
05/07/2025
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በህገወጥ መንገድ የተወረሩ ከ3 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን የወል መሬት ወደ መሬት ባንክ መግባቱ ተገለፀ
ዎላይታ ሶዶ፣ሰኔ 28/2017 (ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባኤ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንዳሉት መሬት ለኢኮኖሚ መሠረት ነዉ።
ያለመሬት ብልጽግና ማረጋገጥ እንደማይቻል የገለፁት ኃላፊው፤ ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመከላከል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለዜጎች በፍትሃዊነት ተደራሽ እንዲሆን አመራሩና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ዶክተር መሪሁን አሳስበዋል።
የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ኖህ ታደለ፤ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ጊዜያት በህገወጥ መንገድ የተወረሩ መሬቶችን የመከላከሉ ስራ ዉጤት ማስዝገቡን ጠቁመው፤ ከ3 ሺህ 3 መቶ ሄክታር በላይ የሚሆን የወል መሬት ወደ መሬት ባንክ ስለመግባቱ ጠቁመዋል።
በቀጣይም ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚነሱት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
"መሬት የሀብት ሁሉ ምንጭ ነዉ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚሁ መድረክ፤ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካለት እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
በማንኛዉም ሰዓት ጥቆማና አሰተያየት ለመስጠት
የስልክ መስመራችን ክፍት ናቸው ይደውሉ
ስልክ - 0461809999
0461801609
0964647777
በተጨማሪም ይህንን የፌስቡክ ገጻችንን https://www.facebook.com/wogeta?mibextid=ZbWKwL Follow, Share, Like, በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ለቀጥታ ስርጭት linkኩን ይጫኑ https://zeno.fm/radio/wogeta-fm-96-6-lw1u
ትጋትና ታማኝነት ለብልፅግና!