ የክልላችን ህዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ/አለን ! የምናከብረው ከዓመት መለወጥ በላይ ትርጉም ያለዉ የገፅታ፣ የትርክት፣ የጂኦ ፖለቲካዊ ቁመና ለዉጥ በመሆኑ የዚህ አኩሪ ታሪክ አካል በመሆናችን ልንኮራ ይገባል።

በተጠናቀቀው ዓመት በክልላችን ሁለንተናዊ የለዉጥ ጉዞ ዉስጥ በርካታ አመርቂ ድሎችን አስመዝግበናል። የተቋም ግንባታችንን እያጠናከርን ህብረ ብሄራዊ የሆነዉ ክልልላችንን የሰላም፣ የመቻቻል እና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በእጅጉ ተግተናል።

አዲሱ ዓመት የለኮስነዉን የማንሰራራት ችቦ ከማቀጣጠል ዉጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ተገንዝበን በመላው ሕዝባችን የተደመረ አቅም የጀመርናቸውን ሀገራዊና ክልላዊ የልማት፣ የሰላም እንዲሁም ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ በላቀ ከፍታ የምናስቀጥልበት ይሆናል።

ትናንት በጉባ እንዳየነዉ ብልጽግና በትዉልድ ቅብብሎሽ እዉን የሚሆን፤ የእያንዳንዱን ዜጋ አስተዋፅኦ የሚፈልግ የለዉጥ ሂደት ነዉ። ሁለተኛው የአርበኝነት ምዕራፍ ደግሞ በእጃችን ይገኛል። ታሪክ ከማዉራት በላይ ታሪክ መስራት እንደምንችልም ለዓለም አሳይተናል።

አዲሱ ዓመት በጀመርነዉ የብልጽግና ጉዞ የክልላችንን ሕዝቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት፣ የእያንዳንዳችንን አሻራ በጉልህ የምንፅፍበት፣ ሰላማችንን የምናፀናበት እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሜ መልካም አዲስ ዓመት !

10/09/2025

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በወላይታ ሶዶ ከተማ የዋዱ አምባ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች የፌደሬሽን፣የክንፍና የማህበር አደረጃጀት መዋቀር። posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share