Deme Dana - ''Unity''

Deme Dana - ''Unity'' Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Deme Dana - ''Unity'', Digital creator, Sodo.

በፈጣሪ ዕርዳታ እና በደጋግ ኢትዮጵያዊያን ቀና ትብብር ዶ/ር  #ቤተል ከ8.5 ሚሊዮን ብር በላይ ተስብስቦላት በሕንድ ሀገር ኒው ዴሊህ ከተማ Rajiv Gandhi Cancer Hospital (...
28/05/2024

በፈጣሪ ዕርዳታ እና በደጋግ ኢትዮጵያዊያን ቀና ትብብር ዶ/ር #ቤተል ከ8.5 ሚሊዮን ብር በላይ ተስብስቦላት በሕንድ ሀገር ኒው ዴሊህ ከተማ Rajiv Gandhi Cancer Hospital ( India's Leading Cancer Care Center) በተሳካ ሁኔታ ሕክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ፌዴራል ድረስ ተሸላሚ የነበረው፣ ባለትዳርና የ4 ሕጻናት አባት የሆነው ርዕሰ መምህር ሁለቱም ኩላሊቶች ሥራ በማቆማቸው ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና 3.5 ሚሊዮን ብር ተጠይቀዋል። ስለሆነም ለዶ/ር ቤተል ወገናዊ አለኝታነታችሁን ያረጋገጣችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን፣ መምህሩን ከሞት እንዲሁም ቤተሰቡን ከመበተን አደጋ እንዲታድጉ በኃያሉ እግዚአብሔር ስም እንማጸናለን።

Mengistu Megiso Menta
👉 CBE፦ 1000150452407

Clinical pharmacy
28/05/2024

Clinical pharmacy

የወላይታ ዞን ምክርቤት ቤት የእስካሁን ተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በክልሉ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 19/2016 የወላይታ ዞን ምክርቤት ቤት የእስካሁን ተግባ...
27/05/2024

የወላይታ ዞን ምክርቤት ቤት የእስካሁን ተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በክልሉ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 19/2016 የወላይታ ዞን ምክርቤት ቤት የእስካሁን ተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በክልሉ ደረጃ 1ኛ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፊኬት ባለቤት ሆኗል።

የክልሉ ምክር ቤት የ2016 አፈጻጸም የመጀመሪያ ዙር የጋራ ምክክር ፎረም በዲላ ከተማ ባካሄደው መድረክ ላይ የወላይታ ዞን ምክር ቤት የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ በክልሉ ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

የዞኑ ምክርቤቱ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የክልሉ ምክርቤት ዋንጫና የማበረታቻ ሰርተፊኬት አበርክተዋል።

የሁምቦ ወረዳ ም/ቤት በክልሉ ውስጥ ካሉ ወረዳዎች አንደኛ በመውጣት የዋንጫና የማበረታቻ ሰርተፊኬት መሆን ችሏል።

የወላይታ ዞን ምክርቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ ወላይታ ዞን በክልል ካሉ 12ዞኖች መካከል 1ኛ በመሆን ዋንጫን ሰርተፊኬት እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን ምስጋና አቅርበዋል።

ለቀጣይም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ እንትጋ ብለው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የወላይታ ዞን አስተዳደር የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በነገው ዕለት የጀግና አቀባበል ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀቀወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 19/2016 የወላይታ ዞን አስተዳደር...
27/05/2024

የወላይታ ዞን አስተዳደር የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በነገው ዕለት የጀግና አቀባበል ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 19/2016 የወላይታ ዞን አስተዳደር የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በነገው ዕለት የጀግና አቀባበል ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

ክለቡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በ2016ዓ.ም የውድድር ዘመን አሸናፊ በመሆኑ እና ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉ ይታወቃል።

ይህን በማስመልከት የወላይታ ዞን አስተዳደር በነገው ዕለት ከሀዋሳ ከተማ የሚመጠውን አርባምንጭ ከተማ ስፖርት ክለብን የጀግና አቀባበል ያደርጋል።

ለዚህም የወላይታ ዞን አስተዳደር አስፈላጊውን ዝግጅት በመጨረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

የወላይታ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ከዲምቱ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንዲያደርግ እና ደስታውን እንዲገልጽ የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርበዋል።

ስፖርት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን እና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር መሆኑን ይታወሳል።

Healthcare
27/05/2024

Healthcare

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deme Dana - ''Unity'' posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share