Tigrai Television Amharic

Tigrai Television Amharic Mekelle-based regional media that disseminates news & programs worldwide via multiple platforms.
(1)

11/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሓምሌ 04/2018 ዓ.ም | | |
----

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሳምንታዊ መልእክት!!==================================በውሸትና ማወናበድ  ብዛት የሚደናቀፍ የትግራይ የመኸተ ትግል የለም!!የትግራይ ህ...
11/07/2026

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሳምንታዊ መልእክት!!
==================================
በውሸትና ማወናበድ ብዛት የሚደናቀፍ የትግራይ የመኸተ ትግል የለም!!

የትግራይ ህዝብ እስከአሁን ድረስ ባህሉ፣ ቋንቋው፣ ማንነቱ፣ ታሪኩና ክብሩ ጠብቆ የተጓዘው በየጊዜው ጨካየቋኞችና ወራሪዎች ስልለገጠሙት አልያም ስላለፈተኑትና ህልውናውን ለማጥፋት ባለመፈለጋቸው አይደለም።

ይልቁንስ በሁሉም የትግል ምዕራፎችና ታሪኮቹ የገጠሙትን ሐያላን አየመከተ ፣ መስዋእትነት እየከፈለና ጠላቶቹ እያሸነፈ ነው እዚህ የደረሰው።
የዛሬ ትውልድም የአባቶቹ ታሪክ በመድገም በጀኖሳይደሩ የአብይ አሕመድ አገዛዝ የተፈፀመበት ከባድ የጀኖሳይድ ጭፍጨፋ በመመከት የትግራይን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ የጀግንነት ታሪኩ እየደገመ ይገኛል።

በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ጀኖሳይድ ከባድ ቢሆንም የትግራይ ወጣት ህዝቤ ከገፀምድር አይጠፋም፣ የትግራይ መሬት አይቆረስም፣ ክብሬና ማንነቴ አይራከስም በማለት በግንባር፣ በደጀን እና በውጭ የተለያዩ ሃገራት ጠንካራ አንድነት በመፍጠር የጀኖሳይዳዊ ወራሪ አጀንዳ አክሽፎታል። የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት የመጡትን ጠላቶች ከአብዛኛው የትግራይ መሬት ጠራርጎ በማባር የአብይ አሕመድ ጀኖሳይዳዊ አገዛዝ የፕሪቶርያው ስምምነት ተገድዶ እንዲፈረም መደረጉ ይታወቃል።

ትግራይ የፕሪቶርያው ስምምነት በሰላማዊ መንገድ እንዲተገበር ረዥም ርቀት ብትጓዝም የአብይ አሕመድ ጀኖሳይዳዊ አገዛዝ በፈጠራቸው አደናቃፊና አፍራሽ ተግባራት ምክንያት አልተሳካም። የፕሪቶርያው ስምምነት አፈራራሚ አካላትም ቢሆን የሚጠበቅባቸውን ሐላፊነት ሊወጡ አልቻሉም። በመሆኑም ከብዙ ትዕግስትና ተማፅኖ በኻላ ስምምነቱ እንደፈረሰ በመገንዘብ በህዝብ ተመርጦ በይደር የቆየው የትግራይ መንግስት ወደ ቦታው ተመልሶ እንዲመራ ተወስኖ ማስተካከያዎች ተደረጓል።

በማስተካከያው መሰረት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዲስ መልክ አቃፊና አሳታፊ በሆነ አግባብ ተስተካክሎ የስራ አስፈፃሚ ምክርቤት በማቋቋሞ ወደስራ ተገብቷል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የውስጥ ዓቅምና ራስን የማስቻል ብቃትን በማጠናከር፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት በማረጋገጥ የትግራይ መከተ በድል ለማጠናቀቅ እንዲሁም በወራሪዎች ስር እየተሰቀመየ የሚገኝ ህዝባችን ነፃ ለማውጣት እና የተሰደደና በተለያዩ መጠሊያዎች በስቃይ እየማቀቀ የሚገኝ ህዝባችን ወደ ቄዬው እንዲመለስ ማስቻል ቁልፍ አጀንዳው በማድረግ በመስራት ላይ ይገኛል።

የፕሪቶርያው ስመምነት ከማፍረስ ጎንለጎን ጀኖሳይዳዊ የአብይ አሕመድ አገዛዝ ትግራይን በሙሉ ከበባ በማድረግ እንድትንምበረከክና እንድትማስን የሚያስችሉት መጠነሰፊ ነውራም ተግባራት እየፈፀመ ይገኛል። ይህ እንዳይበቃ ደግሞ የወጠነውን የትግራይ ጀኖሳይድ ለመፈፀም በአሁኑ ወቅት ጦርነት ለመጀመር የሚያስችሉት ሁሉም ዓይነት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ዝግጅቶች እያከናወነ መሆኑን በቀጠራቸው ተላላኪዎች በኩል ፕሮፓጋንዳውን በመደስኮር ላይ ይገኛል።

በተመሳሳይ መልኩ ከአሁን በፊት ከፈፀማቸው የድሮን ጥቃቶች በተጨማሪ ወደ ወታደራዊ ስምሪቶችና ትንኮሳዎች የተሸጋገረበት ሁኔታ እየተስተዋለ ነው። በመሆኑም የትግራይ ህዝብና መንግስት እጅና እግራችን ጠፍረን ለሚመጣብን አደጋ የምንጠብቅ ባለ መሆኑ፣ በሰላማዊም ይሁን ለሚመጣብን ማንኛውም አደጋ ለመመከት ሁሉን አቀፍ ውስጣዊ ዓቅምቻችንና የራስን ማስቻል ብቃታችን ለማጠናከር ህጋዊና ሞራላዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን ግዴታችን መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

የአብይ አሕመድ ጀኖሳይዳዊ አገዛዝ አጀንዳዎች በትግራይ ውስጥ ለማስረፅ ያልተሳካላቸውና በትግራይ ህዝብ የተደራጀ ተጋድሎ የተተፉ ተከፋዮች፣ ትግራይን በማጠልሸት ሌትና ቀን እየሰሩ ናቸው። የትግራይ ወጣት ተደናግሮ አከባቢውን ለቆ እንዲወጣ ያለመታከት እየሰሩበት ይገኛሉ። የተወሰኑ አካላትም አውቀውም ይሁን ተደናግረው የጀኖሳይደሩ አገዛዝና ጋሻ ጃግሬዎች ወንጀሎች ለመሸፈን እንዲሁም የትግራይ የመከተ ዓቅም ለማደናቀፍ ሙከራዎች ሲያደርጉ እየታየ ነው። አውቀውም ይሁን ተደናግረው በአገዛዙ ወጥመድ ውስጥ የገቡ አካላት ከጀኖሳይደሩ ቢላ ራሳቸው ሊያመልጡ ይገባል።

ከብርና ጀግንነት ከህዝብህ ጋር ስትወግን የሚገኝ ስለሆነ ተደናግረው የወጡ የትግራይ ወጣቶች ደግመው እንዲያስቡበትና ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ይገባል። የትግራይ ወጣት የአብይ አገዛዝ አየተፈፀመበት ካለው አፈሳ፣ የትግራይ ህዝብ ከብርና ሞራል ከሚያዋርድ እንዲሁም ለጤና ችግር ከሚያጋልጥ ተግባራት እራሱን ማዳን ይገባእ።

በዋነኝነት ደግሞ የትግራይ ፍትሐዊ ትግል ድል እንዲጎናፀፍ የሚያስችሉት በርካታ ምክንያቶች ያሉት በመሆኑ፣ የትግራይን መከተ ለድል እንዳይደርስ የጀኖሳይደሩ አገዛዝ አጀንዳ በመቀበል ፀረ የትግራይ ህዝብ ህልውና ተሰልፈው የሚገኙ አካላት የጊዜ ጉዳይ ከላሆነ በስተቀር ከታሪክ፣ የሞራልና የህግ ተጠያቂነት የማያመልጡ መሆናቸው ሊገነዘቡ ይገባል።

በመጨረሻ፣ የትግራይ ህዝብና መንግስት ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ፍላጎታቸው ብቻ ሳይሆን የሚቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ። የሰላም አማራጭ ለያዘ ሁሉ በራችን ክፍት ነው። ይሁን እንጂ የሰላም ዕድል በመዝጋት የትግራይ ህዝብ አማስኖ ለማጥፋት የሚደረገው ማንኛውም ሙከራ የከፋ አደጋ ከማስከተል ውጭ ሌላ ትርፍ ሊኖሮው አይችልም። በመሆኑም በሰላማዊ ድርድርና ንግግር የሚፈታ ችግር እንጂ ውሸትና ማወናበድ በመደጋገም የሚደናቀፍ የትግራይ ህዝብ ትግል የለም፣ ለወደፊትም አይኖርም።

የትግራይ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ሐምለ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
መቐለ

በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተቀባይነት የሌላቸውና ስምምነቱን የሚጥሱ መሆናቸው የእንግሊፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስራቤት ገለፀ።በምዕራብ ትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ...
10/07/2026

በምዕራብ ትግራይ የቀጠለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተቀባይነት የሌላቸውና ስምምነቱን የሚጥሱ መሆናቸው የእንግሊፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስራቤት ገለፀ።

በምዕራብ ትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መቀጠላቸው፤ በግድ መፈናቀል፣ እስራት እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ተቀባይነት የሌላቸው እና የሰላም ሂደቱን የሚያደናቅፉ መሆኑን የኢንግሊዝ የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር በፃፈው ደብዳቤ አሰታወቀ።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት የእንግሊዝ ፓርላማ አባል እና የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ሰር ዴቪድ አልተን ለውጭ ጉዳይና ዓአለም አቀፍ የልማት ትብብር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጄኒ ቻፕማን ለጻፉት ደብዳቤ በሰጡት ምላሽ ነው።

ሚንስትሯ በምዕራብ ትግራይ በሰላማዊያን ሰዎች ላይ የሚፈፀሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደሚረዱ እና ከዴቪድ አልተን አመለካከት ጋር እንደሚስማሙ በደብዳቤያቸው ላይ አመላክቷል።

እንግሊዝ የፕሪቶሪያ ስምምነትን እንደምትደግፍ እና የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ የሰብአዊ መብቶችን ለማክበር እንዲሁም ሲቪሎችን ለመጠበቅ ከትግራይ አመራር ጋር እንዲሰራ ግፊት ማድረጓን እንደምትቀጥል ገልፀዋል ።

የእንግሊዝ መንግስት ማዕቀቦችን ጨምሮ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ለማስቻል እንደዚህ አይነት ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን መከታተሉን እንደሚቀጥልም በደብዳቤው ተመላክቷል።

ቻፕማን እንዳሉት እንግሊዝ በጦርነቱ ምክንያት ከትግራይ የተፈናቀሉ ሰዎች በፈቃደኝነት እና ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በደብዳቤው አጥብቀው አሳስበዋል።

“በሰላማዊያን ሰዎች ላይ የሚፈጸሙት ግፍ እንዲቆም፣ ተጠያቂነት እንዲኖር እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እና መልሶ ግንባታ እንዲተገበር ለማረጋገጥ ሁሉንም የዲፕሎማሲ መንገዶችን እንዲከተሉም ማረጋገጥ እፈልጋለሁ” ሲሉ ዴቪድ አልተን ባቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

10/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሓምሌ 03/2018 ዓ.ም | | |
----

09/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም | | |
----

09/07/2026

ከብልፅግና መንግስት በፕሪቶርያ የተስማማነው ሁለታችን በመሬት የነበረው እውነታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁለታችን አስፈላጊ ስለ ነበረ ነው-ሚኪኤለ ኣስገዶም

08/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም | | |
----

07/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሰኔ 30/2018 ዓ.ም | | |
----

የትግራይን አቅሞች ማጠናከር ለህዝብ ህልውና ዋስትና!የትግራይ ህዝብ በላዩ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ተፈፅሞበት ላለፉት ዓመታት የተለያዩ የሞትና የመከራ ዓይነቶችን ሲያስተናግድ ቆ...
07/07/2026

የትግራይን አቅሞች ማጠናከር ለህዝብ ህልውና ዋስትና!

የትግራይ ህዝብ በላዩ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ተፈፅሞበት ላለፉት ዓመታት የተለያዩ የሞትና የመከራ ዓይነቶችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። እንደ ህዝብ መቀጠል የለበትም የሚል ፍርድ የተበየነበት በመሆኑ፣ በየቀኑ በወራሪዎች ጥይት፣ በረሃብና በበሽታ ፍዳውን እያየ ይገኛል።

ጀኖሳይድ ፈፃሚው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ እንደ ሁኔታው እየቀያየረ በጥይትና በረሃብ የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እየሰራ ይገኛል። ሁሉንም ተቋማቱና አቅሞቹን በማሰማራት፣ የትግራይን ህዝብ ተፈጥሯዊ የመኖር መብት ለአደጋ ዳርጎታል። በተጨማሪም ሠራዊቱንና ታጣቂ ኃይሎቹን በመላው ትግራይ በማሰማራት፣ ዳግም ህዝቡን ለመጨፍጨፍ፣ ሴቶችን ለመድፈር፣ የቀሩትን ተቋማት ለማውደም እንዲሁም በአጠቃላይም ትግራዋይ ሆኖ መኖር የማይቻልበት ደረጃ ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት፣ የዘር ማጥፋቱ እንዲቆምና ሁሉም ልዩነቶች በውይይትና በድርድር እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም፣ የአገሪቱን ህዝቦች በኃይል ለመጨቆን የሚንቀሳቀሰው አብይ አህመድ ሁሉንም የሰላም አማራጮች በመዝጋት ዳግም ደማዊ ጦርነት ለማስነሳት እየተዘጋጀ ይገኛል።

የትግራይ ህዝብም ከዚህ ዓይነት አደጋ ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብት አለው። ይህ መብት የሚረጋገጠው አቅሙንና ብሔራዊ ተቋማቱን በማጠናከር ብቻ ነው። ጠላትም ይህን ስለሚያውቅ፣ ለትግራይ ክብርና ሀላፊነት የሌላቸውን ጥቂት ከሃዲዎች በመጠቀም ይህን አቅም ለማፍረስ ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል። ይህም ብሔራዊ ተቋማትን ለማፍረስ የሚደረገው ዘመቻ፣ በመተማመንና በመግባባት ላይ የተመሰረተውን የብሔራዊ አቅም ማጠናከር ለማስተጓጎል ታልሞ እየተሰራ ነው።
እንደ ብሔር የመኖር መብቱ የተነፈገ ህዝብ፣ ከፍተኛ የመታገል ምክንያት አለው። የትግራይ ህዝብም ረጅም የትግል ልምድ ያለው፣ መሰረታዊ ጥቅሙንና የሚገጥመውን አደጋ በግልጽ የሚያውቅ ህዝብ ነው። ስለዚህ ጥቅሙ እንዴት እንደሚረጋገጥና አደጋዎቹ እንዴት እንደሚቋቋሙ በመግባባት እንጂ፣ በኃይል የተጫነ አጀንዳ በላዩ ላይ ሊጫን አይችልም።

ይህን እውነታ ወዳጅም ሆነ ጠላት ቢያውቀውም፣ ጠላት የትግራይን አቅም በማዳከም የዘር ማጥፋት ፕሮጀክቱ ለማሳካት በሰፊ የጥላሸት ዘመቻ ተሰማርቷል። በዚህም ዘመቻ ውስጥ ጥቂት ተጋሩ ነን የሚሉ ከሓዲ ሰዎች ከሥርዓቱ ጋር ተሰልፈው፣ ሌሎችም በተለያዩ መንገዶች ተደናግረው የዚህ ዘመቻ መሣሪያ ሆነው እያገለገሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ሆን ብለውም ይሁን ሳያውቁ በዚህ ዘመቻ የሚሳተፉ በታሪክ ጥቁር አሻራ ከመተው በተጨማሪ፣ ከሕግና ከሥነ ምግባር ተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም።

በዚህ አጋጣሚ ለመላው ህዝባችን ልናስተላልፈው የምንፈልገው መልእክት፣ አቅምህን እንዳታጠናክር የሚደረገውን የጠላት ዘመቻ ዓላማ በመረዳት፣ ይህን ሴራ ለማክሸፍ የምታደርገውን ትግል ማጠናከር እንዳለብህ ነው። የትግል ልምድህ እንደሚያረጋግጠው፣ ሉዓላዊነትህ፣ ህልውናህና ጥቅሞችህ የሚረጋገጡት አቅምህ ሲጠናከር ብቻ ነው።

ከዚህ ውጭ የሚረጋገጥ ጥቅምም ሆነ የሚቆም አደጋ የለም። አቅምህ ሲጠናከር ብቻ እንደ ህዝብ ህልውናህ ይረጋገጣል፤ በወራሪዎች ሥር በማንነቱ እየተገደለና እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ነፃ ይወጣል፤ ከቤቱ ተፈናቅሎ በመጠለያ ማዕከላት ውስጥና ከሀገር ውጭ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ወደ መኖሪያው ይመለሳል፤ ሉዓላዊነትህና ብሔራዊ ጥቅሞችህም ይረጋገጣሉ። የምትመኘው ሰላምም አቅም ሲኖርህ ብቻ ይረጋገጣል።

ስለዚህም፣ አሁንም አንድነትህን በማጠናከር፣ የተደቀነብህን አደጋ የሚመክትና ክብርህን የሚያስጠብቅ ሁለንተናዊ አቅም መገንባት ለነገ የማይባል አጀንዳ በመሆኑ፣ የጠላትን ሴራ እያከሸፍክ በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ኃላፊነት እንድትሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።

06/07/2026

የምሽት 2፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና - ሰኔ 29/2018 ዓ.ም | | |
----

Address

Mekelle
Tigray
7000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tigrai Television Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share