በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Lanfuro Woreda Communication/

  • Home
  • Ethiopia
  • Tora
  • በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Lanfuro Woreda Communication/

በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Lanfuro Woreda Communication/ Lanfuro communication is a 24 hour information provider public media. To disminate information
(3)

የስልጤ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት የወረዳና ከተማ አስተዳደሮችን የ2018 የሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ።ጥቅምት 3/2018 :-የስልጤ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚ...
13/10/2025

የስልጤ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት የወረዳና ከተማ አስተዳደሮችን የ2018 የሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ።

ጥቅምት 3/2018 :-የስልጤ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተያዘው 2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት እቅድ ክንውን በመገምገም በቀጣይ ተግባራት ላይ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በመድረኩ ላይ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት እቅድ ክንውን አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች በእቅድ ዝግጅት፣ በፈጻሚን ማዘጋጀት ሒደት፣ በአባላት መዋጮ አሰባሰብ ላይ፣ በአባላት ስነ ምግባር፣ በአቅም ማጎልበቻ ስልጠና፣ በተቋማዊ አደረጃጀትና ግብዓት አቅርቦት፣ በድጋፍና ክትትል እንዲሁም የፓርቲ ስርዓትን በተገቢው ከመዘርጋትና ከሌሎች የፓርቲ ዲሲፕሊን ስራዎች ጋር ተያይዞ ያከናወኗቸውን ዝርዝር ተግባራትን እቅድ ክንውን በማቅረብ ጉድለቶችን የለየ ውይይት ተደርጓል።

በዚህም በየደረጃው የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረኮችን በወቅቱ በማካሄድ ፈጥኖ ወደ ተግባር ምዕራፍ መሸጋገር፣ ከዞን ጀምሮ እስከ ህብረት ኮሚሽን ድረስ የሩብ ዓመቱን ኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን በጊዜው በማካሄድ ለኮሚሽንና ለፓርቲ አደረጃጀቶች ግብረ መልስና የግኝት ምክረ-ሀሳብ መስጠት፣ ከ2 በላይ የብልፅግና ህብረት ኮሚሽን ባለባቸው ቀበሌዎች ህብረቶቹን እንደ ቀበሌ የሚያስተባብሩ የቀበሌ ኮሚሽኖች እንዲደራጁ የተቀመጠውን አቅጣጫ ፈጥኖ ተግባራዊ ማድረግና የመሳሰሉት በመድረኩ በጥንካሬ ታይተዋል።

በሌላም በኩል የአደረጃጀቶችን አፈፃፀም ከማመጣጠን አንፃር ጉድለቶች የሚስተዋሉ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኘው የኮሚሽን ስራ አመራር ኮሚቴ ለተቋማዊ አቅም ግንባታ ስራ በቀጣይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በቅ/ጽ/ቤቶቹ ላይ በበጀት ዓመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት ከተደረገ ድጋፍና ክትትል መነሻ የተዘጋጀ ግብረ መልስ ቀርቦ በጉድለቶች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሽኩር ጀማል ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት የሁሉም መዋቅር የኢንስፔክሽን ጽ/ቤቶች ግብና ተልዕኳቸውን በውል ተገንዝበው በቀጣይ ወራት የጽ/ቤቱን እቅዶች በተሻለ ለመፈጸም መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ጽ/ቤቱን በግብዓት በማደረጃትና የግንዛቤ ማስጨበጫ አማራጮችን በማስፋት በሁሉም ዘርፎች ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባም አቶ ሽኩር አስገንዝበዋል።

Via ስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ

የወረደው  ፍርድ ቤት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ስራ በይፋ ጀምሯል ።➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ጥቅምት 3/2018፣(ላንፉሮ ኮሙዩኒኬሽን) የላንፉሮ ወረዳ  የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  መደበኛ የዳ...
13/10/2025

የወረደው ፍርድ ቤት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ስራ በይፋ ጀምሯል ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ጥቅምት 3/2018፣(ላንፉሮ ኮሙዩኒኬሽን) የላንፉሮ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ስራ በዛሬው እለት ተጀምሯል ።

ፍርድ ቤቱ ባለፉት ሁለት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው መቆየቱ ይተወሳል ስለሆነም በዛሬው ዕለት የ2018 በጀት አመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ከባለድርሻ አካላት በማካሄድ በይፋ ጀምሯል።

የላንፉሮ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰይፈዲን ሻፊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የወረዳው ፍርድ ቤት ከዛሬ ጥቅምት 3/2018 ጀምሮ መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል ብለዋል።

ፍርድ ቤት የአገልግሎት ተደራሽነቱንና ፍትሃዊነቱን በማረጋገጥ ህዝቡን ማገልገል እንደለበት ተነግሯል ።

ዘርፉ በተለየ መልኩ ነጻነት፣ተጠያቂነትና ግልጸኝነትን መላበስ አለበት ያሉት አቶ ሰይፈዲን ለዚህ ስኬት የዳኝነትና የፍትህ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ቅንጅትና የአገልግሎት መዘመን የተፈጠነ ውሳኔ ለመስጠትና የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል አብራርተዋል ።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይም የላንፉሮ ወረዳ ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ተሚማ የግብረ፣የላንፉሮ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተውፊቅ ከማልን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳተፊ ሆኖዋል።

13/10/2025
የላንፉሮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን በተገቢው ማሳለጥ እንዲችል ከተቋሙ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ።  *▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰*ጦራ/ጥቅምት-3/20...
13/10/2025

የላንፉሮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን በተገቢው ማሳለጥ እንዲችል ከተቋሙ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ።
*▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰*
ጦራ/ጥቅምት-3/2018 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን በተገቢው ማሳለጥ እንዲችል ከተቋሙ ባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው እለት ተወያይቷል።

ጽ/ቤቱ ከህዝብ ክንፍ እና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የቀጣይ የ2ተኛውን ሩብ አመት እቅድ ላይም ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ ተቋሙ የእስካሁን አጠቃለይ የአፈጻጸም ሂደት ላይ በነበሩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበረም ተብራርቷል።

መድረኩን የመሩት የላንፉሮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ሁሴን አልዬ እንደገለጹት በቀጣይ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ችግሮችን እየለየን ክፍተቶችን የምንቀርፍባቸውን ሁኔታዎችን እየፈጠርን የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ሚሊንየም 1ኛና መካከለኛ  ደረጃ ት/ቤት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሁለተኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ የተሻለ አፈፃፀም  በማስመዝገብ የ50ሺ...
13/10/2025

እንኳን ደስ አላችሁ!

በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ሚሊንየም 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሁለተኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የ50ሺህ ብርና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

13/10/2025
13/10/2025
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 5 የትምህርት ኢኒሼቲቮች ይፋ ሆኑ!ጦራ፣ጥቅምት 3፣2018 (ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል...
13/10/2025

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 5 የትምህርት ኢኒሼቲቮች ይፋ ሆኑ!

ጦራ፣ጥቅምት 3፣2018 (ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ አምስት አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ይፋ አድርጓል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ዘርፍ ጉባዔ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴ እና የክልሉ አፈ ጉባኤ ፋጤ ሴርሞሎን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምርት ቢሮ ሃላፊ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሳደግ ዘርፍ ብዙ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም ደረጃቸውን የጠበቁ ት/ቤቶችን ከመገንባት ጀምሮ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን መተግበር እንደተጀመረ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሃብት በማሰባሰብ የትምህር ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የመምህራንን ብቃት የማሳደግ ሥራ መከናወኑን ጠቁመው 417 ሺህ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለት/ቤቶች መሰራጨታቸውንም ተናግረዋል፡፡

#ፋና

የወባ በሽታ ሥርጭትን ለመከላከል ቤት ለቤት የሚካሄደው የወባ መከላከያ ኬሚካል ርጭት በትኩረት  መሰራት እንዳለባቸው የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ አሳሰቡ።➖➖➖➖➖➖➖➖...
13/10/2025

የወባ በሽታ ሥርጭትን ለመከላከል ቤት ለቤት የሚካሄደው የወባ መከላከያ ኬሚካል ርጭት በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው የላንፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ አሳሰቡ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ጥቅምት 03/2018 (ላንፉሮ ኮሙዩኒኬሽን) በላንፉሮ ወረዳ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም ለመጥፋት በወረዳው በ18ቱም ቀበሌያት የቤት ለቤት የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ለማካሄድ ለጤና ባለሙያዎች እና ለረጪዎች እንዲሁም ለሌሎችም ለጤና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የላፉሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ ሥልጠናውን መድረክ ባስጀመሩበት ወቅት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የወባ በሽታ የጨመረ በመሆኑ የሚደረገው የቤት ለቤት ርጭት በተገቢው መከናወን እንዳለበት ገልፀዋል።

የላንፉሮ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ስርበላ በመክፈቻ ንግግራቸው የወባ በሽታን ለመከላከል የአከባቢ ቁጥጥር፣ የአልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም እና የቤት ዉስጥ የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት ማካሄድ እንደሆነ ገልፀው በርጭቱ 24,720 ቤቶች ተደራሽ እንደሚደረጉም ተጠቅሷል።

ስልጠናው ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚቆይም የገለፁት የጽ/ቤቱ ምክረ ሀላፊ አቶ ዳሴ ሀሰን ለዚህም የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት መሆን አለባቸው ብለዋል።

ስልጠናው በዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በመድረኩ የላንፉሮ ወረዳ ምክትል የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሙሀባ ረሺድ እና አቶ አብደላ አህመድ ፣የጤና ባለሙያዎች እና ረጪዎች እንዲሁም ሌሎችም የጤና ባለድርሻ አካላት ተሳተፊ ሆኖዋል።

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን"ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ"በሚል መሪ ቃል በላንፉሮ ወረዳ ጦራ ከተማ በልዩ...
13/10/2025

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን"ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ"በሚል መሪ ቃል በላንፉሮ ወረዳ ጦራ ከተማ በልዩ ልዩ ትርዒቶች እና ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል::
*▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰*
ጦራ/ጥቅምት-3/2018 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን"ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ"በሚል መሪ ቃል በስልጤ ዞን በላንፉሮ ወረዳ ጦራ ከተማ በልዩ ልዩ ትርዒቶች እና ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል::

በላንፉሮ ወረዳ ጦራ ከተማ የወረዳው አስተባባሪ አካላት፣የፖሊስ አባላት፣አመራሮች፣የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተው"ሰንደቅ ዓላማችን የዘመናት የነፃነታችን እና የሥልጣኔያችን አብሪ ኮከብ"በሚል መሪ ቃል ለ18ኛ ጊዜ የሰንደቅ አላማ ቀንን በደማቅ ስነስርአት እየተከበረ ይገኛል።

የላንፉሮ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ተሚማ ልግብቾ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ የባንዴራ የመስቀል ስነ ስራዓት በማካሄድና መልዕክቶችን በማስተላለፍና የወረዳው የፖሊስ አባላት ወታደራዊ ትርዕቶችን በማሳየት እየተከበረ ይገኛል።

በትምህርቱ ዘርፍ ጠንክረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሳያ ነው ፦ አቶ ዘይኔ ቢልካ!ይህንንም ልምድ ወደ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማስፋት እን...
12/10/2025

በትምህርቱ ዘርፍ ጠንክረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሳያ ነው ፦ አቶ ዘይኔ ቢልካ!

ይህንንም ልምድ ወደ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማስፋት እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ተናግራዋል፡፡

የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ለውጤቱ መብቃት አስተዋጽኦ ለደረጉ መምህራን የሽልማትና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ-ግብር በወራቤ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በዚህ ወቅት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንደገለጹ ትምህርት ለአንድ ሀገር ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት መሠረት በመሆኑ ከዘርፉ የሚጠበቀው ብቁ የሆነ የአመለካከት ፣የክህሎትና የእውቀት አቅም ያለው ከተለዋወጭ አለም ተሻግሮ መሄድ የማችል ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ትምህርት የልማቶች ሁሉ መሠረት መሆኑን በማንሳት በትምህርት ዘርፉ ከተሰራ በሁሉም ልማት ዘርፍ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡

በዞኑ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ትኩረት በአሁን ሰዓት ከ47 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ከ365 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ከ700 በላይ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ይህንንም የትምህርት ጥራት ለማሻሻልና ተሳትፎ ለማሳደግ ባለሀብቶች ፣አርሶ አደሮች ፣መላው ማህበረሰብ በዚህ ዓመት ብቻ ከ333 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ርብርብ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በዚህም ከፍተኛ መሻሻሎች ቢኖሩም የትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ከልሰጠን የምንፈልገው ደረጃ መድረስ እንደማይቻል በ2017 በተሰጠው ብሔራዊ ፈተና ማየት ችለናል ብለዋል

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ የዳሳሰ ጥናት አድርገን በመለየት በቀጣይ መላውን ህዝብ ያሳተፈ ኮንፈረንስ ለመፍጠር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደሚቻል የሀይራንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማሳያ መሆኑን አቶ ዘይኔ አንስተዋል፡፡

በ2007 የስልጤ ልማት ማህበር ለማህበራዊ ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በተለም በትምህርቱ ዘርፍ ትውልድን የመቅረፅ ጉዳይ ነው በሚል ለመምህራንና አመራሩ አደራ በመስጠት በተደረጉ ጥረቶች እስካሁን በተከታታይ ዓመታት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከሀገሪቱ ከሚገኙ ግንባር ቀደም ትምህርት ቤቶች ተጠቃሽ እንዲሆን ተድርጓል ብለዋል፡፡

ለዚህም ልማት ማህበሩ በትምህርት ዘርፍ አንግቦ ለተነሰው ጥረት የትምህርት ቤቱ አመራሮችና መላው መምህራን ለደረጉት ጥረት አቶ ዘይኔ በዞኑ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ይህንንም ቀጣይነት እንዲኖራው ተግታን መስራት ይኖርብናል ያሉት አቶ ዘይኔ ይህን ተግባር ለማሳደግ ባለሀብቶቻችን የሰነቁት ሰናይ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አቶ ዘይኔ አክለውም በቀጣይ በዞኑ ከአንድ በላይ ሀይራንዚ ትምህርት ቤቶች ለማስፋት እንቅስቃሰ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል

በዞኑ የሚገኙ ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ይህንን ልምድ ወስደው እንዲሰሩ ያሳሰቡት አቶ ዘይኔ ለዚህም የትምህርት አመራሩ ፣ መምህራንና ወላጆች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቋል፡፡

የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚ አቶ ሸምሴ ኑሪ በበኩላቸው ስልማ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች የልማት መስኮች ያሉ የልማት ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ሰናይ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንም አመላክተዋል።

በተለይም በትምህርት ዘርፍ በሀገር አቀፍ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማህበረሰብ መፍጠር ዋነኛ ዓላማ እንደሚገኝም ተናግራዋል።

በልማት ማህበሩ በ2007 ዓም የተቋቋመው ይህ የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ትምህርት ቤት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በሀገር ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ስማ ጥሩ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ትምህረት ቤቱ ከባለፉት ዓመታት በላቀ መልኩ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ብቻም ሳይሆን ከስፈተናቸው 105 ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ በማሳለፍ መሆኑን በአብነት አንስተዋል።

በቀጣይ በት/ቤቱ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ቀጣይነት ባለው መልኩ መሄድ እንዲችል የልማት ማህበሩ አባላት እና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ት/ቤቱ ከተመሰረተበት ጀምሮ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም ደግሞ የተናገሩት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አብዱልመጂድ ኑረዲን ናቸው ፡፡

በዛሬው እለት በዚሁ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በተዘጋጀው የእውቅና እና የሽኝት መርሓ-ግብር ላይ የፌዴራል ፣የክልል ፣የዞን ፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣የትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ተሸላሚ ተማሪዎችና ወላጆች ፣ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚኖሩ የስልጤ ባለሀብቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

Via ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

Address

Silti
Tora

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Lanfuro Woreda Communication/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Lanfuro Woreda Communication/:

Share